Get Mystery Box with random crypto!

ከ9 ሺሕ በላይ የሽጉጥ ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ ተያዘ!! የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሔራዊ መረ | Adise Mereja

ከ9 ሺሕ በላይ የሽጉጥ ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ ተያዘ!!

የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በጋራ በመቀናጀት ባደረጉት ክትትል ከ9 ሺሕ በላይ የሽጉጥ ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ መያዛቸውን አስታወቁ፡፡

የጦር መሳሪያ ዝውውሩን ለመቆጣጠር እየተሰራ ያለው ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

መነሻውን ባሕርዳር ከተማ ያደረገ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-98555 አ/አ ኤፍ.ኤስ.አር ተሽከርካሪ ላይ ከጫት ጋር በማድረግ በማዳበሪያ ተጭኖ ወደ አዲስ አበባ የገባ ጥይት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አጂፕ ቶታል አካባቢ ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት እጅ ከፍንጅ እንደተያዘ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ጥይቱን ሲያዘዋውሩ የተገኙ አራት ተጠርጣሪዎች እና ለህገ-ወጥ ተግባር የተገለገሉበት አንድ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው መቀጠሉም ተገልጿል፡፡