Get Mystery Box with random crypto!

🦋የህይወት ሳይኮሎጂ🦋

የቴሌግራም ቻናል አርማ adviceeeeee — 🦋የህይወት ሳይኮሎጂ🦋 የ
የቴሌግራም ቻናል አርማ adviceeeeee — 🦋የህይወት ሳይኮሎጂ🦋
የሰርጥ አድራሻ: @adviceeeeee
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.69K
የሰርጥ መግለጫ

* [ #የህይወት_ሳይኮሎጂ ቻናል ] *
✨ሰው የአመለካከቱ ውጤት ሲሆን ማንነቱም የአመለካከቱ ነፀብራቅ ነው።
➖የ ስኬት ንግግሮች
➖ዘፈኖች
➖የህይወት መርሆች
➖አስተማሪ ቪዲኦ
➖️ ተከታታይ ታሪኮች
➖ አስተማሪ ፁሁፎች
ሁሉንም ባአንድ ላይ እዚህ ያገኙታል ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት 👇 ላይ ያገኙታል
@wintagh

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-08 23:11:54 የባከነችነብስ #ክፍል\9 የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ ማታ ከጠጣሁት ወይን ጋር ስለቀላቀለብኝ ነገር እርቃኔን ስላነሳኝ ፎቶና ስለቀረፀኝ ቪዲዮ እያፌዘ ያወራልኛል። በጣም አፀያፊ ቃላቶችን እየተናገርኩና እርቃኔን እየደነስኩ የቀረፀኝን የቪዲዮ ምስል ሲያሳየኝ ከመደንገጤ የተነሳ ልቤ በሀይል ድዉ ድዉ እያለች በጉሮሮዬ ልትወጣ ምንም አልቀራትም ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ።…
1.2K viewswÎùtãùü, 20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 23:11:15 የባከነችነብስ

#ክፍል\9

የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ

ማታ ከጠጣሁት ወይን ጋር ስለቀላቀለብኝ ነገር እርቃኔን ስላነሳኝ ፎቶና ስለቀረፀኝ ቪዲዮ እያፌዘ ያወራልኛል። በጣም አፀያፊ ቃላቶችን እየተናገርኩና እርቃኔን እየደነስኩ የቀረፀኝን የቪዲዮ ምስል ሲያሳየኝ ከመደንገጤ የተነሳ ልቤ በሀይል ድዉ ድዉ እያለች በጉሮሮዬ ልትወጣ ምንም አልቀራትም ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ።
<<አ.ም.ኜ.ህ ነ.. ነበ.. ነ.በ.ር! እንደ ህፃን ልጅ ተንተባተብኩኝ!
<<ደሞ እናንተ ምናችሁ ይታመናል? ሴትን ማመን መጨረሻዉ ለፍትህ አልባ ህመም መዳረግ እንደሆነ ከእኔ በላይ ምስክር አይኖርም!>>
እጅግ በጣም የሚያፈቅራት ሴት ከድታዉ እንደሄደችና በእሷ ምክንያት ሴቶችን መበቀል እንደሚያስደስተዉ እየተመፃደቀ ሲናገር አዉሬ እንጂ የሰዉ ልጅ አልመስልሽ አለኝ! በፍፁም ያልጠበኩትን ያልገመትኩትን ማንነትን ነበር የተላበሰዉ ልክ በለሰለሰ ቆዳ እንደተሸፈነ መርዛማ እባብ!። በ ሶስት ቀናት ዉስጥ 50ሺ ብር እንድሰጠዉ ካልሆነ ግን ፎቶዉንና ቪዲዮዉን በማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ እንደሚበትነዉ እየዛተበኝ ነገረኝ
<<እባክህ...በሴት ልጅ...አምላክ!...ስለ እናትህ ብለህ... ስለወደድኩህና ስላመንኩህ እንዲ ልታረገኝ አይገባም እባክህ...>>
የዓይኖቼ መስኮቶች ተከፍተዉ እንባዬ ገላዬን እስከሚያርስ ድረስ ለመንኩት!
<<አንድ ሳምንት ሰጥቼሻለሁ በአንድ ሳምንት ዉስጥ ገንዘቡን ካላመጣሽ...>>
ንግግሩን ሳይጨርስ ከለቅሶዬ ጋር ትቶኝ ወጣ! ዓለም በምን አይነት ክፉና አስመሳይ ሰዎች እንደተሞላች ዛሬ ገና ገባኝ! ክህደትና ዉርደቴን ተከናንቤ ከነበርኩበት ክፍል ወጣሁ ማታ እራት ለመብላት የገባንበት ሆቴል ነበር። ለእየሩስ ደዉዬ ያለሁበትን ቦታ በምልክት አስረድቼ በፍጥነት እንድትመጣልኝ እያለቀስኩ ነገርኳት ከ 30 ደቂቃ በሗላ እየሩስና አባቷ ኮንትራት ታክሲ ይዘዉ ያለሁበት ቦታ ደረሱ! እየሩስ እየሮጠች መጥታ ተጠመጠመችብኝ
<<አይዞሽ የእኔ ቆንጆ ሁላችንም ከጎንሽ ነን! እኛ እንደዉም ማታ የእረፍቷን ዜና ሰምተሽ በድንጋጤ ከእየሩስ ጋር መለያየታችሁን ስትነግረን ማታዉኑ ጉዞ የጀመርሽ መስሎን ነበር!>> የእየሩስ አባት ነበር! ስለ ምን እንደሚያወራ አልገባኝም! እየሩስን አየሗት አይናን ከእኔ ለማሸሽ ስትሞክርና እንባ በአይኖቿ ግጥም ሲል አስተዋልኩ!
<<መቼም እግዚአብሔር የፈቀደዉ ነዉ የሚሆነዉ! በርታ ማለት ይኖርብሻል ገዜ ስለሌለን ለቀብር እንድንደርስ በፍጥነት ጉዞ መጀመር ይኖርብናል!>> አለኝ
<<የ.ም.ን ቀ.ብ.ር?>>...

...ከሆስፒታል አልጋ ላይ እራሴን አገኘሁት። እናቴ ላይ ጨክኖ አፈር ማልበሱ ክፉኛ ሰቀቀን ሆኖብኝ ነበር ነገር ግን ድካም፣ሀዘን፣ብስጭትና ረሀብ ተደማምረዉ እራሴን እንድስት ስላደረጉኝ እጅግ የምሳሳላት እናቴን እንደ ወጉ አልቅሼ መቅበር ተስኖኝ በቀብሯ ማግስት እራሴን ስቼ ለህክምና ከገባሁበት ሆስፒታል ዉስጥ ነቃሁ። መጀመሪያ ላይ የአባቴ መጥፋት የሄደበት የገባበት አለመታወቁ ክፉኛ ያስጨንቃት ነበር ምናልባት ሰዎች አደጋ አድርሰዉበት እንዳይሆን ብላም ትሰጋ ነበር እዉነታዉ ግን አባቴ በእድሜ እጅግ ከምታንሰዉ እንደዉም እንደሰዎች አባባል ከእኔ እኩያ ከምትሆን ሴት ፍቅር ይዞት ቤት ንብረቱን በትኖ ከእሷ ጋር መኮበለሉን ስትሰማ ድንጋጤ ከነበረባት ግፊት ጋር ተዳምሮ ለሞት ዳረጋት።አሁን በህይወት ለመቆየት ምን ምክንያት ይኖረኛል? ህይወት እራሷ በሀዘኔ ዳንኪራ ልትመታ!፤በለቅሶዬ ጭቃ አቡክታ ቤቷን ልትሰራ!፤የእኔን ዉጣ ዉረድ እንደ ኮሜዲ ፊልም ልትኮሞኩም ስቃይና ሀዘንን ለግሳ ለዚህች ጠማማ ዓለም ካስረከበችኝ በሗላ ጭላጭ ተስፋን እንደማትሰጠኝ ልቦናዬ ከተረዳ ሰነባብቷል። እየሩስ ከአጠገቤ ነበረች መንቃቴን ስትመለከት በፍጥነት ሄዳ ዶክተሯን ጠርታ መጣች
<<እንዴት ነሽ? ምን አየተሰማሽ ነዉ?>>
ተስፋ መቁረጥና የሞትን ፅዋ ለመጎንጨት መጓጓት! ነዉ የሚሰማኝ ብዬ ለዶክተሯ ብነግራት ምነኛ ደስ ባለኝ ነገር ግን ይህንን ለመረዳት እኔ የቆምኩበት ላይ ልትቆም እኔ የሚሰማኝ ሊሰማት እንደማይችል ልቦናዬ ስላወቀዉ
<<ደ.ህ.ና ነ.ኝ!>> አልኳት
በእጆቿ ግንባሬን ከነካካችና የሙቀት መጠኔን ከለካች በሗላ
<<አሁን ደህና ነሽ ነገር ግን ሰዉነትሽ ስለተጎዳ ፈሳሽ ነገሮች በብዛት መዉሰድ ይጠበቅብሻል የማዝልሽንም መድሀኒት በአግባቡ መዉሰድ ይኖርብሻል!>> አለችኝ! ከእየሩስ ጋር የታዘዘልኝን መድሀኒት ተቀብዬ ወደ ቤት አመራን። አክስቴ ባለቤቷና ከአዲስ አበባ አብረዉን የመጡት ሰዎች ሀዘንተኞቹን ምሳ ሲመግቡ ደረስን! አብዛኞቹ እኔን ሲመለከቱ በሀዘን ደረታቸዉን መምታት ጀመሩ እየሩስ በፍጥነት ወደ መኝታ ክፍሌ ይዛኝ ገባች... መኝታ ክፍሌ ዉስጥ ባማረ ፍሬም የተሰቀለዉን የአባቴን ፎቶግራፍ ስመለከት የንዴትና የበቀል ስሜት በደም ስሬ ዉስጥ ይሯሯጥ ጀመር...

Join us @adviceeeeee
1.0K viewswÎùtãùü, 20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 23:11:15 የባከነችነብስ

#ክፍል\8

የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ

...መሸትሸት ሲል ከእንቅልፌ ነቃሁ እየሩስ ከአጠገቤ ጋደም ብላለች። ስልኬ ላይ አምስት ሚስኮል አገኘሁ ሁለቱ የእናቴ ሲሆን የተቀረዉ አዲስ ቁጥር ነበር በቀጥታ ወደ እናቴ ደዉዬ ስለ አባቴ አዲስ ዜና ካለ ጠየኳት ምንም አዲስ ነገር እንደሌለ በሀዘን ተዉጣ ነገረችኝ እኔም እሷን ትቼ አዲስ አበባ ብዙ መቀመጥ እንደማልችል እንደዉም በዚህ ሁለት ቀን ዉስጥ ከእየሩስ ጋር ወደ ጅማ እንደምመለስ አሳምኛት ስልኩን ዘጋሁት።
<<...ምሳ እንኳን አልበላሽም አሁን ተነሺና እራት እንብላ>>
<<ይቅርብኝ አራበኝም! ...ይልቅ ነገን እዚህ አሳልፌ ከነገ ወዲያ መመለስ ይኖርብኛል አብረን እንሄዳለን?>>
እየሩስ ሀሳቤን አልተቃወመችኝም። ስልኬ ላይ ወዳገኘሁት አዲስ ቁጥር ደወልኩ አቤል ነበር ድምፁን ስስማ ልቤ ድንግጥ አለ! ልክ እንደተማረከ ወታደር ለምን የልቤን እንደምናዘዝለት ባላዉቅም አዲስ አበባ ከደረስኩ በሗላ የገጠመኝን ሁሉ ምንም ሳላስቀር ነገርኩት!
<<ከቻልሽ ነገ ላግኝሽ እኔ ጋር የረሳሽዉ እቃ አለ>> አለኝ!
ግራ ገባኝ እስከማስታዉሰዉ ድረስ እሱ ጋር የረሳሁት ምንም ነገር የለም ቢሆንም ነገ ከእየሩስ ጋር ትኬት ለመቁረጥ ወደ መስቀል አደባባይ እንደምንመጣና በዛዉ ላገኘዉ እንደምችል ነገርኩት የሚሰራበት ቦታ ቦሌ አካባቢ እንደሆነ ነግርኝ እሱ ያለበት ቦታ ለመገናኘት ተቀጣጥረን ስልኩ ተዘጋ። እየሩስ እራት እንድበላ ብታስጨንቀኝም ፍቃደኛ ልሆንላት ስላልቻልኩ እሷ ጋር ያለዉን ለእኔ እኔ ጋር ያለዉን ደግሞ ለእሷ እያጫወትኳት እንቅልፍ ወሰደን... እንደሌላዉ የሀምሌ ቀን ዝናብ ያስጨነቀዉ ሳይሆን ቀለል ያለ ብሩህ ጠዋት ነበር ከእየሩስ ጋር አርፍደን ተነሳን ጥሩ ቁርስ...የሚገርም ምሳ...ቤተሰባዊ መስተንግዶ ስለተደረገልኝ በትንሹም ቢሆን ሀዘኔን ቀለል አደረገዉ።
ወደ ጅማ የምንሄድበትን የጉዞ ትኬት አክስቴ ከምትደክሙ ብላ ሰዉ አስልካ አስቆረጠችልን። ሲኒማ ፊልም ልናይ ነዉ በሚል ሰበብ ከእየሩስ ጋር 11:30 ላይ ተያይዘን ወጣን! ለአቤል ደዉዬ እየመጣሁ እንደሆነ ስነግረዉ ያለበትን ትክክለኛ ቦታ አሳወቀኝ ስደርስ እንደምደዉል ነገርኩት...
እየሩስ<<ምናልባት ብቻሽን ሊያገኝሽ አስቦ ይሆናል እኔ እዛዉ አካባቢ ከአንዷ ጓደኛዬ ጋር ልቆይና ስትጨርሺ አብረን እንመለሳለን አይሻልም?>> አለችኝ!
ልቤን ፍርሀት... ፍርሀት እያለዉ እሺ አልኳት...
...አቤል የሚሰራበትን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሸጫና መጠገኛ የሆነዉን ሱቅ አስጎበኘኝ ሱቁ የታላቅ ወንድሙ እንደሆነ ነገር ግን ከጅማ ድረስ እየመጣ ለመቆጣጠር ስለማይመቸዉ እሱ በሀላፊነት እንደሚያስተዳድርለት ነገረኝ።
ሱቁ አነስ ያለ ነገር ግን በርካታና ጥራት ያላቸዉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለዓይን በሚማርክ ሁኔታ ተደርድረዉበታል የሱቁን ጉብኝት እንደጨረስን እራት እንድንበላ ጠየቀኝ ብዙ ማምሸት እንደማልችልና ነገ ተጓዥ ስለሆንኩ በጊዜ ገብቼ እረፍት ማድረግ እንዳለብኝ አስረዳሁት
<< ለተወሰነች ደቂቃ ብቻ! ተረጋግቼ ላወራሽ የምፈልገዉ ነገር ስላለ ነዉ?>>
ሰዉን ቶሎ ከሚያምኑት ወገን ባልመደብም ብቻ አቤል ምን አይነት አስማት እንዳለዉ አልገባኝም ልቃወመዉ አልቻልኩም። ከሱቁ ወጥተን እዛዉ ቦሌ አካባቢ ከሚገኝ ተለቅ ያለ ሆቴል ገባን! ለዓይን ያዝ ማድረግ ጀምሮ ስለነበር በተለያዩ አይነት ከለር ብልጭ ድርግም የሚሉት መብራቶች ለስለስ ብሎ ከሚንቆረቆረዉ የእንግሊዘኛ ሙዚቃ ጋር ተዳምረዉ ለሆቴሉ ልዩ ዉበት አጎናፅፈዉታል። እኔና አቤልን ለተመለከተን በፍቅር ረጅም ጊዜ ያሳለፉ ጥንዶች እንጂ በጣት የሚቆጠር የትዉዉቅ ቀናቶች ያለን አንመስልም። <<በእኔ ምርጫ>> ብሎ ከታዘዘዉ የበግ ጥብስ ላይ ደጋግሞ አጎረሰኝ ለሴት ልጅ ያለዉ አክብሮትና ጨዋታ አዋቂነት አቤልን ያለ ምንም ፍርሀት ግልፅ ሆኜ በነፃነት እንዳወራዉ እያደረጉኝ ነዉ! የመጠጥ ተጠቃሚ አለመሆኑን ነገር ግን ይህ ምሽት ያለ ወይን አይደምቅም ብሎ ወይን ታዘዘ! በሁለታችንም ብርጭቆ ልዩ ስሜትን በሚሰጥ እርጋታ ወይኑን ቀዳዉ
<<እንግዲህ እኔ ጋር የረሳሽዉ...>> ንግግሩን እንደጀመረ ስልኬ ጠራ እየሩስ ነበረች አቤልን ይቅርታ ጠይቄ ላናግራት ወደ መፀዳጃ ሄድኩ ከ30 ደቂቃ በሗላ እንደምጨርስ ነግሬያት ተመለስኩ
<<ለጥሩ ምሽታችንና እኔ ጋር ለረሳሽዉ ነገር ፅዋችንን እናንሳ!>> እሱ ጋር ምን ልረሳ እችላለሁ? ዉስጤ የበለጠ ለማወቅ ስለጓጓ ብርጭቆዉን አንስቼ ተጎነጨሁ አቤል ምን እንደሚያወራ ባይገባኝም የሆነ ነገር ያወራልኛል ምስሎች ብዥዥ...ብዥዥ... እያሉብኝና የእንቅልፍ ስሜት ሲጫጫነኝ ይታወቀኛል
...ጠዋት እራሴን ከማላዉቀዉ ክፍል አልጋ ዉስጥ አገኘሁት ፊት ለፊቴ ካለዉ ወንበር ላይ አቤል ሲጋራ እያጨሰ ነበር መንቃቴን ሲመለከት ከት ብሎ ሳቀብኝ
<<ወፏ ወደ ወጥመዷ ገብታለች!>> አለኝ የማየዉ የምሰማዉ ህልም እንጂ እዉነት አልመስልሽ አለኝ
<<የት ነኝ?>> አልኩትና
<<ሲኦል>>...

Join us @adviceeeeee
1.1K viewswÎùtãùü, 20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 20:14:36 SKY TRENDING CHANNELS
••••••
️DEEP THOUGHTS

60k| couple gallery

50k| Broken heart

16k|Free 10,000 Udemy Courses
14k|7000$ Paid Courses 4 FREE
11k|Free Udemy Courses
11k|Dark diary

••••••
9k|Manchester United
9k|ADULT COMICS
8k|DAILY MODDED APPS
6k|Broken hearts
6k|Mod_App_Full_Unlocked

••••••
5k|Psychology life
5k|Free 4000+ Udemy Courses
4k|ɪɴ ᴍʏ ғᴇᴇʟɪɴɢs
4k|SWEET POEMS
4k|In my late night thoughts
3k|UNLIMITED KNOWLEDGE
3k|Dark, funny and hilarious
3k|ʙʀᴏᴋᴇɴ_ꜰᴇᴇʟɪɴɢs_143
3k|𝙱𝚘𝚘𝚔𝚐𝚛𝚊𝚖
2k|nasty and dark humor
2k|Home of Art and more
2k|UHD wallpaper
2k|ᴍᴜsɪᴄ ᴠɪᴅᴇᴏs
2k|An awareness if the universe
1k|ᴍᴄᴇᴜɴɪᴠᴇʀꜱᴇ
1k|NETFLIX SERIES

ᴘsʏᴄʜᴏʟᴏɢʏ ᴡᴏʀʟᴅ
ᴅᴇᴇᴘ ᴛʜᴏᴜɢʜᴛˢ&ϙᴜᴏᴛᴇˢ

1hr on Top & 7hr in channel.

ADD YOUR CHANNEL
868 viewsㅤㅤㅤㅤ , 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 23:18:16
1.5K viewsall people racism, 20:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 23:45:25 ​​​​ የባከነችነብስ

#ክፍል\➏

የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ

... መነሻዉ ከጅማ ከተማ ሆኖ ከንጋቱ 11:30 የተጀመረዉ ጉዞ ከቀኑ 8:00 አካባቢ መድረሻዉን አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አድርጎ በሰላም ተጠናቀቀ። ከመኪናዉ እንደወረድኩ ለአክስቴ ልጅ ለእየሩስ ደወልኩላት መምጣቴ አስቀድሞ ስለተነገራት ኮንትራት ታክሲ ይዛ መስቀል አደባባይ አካባቢ እየጠበቀችኝ እንደሆነ ነገረችኝ። እኔ እንዲቸገር ባልፈልግም አቤል ግን የያዝኩትን ሻንጣ ተሸክሞ እየሩስ የቆመችበት ቦታ ድረስ አደረሰኝ። አቤልን ከእየሩስ ጋር አስተዋዉቄዉ እንዲደዉልልኝ የስልክ ቁጥሬን ከሰጠሁት በሗላ ቻዉ ብሎ መሰናበቱ ከበደኝ! በዝምታ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ትኩር ብዬ ስመለከተዉ ሁኔታዬ ከእኔ አልፎ እየሩስንም ስለገረማት
<< እዚሁ የማደር ሀሳብ አለሽ እንዴ?>> አለችኝ!
ከእንቅልፉ እንደተቀሰቀሰ ሰዉ ድንገት ከገባሁበት ዝምታ ብንን ብዬ ነቃሁ።
<<ስለ ሁለም ነገር አመሰግናለሁ እጅግ በጣም ደስ የሚል ጉዞ ነበር! መልካም ቀን ይሁንልህ!>>
<<አሜን መልካም ቀን ይሁንልን!>>
አቤል ያልገባኝን ስሜት አስታቅፎኝ እኔና እየሩስን ተሰናብቶን ሄደ! ከእየሩስ ጋር በቀጥታ ሳሪስ ወደሚገኝ መኖሪያ ቤታቸዉ እየሄድን ከአቤል ጋር እንዴት እንደተዋወቅንና በአንድ ቀን የተሰማኝን ግራ የሚያጋባ ስሜት አጫወትኳት። እየሩስ የእናቴ እህት ልጅ ብቻ ሳትሆን የእድሜ እኩያ ጓደኛዬ፤የልቤን ሚስጥር ተጋሪ እህቴም ጭምር ነች።
<<አንዳንዴ ብዙ ግምት ሰጥተን ከጠበቅነዉ ነገር ይልቅ ድንገት የምናገኘዉ ደስታን ይሰጠናል>> አለችኝ!
<<እንዴት?>>
<<ልክ እንደ ፈተና ዉጤትሽና እንደ አቤል ማለት ነዋ!>>
እየሩስ የተናገረችዉ ነገር ሙሉ በሙሉ እዉነት ቢሆንም ደህና የረሳሁት ሀዘን ስለቀሰቀሰችብኝ
<<ከዚህ በሗላ ስለ ትምህርት ዉጤቴ መበላሸት ማሰብ አልፈልግም የእሱን ሀዘን ሽሽት ነዉ እዚህ የመጣሁት !>>
<<እንጂ አንቺ ናፍቀሽኝ አይደለም እያልሽኝ ነዉ?>>
<<ከምልሽ በላይ ነዉ የናፈቅሽኝ የእኔ ዉድ እህት>> ብዬ እቅፍ አደረኳት።
በሰላም አዲስ አበባ መድረሴን ለማሳወቅ ወደ አባቴ ስልክ ብደዉልም ስልኩ አልሰራም አለኝ ምናልባት ኔትወርክ ይሆናል ብዬ ወደ እናቴ ደወልኩ ከተደጋጋሚ ጥሪ በሗላ ስልኳን አነሳች!
<<ሄሎ...እማ...አዲስ አበባ ደርሻለሁ...ከእየሩስ ጋር ወደ ቤት እየሄድን ነዉ!...ሄሎ..>>
<<...እሺ!...>> የእናቴ ድምፅ በለቅሶ የታጀበ ነበር!
<<እማ...ምንድነዉ...የተፈጠረ ነገር አለ?>>
<<ሄዷል!>> አለችኝ!
<<ማነዉ የሄደዉ?>>
<<አ.ባ.ት.ሽ ... ላይመለስ... ተሰናብቶን...ሄዷል!>>
ስልኬ ከእጄ ላይ ሸርተት ብሎ ወደቀ...
​​​​ የባከነችነብስ

#ክፍል\➐

የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ

... እዉነትም ሀዘን ከእኔ ፍቅር ይዞታል! አልያም ደግሞ በእኔ ይቀናብኛል ማለት ነዉ! ትንሽ ፈገግ ስል ደስታዬን የሚያጠፋ ሳቄን የሚገድል ችግር መፍጠሩን ተያይዞታል። አባቴ <<ሰላም ሁኑ>> የሚል መልዕክት በቁራጭ ወረቀት ላይ አስፍሮ የት እንደሄደ አለመታወቁን እናቴ ነገረችኝ! ያለችበት ሁኔታ ከባድ ሊሆን ስለሚችል ዛሬን አድሬ ነገ እንደምመጣ ብነግራትም አሷ ግን መምጣቴን አጥብቃ ስለተቃወመች የተወሰኑ ቀናትን አዲስ አበባ ለመቆየት ወሰንኩ።
አድካሚ ህይወት...አድካሚ መንገድ...አድካሚ ቀን!... የእየሩስ ክፍል ገብቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ!
<<ምናልባት በስራ ምክንያት የሄደበት ጉዳይ ሊያቆየዉ ስለሚችል ሊያስጨንቃችሁ ስላልፈለገ ይሆናል መልዕክት የተወላችሁ!>>አየሩስ ነበረች!
መልስ ልሰጣት አልቻልኩም! ምን አይነት ምላሽ ልሰጣትስ እችላለሁ? በወቅቱ አልነበርኩ ሰዉ ስላልነበረበት ሁኔታ እንዴት በእርግጠኝነት መናገር ይቻለዋል?
<<ደ.ክ.ሞ.ኛ.ል! በህይወቴ የሚፈጠሩ ተደጋጋሚ ችግሮች አድክመዉኛል!>> አልኳት! እንባዬ ያለ ከልካይ ይወርድ ስለነበር ሁኔታዬ እየሩስን አሳዘናት የተወሰነ እረፍት እንዳደርግ ከአልጋ ዉስጥ አስገብታኝ
<<አንድ ሁለት ቀናትን እዚህ እናሳልፍና ወደ ጅማ አብረን እንሄዳለን! አሁን ግን ተረጋግተሽ እረፍት ማድረግ ይኖርብሻል!>> ብላ ተሰናብታኝ ወጣች!
እኔ ቀጥ ብዬ መቆም ስፈልግ ህይወት ታንገዳግደኛለች! ይነጋል ሰዉም አብሮ ከንጋቱ ጋር ይነቃል፤ይመሻል ሰዉም አብሮ ከምሽቱ ጋር ይተኛል!... ህይወት በድግግሞሿ ዉስጥ የሰዉን ልጅ አቅፋ ትሽከረከራለች... የሰዉ ልጅም በህይወት አዙሪት ዉስጥ ይዞራል! ድካም...ለቅሶ...ሀዘን...ተደራርበዉ ለእንቅፍ አሳልፈዉ ሰጡኝ... ሽልብ አደረገኝ...

ይቀጥላል...
joun us @adviceeeeee
◉◉◉◉◎◎ ●●◉◉◉◉
Join & share

@wintay​​​​
1.4K viewswÎùtãùü, edited  20:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ