Get Mystery Box with random crypto!

የኦሮሚያ ክልል ለሚያስገነባው አዲስ ቤተ-መንግስት ማሰሪያ ከወር ደመወዛችን ላይ ተቆርጦብናል ሲሉ | አዲስ መረጃ

የኦሮሚያ ክልል ለሚያስገነባው አዲስ ቤተ-መንግስት ማሰሪያ ከወር ደመወዛችን ላይ ተቆርጦብናል ሲሉ በሶማሊያ ሰላም ማስከበር የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ቅሬታ አቀረቡ!

በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) ስር ሆነው በሰላም ማስከበሩ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን የሰራዊት አባላት ከሚከፍላቸው ወርሃዊ ደመወዝ ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚያስገነባው ቤተ-መንግስት ማሰሪያ የሚሆን ኢትዮጵያውያን ወታደሮችን በወከሉ አመራሮች በኩል እንደተቆረጠባቸው ገለፁ።

በሶማሊያ ሰላም ማስከበር የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ወታደሮችን ጨምሮ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት በቦረና ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ በሚል እያንዳንዳቸው ከደመወዛቸው ላይ 25% እንደተቆረጠባቸው ይታወቃል።

በዚህም ከተቆረጠብን 25% ገንዘብ ላይ በቦረና ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ብቻ ሳይሆን በአማራ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች ላይ ተጠልለው ለሚገኙ የእለት ደራሽ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖችም ይሰጥልን የሚል ጥያቄ ያቀረቡ የሰራዊቱ አባላት ታፍነው የተሰዱ ሲሆን የደረሱበት አለመታወቁንም የአማራ ድምፅ ከወራት በፊት የአይን እማኞችን ጠቅሶ መዘገቡ አይዘነጋም።

በአሁን ሰዓት በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) ስር ሆነው በሶማሊያ ሰላም ማስከበር የተሰማሩ ከሰባት ሺ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ይገኛሉ የተባለ ሲሆን ከባለፈው ወር ጀምሮ ከወርሀዊ ደመወዛቸው ላይ እየተቆረጠባቸው መሆኑን ነው የገለፁት።

የሰራዊት አባላቱ፡ "ግዳጁን ስንጨርስ ከሚከፈለን ብር ተጨማሪ በየወሩ ለኪስ 38 .33 $ እና ለሻይ ቡና ተብሎ ደግሞ 6.90 $  በድምሩ 45.23  ዶላር አትሚስ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ይከፈለን ነበር ነገር ግን አሁን ላይ ለኪስ ተብሎ ከሚሰጠን ገንዘብ ላይ 22 $ ለሻይ ቡና ተብሎ ከሚሰጠን ላይ ደግሞ 4.7$ በድምሩ 26.70 $ ተቆርጦብናል" ለቤተመንግስቱ ማሰሪያ ተቆርጦብናል ሲሉ ገልፀዋል።