Get Mystery Box with random crypto!

የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከነገ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት እና ከረጅም ጊዜ በኋላ | 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿

የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከነገ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት እና ከረጅም ጊዜ በኋላ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው የስድስተኛ ክፍል ፈተና፤ ከሰኔ 28 እስከ 30/2015 ዓ.ም ይከናወናል።

በአዲስ አበባ ከተማ ከ150 ሺ በላይ ተማሪዎች የስድስተኛ እና የስምንተኛ ክፍል ፈተናዎችን ይወስዳሉ።

በአዲስ አበባ 75,100 ተማሪዎች የስምንተኛ ክፍል ፈተና ለመውሰድ መመዝገባቸውን የከተማዋ ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅት ዳይሬክተር ዲናኦል ጫላ ለኢፕድ ተናግረዋል።

እንዲሁም 75,090 ተማሪዎች የስድስተኛ ክፍል ፈተና እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

ተፈታኞች እርሳስ፣ ላጲስ እና ማስመሪያ ብቻ ወደ ፈተና ማዕከላት ይዘው መሔድ እንደሚችሉ ተመላክቷል።

ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ታብሌት፣ ጆሮ ማዳመጫ፣ ዲጂታል ሰዓት እንዲሁም ማንኛውንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን ይዞ በፈተና ማዕከላት መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
@Adis_Media
@Adis_Media