Get Mystery Box with random crypto!

አላታ ወንዶ በከተማው የመጀመሪያ የህዝብ መድኃኒት ቤት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዛሬ | Affini Media and Communication

አላታ ወንዶ በከተማው የመጀመሪያ የህዝብ መድኃኒት ቤት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዛሬው ዕለት አስመርቀዋል ፤
=======================================
አፊኒ ቀን ነሐሴ 16፣2014 ዓ.ም
ሀዋሳ
የአለታ ወንዶ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የረጅም ጊዜ የማህበረሰብ ጥያቄ የሆነውን የመድኃኒት አቅርቦት እና ተደራሽነት ለማረጋገጥ በአጭር የተሰራው ስራ የሚያስመሰግን እንደሆነ ተገልጿል ፡፡ በቋሚነት ይህንን መድኃኒት ቤት ሕዝቡ በባለቤትነት መምራት እንዳለበት አጽዕኖት ተሰጥተዋል ።፡

እንደ ከተማው ከንቲባ ጌዲዎን ጋቢሶ በበኩላቸው አሁን እየተሰሩ ከሚገኙ ስራዎች በተሻለ የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ሌት ከቀን እንሰራለን ሲሉ መልዕክታቸውን ያስተላለፈው ስሆን ፣ የሆስፒታሉ ስራ-አስኪያጅ አቶ ፍጹም ዳንጉራ ህዝብ መድኃኒት ቤቱን ወደ ስራ ለማስገባት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለተባበሩ፣ድጋፍ ላደረጉ ሁሉ በተገልጋይ ማህበረሰብ ስም አመስግነዋል ። በመጨረሻም አገልግሎቱ መጀመሩን በማብሰር ፣በሀገር ሽማግሌዎች ተመረቀው በይፋ አግልግሎት ጀምረዋል ።
እንዲህ አይነት መልካም ተሞክሮ በክልሉ በሁሉም አከባቢ መስፋፋት እንዳለባቸውም ተጠቅሷል ።
አፊኒ_ሚዲያና_ኮሙኒኬሽን
#Affini_Media_Communication
ትኩስ እና እውነተኛ መረጃዎችን ለማግኘት ይከታተላሉ
ዩቲዩብ:https://youtube.com/channel/UCzxVCZUtW-XmosukNkCXZEA
telegram:https://t.me/affinimedia
https://t.me/affinihasaaw