Get Mystery Box with random crypto!

ያልፋል     የዛሬው መራብህ ያልፋል፤ የዛሬው መቸገርህ ያልፋል፤ የዛሬ ለቅሶህ ያልፋል፤የዛሬው | Adoni Gospel channel

ያልፋል


    የዛሬው መራብህ ያልፋል፤ የዛሬው መቸገርህ ያልፋል፤ የዛሬ ለቅሶህ ያልፋል፤የዛሬው ተስፋ የመቁረጥ ስሜትህ ያልፋል፤ የዛሬ መድከምህ ዝለህ መሰልቸትህ ያልፋል፤ ጤናህ ተናግቶ መሰቃየትህ ያልፋል፤ በወዳጅ መከዳትህ ያልፋል፤ ጓደኛ ማጣት ያልፋል፤ ግራ ያጋባህ የሀገርህ ሁኔታ ያልፋል፤ ታስረህም ቢሆን ይሄም ያልፋል።

                    ይሄም ያልፋል

ዛሬ ሞልቶህ ቢሆን መልካም ነው ግን ያልፋል፤ የጣመ እየበላህ ያማረ እየጎረስክ ይሆናል ይህም መልካም ነው ግን ያልፋል፤ ካዝና ሙሉ ሀብት ቢተረፈረፍልህ ሳትቸገር የፈለከውን ታደርግ ይሆናል ይህም ግን ያልፋል።

    ወዳጆቼ በዚህ ዓለም ላይ አለኝ ብላችሁ የሚያኮራ አንድም ነገር የለም፤ አጣሁም ብላችሁ ሕይወትን ከንቱ የሚያደርግባችሁም ምንም ነገር የለም። ማጣትም ማግኘትም ያልፋል አሳላፊው እግዚአብሔር በዙፋኑ ስላለ ያልፋል። አንተ ቤት ገንብተህ እፎይ ብለህ፣ ህንፃ አቁመህ እፎይ ብለህ ይሆናል። ህንፃውም ምድሪቱም በታላቅ ትኩሳት እንደወረቀት ተጠቅልለው ያልፋሉ። የማያልፈው ልዑል አምላክህ እግዚአብሔር ነው። ከሞትም በኃላ ላለው ሕይወትህ ሊያልፍህ የማይገባው ይህ ጌታ ብቻ ነው።

  እዚህ ምድር ላይ ላያልፍ የመጣ ምንም ነገር የለም!

           እግዚአብሔር ከፊታችሁ እንደ ጋሬጣ የተገተረባችሁን ነገር ሁሉ ያሳልፍላችሁ። ቤታችሁ የገባ ሀዘን ቢኖር ይለፍላችሁ። በመለኮታዊ ክንዱ ይለፍ የምትሉትን ነገር ሁሉ ያሳልፍላችሁ።

                     አዶኒ

በድጋሚ የተለጠፈ ሚያዝያ 22/2014 ዓ.ም

Join
             @adonigospel
             @adonigospel