Get Mystery Box with random crypto!

ከ'ናቴ መሀፀን፣አባብለው አሶጡኝ፡ ማርያም ማርያም፣ሲሉ መጨቀን አቅጦኝ፡ ባይሆንማ ኖሮ ፣መች እሺ | የግጥም ጅረት ፦ከአድናቆት✍

ከ'ናቴ መሀፀን፣አባብለው አሶጡኝ፡
ማርያም ማርያም፣ሲሉ መጨቀን አቅጦኝ፡
ባይሆንማ ኖሮ ፣መች እሺ ልላቸው፡
በስምሽ መጡበኝ፣ተወለድኩላቸው፡፡
በማህፀን ሳለው፣የሰማሁት ስምሽ፡
በልቤ ታትሟል፣ድንግል መሀተም ነሽ፡፡
ሁሌ ጠራሻለው፣ካ'ፌ አትጠፊም፡
አማላጇ እናቴ፣ቅድስት ድንግል ማርያም፡፡

(አድናቆት ክፍሌ የብርቱካን)
https://youtube.com/shorts/M1G1svY9tj4?feature=share