Get Mystery Box with random crypto!

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከ 3 ሚልዮን በላይ ህዝብ ለከፍተኛ ረሀብ አደጋ እንደተጋለጠ ተመ | Affini Media and Communication

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከ 3 ሚልዮን በላይ ህዝብ ለከፍተኛ ረሀብ አደጋ እንደተጋለጠ ተመለከተ፤
==================================:=
አፊኒ ነሐሴ 24፣2014
ሀዋሳ
በዘንድሮው ዓመት የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው አደጋ በክልሉ 17 ወረዳዎች የግብርና ምርት ሙሉ በሙሉ ውጤት አልባ መሆናቸውን ተከትሎ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ለከፍተኛ ረሀብ ተጋልጧል። ይሁን እንጂ እስከአሁን የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃውን ለሚመለከታቸው አካላት እንድሁም ለፌደራል መንግሥት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑና አስፈላጊ ትኩረትና ድጋፍ ማግኘት ባለመቻሉ ህዝቡ የመኖር እና ያለመኖር ፈተና እንደተጋረጠበት ለአሚኮ አሳውቋል።

የሲዳማ ህዝብ ለብዙ ዘመናት የምግብ ዋስትናውን ያለ ማንም እርዳት ያረጋገጠ፣ ከእራሱ አልፎ ሌላውን የሚመግብ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም እራሱን በእራሱ የማስተዳደር የፓለቲካ ጥያቄው በተመለሰ ማግስት ትኩረት ያላገኘ የረሀብ አደጋ፣ የህዝብን ፍላጎት ያማከለ ልማት እጦት፣ የመልካም አስተዳደር ችግር እየተፈታተነው ይገኛል። ለዚህም ማሳያዎች ሰሞኑን የክልሉ ኦድት ቢሮ ይፋ ባደረገው ሪፖርት መሠረት በአንድ አመት ውስጥ 197,025,436.32 ብር ጉድለት ተገኝቷል።

ከዚህም ባሻገር የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በዞን መዋቅር ወቅት የነበረ እና የአንድ አመት የክልሉ ፋይናንሻል ሪፖርት መረጃ በማሸሽ ተጠያቂነት እንዳይኖር ማድረጉ ይታወሳል። የሆነ ሆኖ የክልሉ መንግስት ለተከሰተው ረሀብ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት መስጠትና መረጃውን ለፌደራል መንግሥት፣ ለብሔራዊ አደጋ እና ስጋት፣ ለሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንድሁም ለተራድኦ ድርጅቶች እንድሁም ለሚመለከታቸው ሁሉ እንዲያሳውቅና አስቸኳይ ድጋፍ ልደረግላቸው እንደሚገባ የአደጋው ተጋላጮች ለአፊኒ ገልፀዋል። ፈጣን ምላሽ እንዲሰጣቸው እየጠየቅን እንደየአስፈላጊነቱ በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ ይዘን እንቀርባለን።

አፊኒ_ሚዲያና_ኮሙኒኬሽን
#Affini_Media_Communication
ትኩስ እና እውነተኛ መረጃዎችን ለማግኘት ይከታተላሉ
ዩቲዩብ:https://youtube.com/channel/UCzxVCZUtW-XmosukNkCXZEA
telegram:https://t.me/affinimedia
https://t.me/affinihasaaw