Get Mystery Box with random crypto!

አይገርምም!! የተወለድነው በሌሎች ሰዎች እርዳታ ነው። ስማችንን የተቀበልነው ሌሎች ሰዎች | የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች

አይገርምም!!

የተወለድነው በሌሎች ሰዎች እርዳታ ነው።

ስማችንን የተቀበልነው ሌሎች ሰዎች ባወጡልን መሰረት ነው።

የገቢ ምንጫችን የሚመጣው ከሌሎች ሰዎች ነው።

«ክብርና እውቅና የሚሰጡን ሌሎች ሰዎች ናቸው።

ገላችንን ለመጀመሪያ ጊዜ ያጠቡን ሌሎች ሰዎች ናቸው።ለመጨረሻ ጊዜ የሚያጥቡንም ሌሎች ሰዎች ናቸው።

ከዚህ አለም ስንሰናበት ቤታችንና ንብረታችን በሌሎች ሰዎች ይወሰዳል።

እጃችንን ይዘው በመደገፍ መራመድ ያስለመዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው በመጨረሻም እጃችንን ይዘው በመደገፍ የሚያራምዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው።

በመወለዳችን ምክንያት በደስታ የደገሱ የበሉት ሌሎች ሰዎች፤ ሰንሞትም በኃዘን የሚደግሱና የቀብር ስርአታችን የሚከናወነው በሌሎች ሰዎች ነው።

ይህ ሁሉ እውነታ እያለ "ነኝ "እና "አልኝ" በምንለው ነገር የምንመካበት ጉዳይ አይገባኝም። እስቲ ያወሰሰብናትን ሕይወትን
ቀለል እናድርጋትና ለመከባበርና ለመዋደድ ቅድሚያን በመስጠት እንኑር!!
https://t.me/Adnan567mh