Get Mystery Box with random crypto!

ደህና አደራችሁ? ደመና ባይኖር፣ ሰረገላ ባይኖር፣ መንኮራኩር ባይኖር .....መሳፈሪያም | Adoni Gospel channel

ደህና አደራችሁ?


ደመና ባይኖር፣ ሰረገላ ባይኖር፣ መንኮራኩር ባይኖር .....መሳፈሪያም መጓጓዣም ሁሉ አንዳች ባይኖር በሁሉም ቦታ ፈጥኖ የሚደርስ አንድ አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ወደ ህይወታችሁ ሲመጣ አይዘገይም የሚቀድመውም የለም።

ለእግዚአብሔር ክረምት ገባ ወንዙን እንዴት ተሻግሮት ይመጣል አይባልም ወንዙን አስፓልት አድርጎ ጠቅጥቆት ይመጣል። መከራዬ በረታ እንዳይፈታው የቋጠሮው ውል ጠፍቷል አይባልም በእርሱ ፊት ትልቅ ችግር ትልቅ ፈተና የለም። ችግሬ እንኳን በሰው በአምላኬም አይፈታም አይባልም የኛ ችግር ሁሉ ከእግሩ በታች ነው። እግዚአብሔር ትልቅ ነው።

የትኛውም ቦታ መድረስ የሚችል የእግዚአብሔር እጅ ብቻ ነው። ከሲዖል የጠለቀ የለም እዛም ውስጥ ገብቶ የሚያወጣን ታዳጊ እጅ የእግዚአብሔር ነው። እጁ ያስጨነቀንን የሚያሳድድ፣ ሞትን የሚገድብ፣ ህይወትን የሚያቀርብ ረድዔታችን ነው። የደስታ ቀን ይሁንላችሁ።

አዶኒ

ነሐሴ 26/2014 ዓ.ም

@adonigospel
@adonigospel