Get Mystery Box with random crypto!

የባከነችነብስ #ክፍል\9 የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ ማታ | 🦋የህይወት ሳይኮሎጂ🦋

የባከነችነብስ

#ክፍል\9

የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ

ማታ ከጠጣሁት ወይን ጋር ስለቀላቀለብኝ ነገር እርቃኔን ስላነሳኝ ፎቶና ስለቀረፀኝ ቪዲዮ እያፌዘ ያወራልኛል። በጣም አፀያፊ ቃላቶችን እየተናገርኩና እርቃኔን እየደነስኩ የቀረፀኝን የቪዲዮ ምስል ሲያሳየኝ ከመደንገጤ የተነሳ ልቤ በሀይል ድዉ ድዉ እያለች በጉሮሮዬ ልትወጣ ምንም አልቀራትም ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ።
<<አ.ም.ኜ.ህ ነ.. ነበ.. ነ.በ.ር! እንደ ህፃን ልጅ ተንተባተብኩኝ!
<<ደሞ እናንተ ምናችሁ ይታመናል? ሴትን ማመን መጨረሻዉ ለፍትህ አልባ ህመም መዳረግ እንደሆነ ከእኔ በላይ ምስክር አይኖርም!>>
እጅግ በጣም የሚያፈቅራት ሴት ከድታዉ እንደሄደችና በእሷ ምክንያት ሴቶችን መበቀል እንደሚያስደስተዉ እየተመፃደቀ ሲናገር አዉሬ እንጂ የሰዉ ልጅ አልመስልሽ አለኝ! በፍፁም ያልጠበኩትን ያልገመትኩትን ማንነትን ነበር የተላበሰዉ ልክ በለሰለሰ ቆዳ እንደተሸፈነ መርዛማ እባብ!። በ ሶስት ቀናት ዉስጥ 50ሺ ብር እንድሰጠዉ ካልሆነ ግን ፎቶዉንና ቪዲዮዉን በማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ እንደሚበትነዉ እየዛተበኝ ነገረኝ
<<እባክህ...በሴት ልጅ...አምላክ!...ስለ እናትህ ብለህ... ስለወደድኩህና ስላመንኩህ እንዲ ልታረገኝ አይገባም እባክህ...>>
የዓይኖቼ መስኮቶች ተከፍተዉ እንባዬ ገላዬን እስከሚያርስ ድረስ ለመንኩት!
<<አንድ ሳምንት ሰጥቼሻለሁ በአንድ ሳምንት ዉስጥ ገንዘቡን ካላመጣሽ...>>
ንግግሩን ሳይጨርስ ከለቅሶዬ ጋር ትቶኝ ወጣ! ዓለም በምን አይነት ክፉና አስመሳይ ሰዎች እንደተሞላች ዛሬ ገና ገባኝ! ክህደትና ዉርደቴን ተከናንቤ ከነበርኩበት ክፍል ወጣሁ ማታ እራት ለመብላት የገባንበት ሆቴል ነበር። ለእየሩስ ደዉዬ ያለሁበትን ቦታ በምልክት አስረድቼ በፍጥነት እንድትመጣልኝ እያለቀስኩ ነገርኳት ከ 30 ደቂቃ በሗላ እየሩስና አባቷ ኮንትራት ታክሲ ይዘዉ ያለሁበት ቦታ ደረሱ! እየሩስ እየሮጠች መጥታ ተጠመጠመችብኝ
<<አይዞሽ የእኔ ቆንጆ ሁላችንም ከጎንሽ ነን! እኛ እንደዉም ማታ የእረፍቷን ዜና ሰምተሽ በድንጋጤ ከእየሩስ ጋር መለያየታችሁን ስትነግረን ማታዉኑ ጉዞ የጀመርሽ መስሎን ነበር!>> የእየሩስ አባት ነበር! ስለ ምን እንደሚያወራ አልገባኝም! እየሩስን አየሗት አይናን ከእኔ ለማሸሽ ስትሞክርና እንባ በአይኖቿ ግጥም ሲል አስተዋልኩ!
<<መቼም እግዚአብሔር የፈቀደዉ ነዉ የሚሆነዉ! በርታ ማለት ይኖርብሻል ገዜ ስለሌለን ለቀብር እንድንደርስ በፍጥነት ጉዞ መጀመር ይኖርብናል!>> አለኝ
<<የ.ም.ን ቀ.ብ.ር?>>...

...ከሆስፒታል አልጋ ላይ እራሴን አገኘሁት። እናቴ ላይ ጨክኖ አፈር ማልበሱ ክፉኛ ሰቀቀን ሆኖብኝ ነበር ነገር ግን ድካም፣ሀዘን፣ብስጭትና ረሀብ ተደማምረዉ እራሴን እንድስት ስላደረጉኝ እጅግ የምሳሳላት እናቴን እንደ ወጉ አልቅሼ መቅበር ተስኖኝ በቀብሯ ማግስት እራሴን ስቼ ለህክምና ከገባሁበት ሆስፒታል ዉስጥ ነቃሁ። መጀመሪያ ላይ የአባቴ መጥፋት የሄደበት የገባበት አለመታወቁ ክፉኛ ያስጨንቃት ነበር ምናልባት ሰዎች አደጋ አድርሰዉበት እንዳይሆን ብላም ትሰጋ ነበር እዉነታዉ ግን አባቴ በእድሜ እጅግ ከምታንሰዉ እንደዉም እንደሰዎች አባባል ከእኔ እኩያ ከምትሆን ሴት ፍቅር ይዞት ቤት ንብረቱን በትኖ ከእሷ ጋር መኮበለሉን ስትሰማ ድንጋጤ ከነበረባት ግፊት ጋር ተዳምሮ ለሞት ዳረጋት።አሁን በህይወት ለመቆየት ምን ምክንያት ይኖረኛል? ህይወት እራሷ በሀዘኔ ዳንኪራ ልትመታ!፤በለቅሶዬ ጭቃ አቡክታ ቤቷን ልትሰራ!፤የእኔን ዉጣ ዉረድ እንደ ኮሜዲ ፊልም ልትኮሞኩም ስቃይና ሀዘንን ለግሳ ለዚህች ጠማማ ዓለም ካስረከበችኝ በሗላ ጭላጭ ተስፋን እንደማትሰጠኝ ልቦናዬ ከተረዳ ሰነባብቷል። እየሩስ ከአጠገቤ ነበረች መንቃቴን ስትመለከት በፍጥነት ሄዳ ዶክተሯን ጠርታ መጣች
<<እንዴት ነሽ? ምን አየተሰማሽ ነዉ?>>
ተስፋ መቁረጥና የሞትን ፅዋ ለመጎንጨት መጓጓት! ነዉ የሚሰማኝ ብዬ ለዶክተሯ ብነግራት ምነኛ ደስ ባለኝ ነገር ግን ይህንን ለመረዳት እኔ የቆምኩበት ላይ ልትቆም እኔ የሚሰማኝ ሊሰማት እንደማይችል ልቦናዬ ስላወቀዉ
<<ደ.ህ.ና ነ.ኝ!>> አልኳት
በእጆቿ ግንባሬን ከነካካችና የሙቀት መጠኔን ከለካች በሗላ
<<አሁን ደህና ነሽ ነገር ግን ሰዉነትሽ ስለተጎዳ ፈሳሽ ነገሮች በብዛት መዉሰድ ይጠበቅብሻል የማዝልሽንም መድሀኒት በአግባቡ መዉሰድ ይኖርብሻል!>> አለችኝ! ከእየሩስ ጋር የታዘዘልኝን መድሀኒት ተቀብዬ ወደ ቤት አመራን። አክስቴ ባለቤቷና ከአዲስ አበባ አብረዉን የመጡት ሰዎች ሀዘንተኞቹን ምሳ ሲመግቡ ደረስን! አብዛኞቹ እኔን ሲመለከቱ በሀዘን ደረታቸዉን መምታት ጀመሩ እየሩስ በፍጥነት ወደ መኝታ ክፍሌ ይዛኝ ገባች... መኝታ ክፍሌ ዉስጥ ባማረ ፍሬም የተሰቀለዉን የአባቴን ፎቶግራፍ ስመለከት የንዴትና የበቀል ስሜት በደም ስሬ ዉስጥ ይሯሯጥ ጀመር...

Join us @adviceeeeee