Get Mystery Box with random crypto!

💠 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው።

የቴሌግራም ቻናል አርማ afe_werk — 💠 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው።
የቴሌግራም ቻናል አርማ afe_werk — 💠 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው።
የሰርጥ አድራሻ: @afe_werk
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 568
የሰርጥ መግለጫ

🇬🇳 በዚህ ቻናል ተሰምተው የማይጠገቡትን የአባታችንን
🌈 ተግሳጾችን

🌈 አባባሎችን
🌈 ትምህርቶችን ታገኙባቸዋላችሁ።
⚡በእውነት በረከታቸው አይለየን፤ በጸሎታቸው ይርዱን። አሜን!
🇬🇳 ጥር 8/5/2013

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-27 15:16:33
"ይስማዕከ እግዚአብሔር በዕለተ ምንዳቤከ!"

"እግዚአብሔር በመከራህ ቀን (ልመናህን) ይስማህ!" (መዝ. ፲፱:፩)

በአንደበቱ እየመረቀ በልቡ ከሚራገም፤
•በወሬ ብዛት ለጠላት አሳልፎ ከሚሰጥ፥
•የሚመክሩትን ከማይሰማ፥
•የወደደ መስሎት በግብረ ጸራዊ ከሚገኝ
•በአጠቃላይ ከቢጽ ሐሳዊ ሁሉ ይሰውርዎ!

@ Dn Yordanos Abebe

https://t.me/zikirekdusn
486 viewsDiakon Mule Ayalew , 12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 21:26:44
በሀገረ እግዚአብሔር / በቅድስት ምድር /
በእመቤታችን ርስተ ምድር በሆነችው በኢትዮጵያ የሰው ልጅ ደም እየፈሰሰ ነው ፡፡
ኢትዮጵያ ሹሙ እንደ ጠፋበት ንብ ህዝቡ ከተበታተነ ሰነበተ። የሰው ሕይወት የውሻ ሕይወት ያክል ተቆጥሮባታል ፡፡
አምላክ ከ 22ቱ ፍጥረታት ለይቶ አምላካዊ ክብሩን
የሰጠው የሰው ፍጡር እየሞተም እየገደለም ነው ፡፡ ሰው ሠውን እያደነ ነው ፡፡
ከሰው ሕይወት ይልቅ ስንዝር መሬት ትልቅ ከበሬታ አግንታለች። ሁሉም ነገ ጥሎት ለሚሄድ መሬት እየተስገበገበ ነው። በዚች ሀገር የጥይት
ባሩድ እየሸተተ ነው ፡፡ ህዝቡ ደስታውን ሳያጣጥም ጥቁር ደመና እየመጣበት ነው ፡፡ በዚች ሀገር ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለው አስታራቂ ሽማግሌ ይፈለጋል፡፡
ቅዱሳን የመነኑበት ምድር በእግዚአብሔር ቁጣ እንደ እስራኤላውያን ቤተ መቅደስ እንዳትሆን እንፈራለን፣የሙሴ ጽላት ያለባት ምድር የሶረያን እጣ እንዳታገኝ እንፈራለን። ምንግዜም ሰው ሲያጠፋ ሀገር ባድማ ትሆናለች፡፡
በፈረሱ የተማመነ ይጠፋል ይላል ነብዩ ዳዊት።
የፈርዖን ታሪክ እንዳይደገም እንፈራለን ፡፡ የሰው ደም ከባድ ነው። ትልቅ መከራ ያስከፍላል ፡፡ ሳጥናኤል ክፉ
ነው። ከላይ ከትዕቢት ተራራ ላይ ሰቅሎ ወደ ውርደት ሸለቆ ይፈጠፍጣል፡፡
ምን ይሁን ኢትዮጲያውያን እርስ
በርስ አዳኝና ታዳኝ ሆነው በደማቸው ይራጫሉ ፡፡
አንደበቱ ቅባ ቅዱስ የተቀባ መሪ እቺ ሃገር ትፈልጋለች።


ለበለጠ join and join

@ETIOPIA_Hagerie


@Afe_Werk
283 viewsDiakon Mule Ayalew , 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 11:46:04 ክርክር ለማን በጀ ?

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እኛ #ልጆቿ በሁሉ ጎዳና ዝግጁ እንድንሆን ትፈልጋለች::
በሃይማኖት በምግባር
በጾም በጸሎት
በፍቅር በደግነት
በትህትና በትእግስት . . . ሁሉ ምሉዓን እንድንሆን ፈቃዷ ነው::

+በተረፈውም በቃለ እግዚአብሔር እንድንበረታና ለሚጠይቁን ተገቢውን ምላሽ የምንሰጥ እንድንሆንም ትመክረናለች:: (1ዼጥ3:15) ዛሬ ዛሬ ግን ብዙዎቻችን በጐ ምግባራትን ዘንግተን በመሰለን ጎዳና እንሔዳለን::

+በተለይ በዚህ የፌስ-ቡክ ገጽ ላይ ብዙ ነገሮችን (ያልተገቡትን ማለቴ ነው) ከክርስቲያኖች መመልከቱ ከመለመድ አልፎ አሰልቺ እየሆነ የመጣ ይመስላል::

እስኪ እነዚህን ጥያቄዎች ልብ በሏቸውና መልሱን ለራሳችሁ ስጡ:-

1.የፌስ ቡክ Account ለመክፈት ለምን አስፈለገን?

2.አሁን በየገጻችን ምን እየሰራን ነው?

3.በየጊዜው የምንጽፋቸውና የምንለጥፋቸው ነገሮች አላማቸው ምንድን ነው?

4.ፌስ ቡክ ውስጥ በመኖራችን ምን አተረፍን? ምንስ አጎደልን?

5.ፌስ ቡክ ይዘጋ (ይቅር) ቢባል ምን ይሰማናል?

6.በዚህ ገጽ ላይ እስከ መቼ ልንቀጥል አስበናል?

7.መጨረሻችን ምንድን ነው?

እስኪ እርሶ! እነዚህን ጥያቄዎች ለራስዎ ይመልሱና ራስዎን ይመርምሩ:: እኔ ግን በዚህ የማኅበረ-ሰብእ መገናኛ ገጽ ላይ ከተመለከትኩአቸውና መታረም ካለባቸው ነገሮች አንዱን ላንሳ::

(ከዓመታት በፊት የነበረው ችግር እጅጉን ገኖ፡ ከፍቶም በማየቴ ነው ጉዳዩን ዳግም ያነሳሁት)

☞ ብዙዎቻችን: በተለይ ሃይማኖትንና ሀገርን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ክርክር ውስጥ ገብተናል::

+በተለይ ደግሞ በተለያየ ጊዜ ማን እንደከፈታቸው እንኩዋ ባልተረዳናቸው ቡድኖች (Groups) ከኢ-አማንያን ጋር ከመከራከር አልፎ መዘላለፍ ዘወትራዊ ሥራ ሆኗል:: አስቸጋሪው ነገር ደግሞ ወደ ቡድኖቹ ማን እንደ ጨመረን አናውቅም::

+የከፋው ግን #የፈጣሪያችን: #የእመቤታችንና #የቅዱሳኑ ስም በክፉና በከንቱ ይነሳል:: ሀገርም ትሰደባለች፡፡ ትናንታችን ይንቋሸሻል፡፡ አበውም ይዘለፋሉ፡፡ ምናልባት "በእነዚህ የቡድን ገጾች የሚለጠፈው ነገር አስተማሪ ነው:: ቡድኖችም የተመሠረቱት ለበጎ ውይይት ነው" ትሉኝ ይሆናል::

☞እንደምትሉት ቢሆንማ ሸጋ ነበር:: ግን አልሆነም::

+ቀላል ቁጥር የሌላቸው ባልንጀሮቻችን ከክርክር አልፈው ጸብ የሚመስል ነገር ውስጥ በመግባታቸው ከክርስቲያን በማይጠበቅ መንገድ ሌሎች እምነቶችን፡ አንዳንዴም ጎሳን ጨምረው ሲዘልፉ እያየን ነው::

☞ ወንጌልን በዚህ መንገድ (በክርክር: ሲከፋም በብሽሽቅ) የምናስፋፋ የመሰለን ሰዎች ካለን ተሳስተናል:: እንዲያውም በነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እየቀለልን ይመስላል::

+ሲጀመር #ክርስትና የክርክር ሃይማኖት አይደለም:: ሲቀጥል ጥራዝ ነጠቅ የሆነ እውቀት ይዞ እንዲህ ዓይነት ነገር ውስጥ መግባቱ እጅጉን አደገኛ ነው:: ምክንያቱም ብዙዎቻችን የክርስትናን ስሙን ይዘናል እንጂ ጣዕሙ የገባን፡ ምስጢሩንም ያጣጣምን አይደለንም::

+እንዲያውም ፌስቡክ፡ ቴሌግራምና፡ ዋትሳፕ ላይ ባነበባትና ባደመጣት ትምህርት ራሱን እንደ አዋቂ ቆጥሮ የተማሩ ሰዎችን እንኳ የሚዘረጥጥ ሰው መመልከቱ አሁን አሁን ብርቅ አይደለም፡፡

+በዚያ ላይ አስፈላጊ ለሆኑ ጥያቄዎች በጊዜው መልስ ከመስጠት በቀር (ይሔውም በመምህራን ነው) እንድንከራከርም ሆነ መሰል ድርጊቶች ላይ እንድንሳተፍ እናት ቤተ ክርስቲያን ፈቃዷ አይደለም::

ምንተ ንግበር (ምን እናድርግ?) (ሐዋ. 2:37)

1.በልኩ እንማር!

=>እንኩዋን ለሌላ ለማስረዳት: ለራስ ለመዳንም በልኩ መማር ያስፈልጋል:: ጥቂት ነገርን ብቻ ይዞ የፌስ-ቡክ አርበኛ ለመሆን መሞከሩ አይረባንምና እንማር::

+ለዚህ ደግሞ ተመራጩ መንገድ . . . ከአበው: ከመምሕራን: ከጉባኤያት ተገኝቶ ከምንጩ መጠጣት ይገባል:: እድሉ የሌለን: በሰው ሃገር ያለን ደግሞ ከመልካም ድረ ገጾች አስፈላጊውን ትምህርት በጥሞና እንውሰድ::

+ያልገባን ነገር ካለም ማኅበረ ቅዱሳንን ለመሰሉ አገልጋዮች ልከን ማብራሪያዎችን ማግኘት እንችላለን::

2. ዓላማ ይኑረን!

=>የምናደርገው እያንዳንዱ ነገር ሁሉ እኛን ጠቅሞ ለሌሎቹ እንደሚተርፍ ካላመንበት ይቅር:: መጻፋችንም: መለጠፋችንም ለዓላማ ይሁን::

3.የከንፈር ምስክርነት ይብቃን!

=>ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ያጣችው በከንፈሩ የሚደልላት አይደለም:: ክርስትና የገባው: ሕይወተ አበውን የሚኖር ምዕመን ያስፈልጋል:: ስለ ተናገርን: ወይ ስለጻፍን መሰከርን ማለት አይደለም::

መመስከር ማለት እንዲህ ነው:-
ሀ..በሕይወት (አብነት በመሆን)
ለ..በአንደበት (ፊት ለፊት ሔዶ ዋጋ በመክፈል)
ሐ..በጽሑፍ (ይህ ግን ጾምና ጸሎት ትሩፋትም ካልተጨመረበት ፍሬ አይኖረውም)

4.በፍቅር ማስረዳት!

=>አንድን ኢ-አማኒ እምነቱን ስለ ሰደብክ አትመልሰውም:: የሚፈለገው በፍቅር: በማስተዋልና በጥልቀት ማስረዳቱ ነው:: ስብከት በፍቅር እንጂ በእልክ አይሆንምና:: (አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ለመገሰጽና የተሳሳተ መንገዳቸውን ለመግለጥ ጊዜ ምረጥ)

+ስለ ሃይማኖታችን የማይገባ ነገር ሲባልም ከቻልን በማስተዋል መመለስ: ካልሆነልን ነገሩን ከመምህራን ማድረስ ይገባል:: ዓላማችን የእኛና የሰው ሁሉ መዳን ከሆነ የእኛን መሻት ትተን የጌታን ፈቃድ ልንከተል ግድ ይለናል::

+ክርስትና ጠላትንም የመውደድ ጥልቅ ምስጢር አለውና ኢ-አማንያንን "ንስጥሮስ ሆይ! አንተን እወድሃለሁ:: ትምህርትህን ግን እጠላዋለሁ" ብለን እንደ ታላቁ ሊቅ #ቅዱስ_ቄርሎስ ልንናገር ይገባል::

ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍም እንዲህ ይላል:-

" " ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ: ብትበላሉ: እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ::
ነገር ግን እላለሁ:: በመንፈስ ተመላለሱ:: የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ . . .

የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው:: እርሱም ዝሙት: ርኩሰት: መዳራት: ጣዖትን ማምለክ: ሟርት: ጥል: #ክርክር: ቅንዓት: ቁጣ: አድመኝነት: መለያየት: መናፍቅነት: ምቀኝነት: መግደል: ስካር: ዘፋኝነት: ይህንም የሚመስል ነው::
አስቀድሜ እንዳልሁ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም:: " " (ገላ. 5:15-21)

" " አንዳንንድ ተከራካሪዎችንም ውቀሱ:: " " (ይሁዳ. 1:22)

=>ለዚህ ደግሞ #የሥላሴ ቸርነት: የድንግል #እመ_ብርሃን አማላጅነት: #የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን::

ስብሐት ለእግዚአብሔር ልዑል!
ወለወላዲቱ ድንግል!
ወለመስቀሉ ክቡር፡ ዕጸ ሣሕል!
አሜን!

https://t.me/zikirekdusn
252 viewsMule negn, 08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 21:24:50
ንጹሐን አቤላውያን ሞተው እኩያን ቃኤላውያን የሚፈነጩባት ኢትዮጵያ ፣ የዋሃን ናቡቴያውን ተገድለው አማጽያን ኤልዛቤላውያን እና አክአባውያን የሚንደላቀቁባት ኢትዮጵያ ፣ ክርስቶሳውያን ተሰቅለው በርባናውያን የተፈቱባት ኢትዮጵያ ድንኳኖቿ በዐራቱም ማዕዘን ተጨንቀዋል ።

በእግዚአብሔር አርዓያ እና አምሳል የተፈጠረ ክቡር የሰው ልጅ እንዲህ እንደ ቅጠል በከንቱ እየረገፈ እያዩ ከመኖር አለመኖር ይሻላል !!!!

የሰው ልጅ ከእንስሳ እና ከቁስ አካል በእጅጉ አንሶ የታየበት ጊዜ ጌታ ሆይ ቀን አምጣ !!!

ለበለጠ join and share
@ETHIOPIA_Hagerie 

@Afe_Werk
223 viewsMule negn, 18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 09:57:53
ኢትዮጵያን በዚህ ዘመን እንደገጠማት አስመሳይ፣ አሽቃባጭ፣ አታላይ መሪ ተብየ ደደብ ገጥሟት አያውቅም።

እርሱ ስለ ሰላጣ፣ ጎመን፤ ጓሮ ለጓሮ እየሄደ ይትኮረኮራል፤
በዚያ የስንት ንጽሐን ደም ይፈሳል።
አይሉት የግብርና ምንስቲር፣ ምን እሚሉት ነው እንድ ኩኖ መደዴብ።

ምን ያክል ጭካኔ ቢሞላብህ ነው፣ ምን አይነት ጥብዑ ልብ ቢኖርህ ነው፣
ምን አይነት ስጋ ለበስ አጋንንት ብትሆን ነው እንዲህ በሰው ደም ስልጣንህን የእምታረዝም።

ትንሽ ስቅቅ አይልህም። እንዴት የ 300 ንጽሐን ደም የአንድ ሰላጣ ያህል አላሳስብህ አለ?
እንዴት የአንድ የጎመን ቅጠል ያህል ቦታ አልሰጠው አልህ።

እግዚአብሔር የፍርዱን ይስጥህ፣ የንጽሐን የግፉዓን ደምና እንባ ይፋረድህ።




ሼር

ለበለጠ join
@ETHIOPIA_Hagerie

@Afe_Werk
263 viewsMule negn, 06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 02:58:54
የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር የነበሩ ለጠየቁት ጥያቄ ከጌታ ይረዱ ዘንድ ወደ ጌታችን የላካቸው እነማን ናቸው?
Anonymous Quiz
21%
ቅዱስ እስጢፋኖስ እና ቅዱስ ጴጥሮስ
21%
ቅዱስ እንድርያስ እና ቅዱስ ዮሐንስ
29%
ቅዱስ እስጢፋኖስ እና ቅዱስ አካዎህ
29%
ቅዱስ ፊሊጶስ እና ቅዱስ ናትናኤል
24 voters223 viewsMule negn, 23:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 17:25:30
የወለጋ ጭፍጨፋ ነው…!!

"…ሙስሊም ሁን፣ ኦርቶዶክስ ሁን ለኦሮሙማው አራጅ ደንታው አይደለም። ይሄ የምታዩት በአንድ ስፍራ ብቻ የታረዱ እና የተጨፈጨፉ ዐማሮች አስከሬን ነው ተብሏል።

"…የሟቾች ቁጥር ከ250 እንደሚበልጥም እየተነገረ ነው። የዐብይ አሕመድና የሽመልስ አብዲሳ ጥምር ጦር ከኦሮሚያ ምድር ዐማራን በዚህ መልኩ እያጸዳው ነው። ለምን ብሎ የሚጠይቅ ባለ ሥልጣንም፣ የመከላከያ አባልም የለም። ዘሩ እያለቀ አሁንም የዐብይ አሕመድን ዙፋን ይጠብቃል።

"…እነ አሕመዲን ጀበል፣ እነ ሃሩን ሚድያ ይሄ ለእነሱ ሞት አይደለም። ጎንደር ላይ ሞተ ያሉት እስላም የዐማራ እስላም ነው። የዐማራ ኦርቶዶክሶች የዐማራ እስላሞችን ፈጇቸው ብለው ሰማይና ምድሩን ያደባለቁት ፅንፈኞች ዛሬ አንዳቸውም የሉም። በኦሮሞ ምድር በኦሮሞዎች የሚገደሉ የዐማራ እስላሞች ለፅንፈኞቹ አራጆች ሙናፊቆች ናቸው። ትንፍሽ የሚልም አታገኙም።

"…መርጦ አልቃሽ ሁላ…!!

#Zemedikun_Bekele

ለበለጠ join and share
@ETHIOPIA_Hagerie

@Afe_Werk
228 viewsMule negn, 14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 15:12:30
እስካሁ ስንቴ ንስሃ ገብታችሁ ታውቃላችሁ?
Anonymous Poll
28%
ገብቼ አላውቅም (ምክኒያታችሁን ንገሩኝ
8%
አንዴ ገብቻ አውቃለሁ
28%
ሁለቴ ገብቼ አውቃለሁ
8%
አራቴ ገብቼ አውቃለሁ
28%
ብዙ ግዜ ንስሐ ገብቼ አውቃለሁ
25 voters219 viewsMule negn, 12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 10:20:52
#ካለመማራችን_በተማርን
።።።።።።።።።።።
ስልጣኔያችን በስይጥንና ሞልቶ፣
በመማራችን አለመማራችን ጎልቶ።
እናትሀገርን ደም ከምናስለቅ፣
የአባቶቻችን ታሪክ ከምናረክስ።
ምነው ስልጣኔው ቀርቶብን፣
ከአባቶቻችን እግር ስር ወድቀን፣
#ካለመማራችን (ማ:- ጠብቃ ትነበብ) በተማርን

@ETHIOPIA_Hageria


@Afe_Werk
205 viewsMule negn, 07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 11:09:20
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር አቅጣጫው ወዴት ነው

"የዘፈን ዳር ዳርታው ለእስክታ ነው" ይላሉ አንዳንድ ሰዎች ሲተርቱ እውነት ነው፣ በሃይማኖት ስም የሚነግዱ ሰዎች አሉ። ሰዎች እንጅ የሃይማኖት ተቋማቱ ግን ሌብነት ፅዩፍ እንደሆነ በፈጣሪም ዘንድ ኃጢአት መሆኑን ነው የሚያስተምሩት። ምን ዓይነት የኦዲት ህግ ልታወጡ ነው? እንደ እኛ ቤተክርስቲያን አንዳንድ ሌቦች ቢኖሩም ቤተክርስቲያን ግን የምትተዳደረው በአስራት በኩራትና ምዕመናን በበጎ ፈቃደኝነት ከሚለግሱት ገንዘብ ነው። መንግስት ለሃይማኖት ተቋማት በጀት ለመመደብ አስቦ ነው? ወይስ ከአስራት በኩራትም ከሚሰበሰብ ገንዘብ ታክስ ለማስከፈል ታስቦ ነው? ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ዛሬ በዋለው ፓርላማ ይህንን ተናግረዋል።

"የሃይማኖት ተቋማት የሌብነት ወንጀል እየተስፋፋባቸው ከመጡ ተቋማት መካከል ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ በኋላ የህግ ማዕቀፍ ተበጅቶ እያንዳንዱ የህዝብ ሃብት በትክክል መዋሉን ለማረገጋገጥ የሚያስችል የኦዲት ስርዓት ሊዘረጋ እንደሚገባ አሳስበዋል። በሁሉም ተቋማት ውስጥ የሚስተዋሉ መሰል የሌብነት ወንጀሎች በማጋለጥ እና ኃላፊነትን በንፁህነት በመወጣት ኢትዮጵያን መድረስ ከሚገባት የልእልና ደረጃ ላይ ማድረስ አንደሚገባም ተናግረዋል"

እኛም እንደ አንድ የቤተክርስቲያን ልጆች ትናንትም ዛሬም ነገም በእኛ ቤተክርስቲያን በኩል በራሱ በጠቅላይ ቤተክህነቱ የሚመራ ጠንካራ የኦዲት ክፍል መኖር አለበት የሚል ጠንካራ አቋም አለን። መንግስት ግን በቤተክርስቲያኒቱ ሀብትና ንብረት ላይ እጁን ማስገባት የለበትም።

ለበለጠ join
@ETHIOPIA_Hagerie

@Afe_Werk
204 viewsMule negn, 08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ