Get Mystery Box with random crypto!

Adise Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ adise_mereja — Adise Mereja A
የቴሌግራም ቻናል አርማ adise_mereja — Adise Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @adise_mereja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.82K
የሰርጥ መግለጫ

📝አዲስ መረጃ 🇪🇹 ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ🇪🇹
ኢትዮጵያ ብዙ ይገባታል!
የመረጃ ፍጥነት መገለጫችን
The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
ለሃሳብ አስተያየታችሁ እንዲሁም ለዜና
ለማንኛውም አስተያየት
📩 @adise_mereja_bot
❌Leave ማረግ አይፈቅድም❌

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-16 00:22:37
150 views𝙩𝙜𝙤𝙙, edited  21:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 18:05:27
ከ9 ሺሕ በላይ የሽጉጥ ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ ተያዘ!!

የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በጋራ በመቀናጀት ባደረጉት ክትትል ከ9 ሺሕ በላይ የሽጉጥ ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ መያዛቸውን አስታወቁ፡፡

የጦር መሳሪያ ዝውውሩን ለመቆጣጠር እየተሰራ ያለው ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

መነሻውን ባሕርዳር ከተማ ያደረገ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-98555 አ/አ ኤፍ.ኤስ.አር ተሽከርካሪ ላይ ከጫት ጋር በማድረግ በማዳበሪያ ተጭኖ ወደ አዲስ አበባ የገባ ጥይት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አጂፕ ቶታል አካባቢ ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት እጅ ከፍንጅ እንደተያዘ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ጥይቱን ሲያዘዋውሩ የተገኙ አራት ተጠርጣሪዎች እና ለህገ-ወጥ ተግባር የተገለገሉበት አንድ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው መቀጠሉም ተገልጿል፡፡
802 views𝙩𝙜𝙤𝙙, edited  15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 15:38:40 በመጪው የትምህርት ዘመን ከመመሪያው ውጭ ወርሃዊ የክፍያ ጭማሪ ማድረግ በሕግ ያስጠይቃል

ትምህርት ቤቶች በ2015 የትምህርት ዘመን ከመመሪያው ውጭ ወርሃዊ የክፍያ ጭማሪ ማድረግና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያ እንዳይጠይቁ የአዲስ አበባ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳሰበ።

የባለሥልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፍቅርተ አበራ እንደገለጹት ከመመሪያው ውጭ የክፍያ ጭማሪ በሚያደርጉ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ ይወሰዳል።

መመሪያው በ2014 ዓ.ም ጭማሪ ያደረጉ የግል ትምህርት ቤቶች በ2015 የትምህርት ዘመን ምንም አይነት ጭማሪ እዳያደርጉ ያዛል።

ነገር ግን መመሪያውን በመጣስ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች አስቀድመው በደብዳቤና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ጭማሪ እንደሚያደርጉ ለወላጆች መልዕክት እያስተላለፉ መሆኑ ተደርሶበታል ብለዋል።

መመሪያውን በሚጥሱ ትምህርት ቤቶች ላይ ፈቃድ የመሰረዝና በሕግ የማስጠየቅ እርምጃዎች እንደሚወስድ ከወዲሁ አሳስበዋል።
954 views𝙩𝙜𝙤𝙙, edited  12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 13:36:26
1.0K views𝙩𝙜𝙤𝙙, edited  10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 12:49:52
#የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች #ፍትህሚኒስቴር ፍትህ ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ ምክር ቤት በፃፈው ደብዳቤ ላይ (ከዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ያለመከሰስ መብት መነሳት ጋር የተያያዘ) ፦ " ... ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ምሩፅ ለከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ቀርበው በሰጡት መግላጫ እንዲሁም በእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ላይ ለህዝብ በይፋ በሰጡት ማብራሪያ ቢሮው በአዋጅ በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት ቴክኖሎጂውን አልምቶ የጨረሰ በመሆኑ…
911 views𝙩𝙜𝙤𝙙, edited  09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 12:49:52 #የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች #ፍትህሚኒስቴር

ፍትህ ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ ምክር ቤት በፃፈው ደብዳቤ ላይ (ከዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ያለመከሰስ መብት መነሳት ጋር የተያያዘ) ፦

" ... ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ምሩፅ ለከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ቀርበው በሰጡት መግላጫ እንዲሁም በእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ላይ ለህዝብ በይፋ በሰጡት ማብራሪያ ቢሮው በአዋጅ በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት ቴክኖሎጂውን አልምቶ የጨረሰ በመሆኑ ቴክኖሎጂው ከሰው ንክኪ ነፃ በመሆኑና በኢንሳ በኩል ተፈትሾ ማረጋገጫ ያገኘ እንዲሁም ለዕጣው አወጣጥ ከባንክ የተላከው ዳታ በአግባቡ የተጫነ መሆኑ ማረጋገጫ ሰጥተው ነበር።

መስተዳደሩም የኃላፊውን ማረጋገጫ በመቀበል እና በማመን ዕጣው ሐምሌ 1 በህዝብ ፊት እንዲወጣ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ከተሰጠው ማረጋገጫ በተቃራኒ ከፍተኛ ከፍተኛ የሆነ የዳታ ማጭበርበር ተግባር የተፈፀመ መሆኑ አመላካች መረጃ በማግኘት ኦዲት እንዲደረግ አቅጣጫ ተሰጥቶ እንዲፈተሽ ተደርጓል።

በዚህ መሰረት ከኢንሳ ፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከኢኖቬሽን ሚኒስቴር በተዋቀረው የባለሞያ ቡድን በተደረገው ማጣራት ፦

1ኛ. ሲስተሙ አዲስ እና የገባው ዳታ በማንም ያልታየ ለመሆኑ ለከተማው አመራር ጭምር በኃላፊው ማረጋገጫ የተሰጠ ቢሆንም ዕጣው ከመውጣቱ በፊት ወደ ኮምፒዩተሩ የገባውን ዳታ ለአምስት ጊዜ የተመለከቱ መሆኑ፤

2ኛ. ለዕጣ ብቁ ናቸው ተብሎ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተላከው 79 ሺህ ተመዝጋቢዎች በላይ ለዕጣው ብቁ ያልሆኑ 73 ሺህ ሰዎችን በድብቅ ወደ ኮምፒዩተሩ በመጫን የተጠቃሚዎችን ቁጥር ወደ 172 ሺህ እንዲያድግ ያደረጉ መሆኑ፤

3ኛ. ኃላፊው ከቤቶች ልማት የተላከውን የተወዳዳሪዎችን መረጃ ለሚያስገባ ባለሞያ ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ እንዲሰራ ማድረግ ሲገባቸው በቀጥታ ለአልሚው በመስጠት የዳታ ማጭበርበሩ እንዲፈፀም ያስደረጉ መሆኑ፤

4ኛ. ሲስተሙ የማልማት ተግባሩ አለም አቀፍ ስታንዳርዱን ያልጠበቀና የሚና መደበላለቅ የታየበት በተለይም ሶስቱን አካላት አልሚውን፣ የተጠቃሚውን እና አረጋጋጩን አካላት የሚና ክፍፍል የሌለበት እና ሁሉም በአንድ ሰው ማለትም በአልሚው ብቻ የተሰራ በመሆኑ አሁን ለተከሰተው ማጭበርበር በር እንዲከፍት ያደረገ መሆኑ፤

5ኛ. ዳታው የተጫነበት ኮምፒዩተር አዲስ እና የዳታ አጠቃቀሙን ከእጅ ንክኪ ነፃ እንዲሆን የሚፈልግ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ኮምፒዩተሩ ለስራው የማይፈለግ ባዕድ ሶፍትዌር ጭምር የተጫነበት ከመሆኑ በላይ የዕጣ አወጣጥ ሂደቱን በኦንላይን ጭምር እንዲከታተሉ የሚያስችል የነበረ መሆኑ ፤

6ኛ. ስለደህንነቱ ምንም አይነት ፍተሻ ባልተደረገበት ቴክኖሎጂ በኢንሳ ተፈትሾ ችግር እንደሌለበት ማረጋገጫ የተሰጠበት ነው በሚል የተሳሳተ መረጃ በማቅረብ የከተማ አስታዳደር አመራሩን በማሳሳት ዕጣ እንዲወጣ ያስደረጉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

በአጠቃላይ ዕጣውን ለማውጣት ጥቅም ላይ የዋለው ቴክኖሎጂ ወይም ሲስተም የአሰራር ስርዓቱን ያልተከተለ፣ አግባብ ባለው ተቋም ያልታየና ምንም አይነት የደህንነት ማረጋገጫ ያልተሰጠበት፣ ለማጭበርበር የሚረዳ ባዕድ ሶፍትዌር የተጫነበት ፣ ለዕጣው ብቁ ናቸው ተብሎ ከሚመለከተው አካል ተረጋግጦ ከተላከው ዳታ ውጭ ሌላ ዳታ ማስገባት መረጃ መጨመር፣ ማጥፋት እንዲሁም ማስተካከል የሚያስችል እድል ለአልሚው በድብቅ የሚሰጥ ስለመሆኑ ማረጋገጥ ተችሏል።

ድርጊቱ በቢሮው ኃላፊ እና በስሩ የተሳተፉት ሌሎች ግለሰቦች የተፈፀመ መሆኑ ተረጋግጦ አብዛኛዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የወንጀል ምርመራ እየተደረገ ይገኛል። "
884 views𝙩𝙜𝙤𝙙, edited  09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 12:49:52
778 views𝙩𝙜𝙤𝙙, edited  09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 12:49:51
772 views𝙩𝙜𝙤𝙙, edited  09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 12:49:51
891 views𝙩𝙜𝙤𝙙, edited  09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 18:43:25
1.4K views𝙩𝙜𝙤𝙙, edited  15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ