Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስቴር አቋም የመውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች በምርቃት ላይ እንዳይገኙ የሚል ነው። | 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿

የትምህርት ሚኒስቴር አቋም የመውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች በምርቃት ላይ እንዳይገኙ የሚል ነው።

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር በበኩሉ የተቋማቸውን የሴኔት ውሳኔ ያገኙ ተማሪዎች፥ የመውጫ ፈተና ያለፉም ሆነ ያላላለፉ በምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ እንዲሳተፉ እና የፎቶ ፕሮግራማቸውን እንዲያደርጉ ነው።

የመውጫ ፈተና ያልተሳካለት ተማሪ ጭምር የምረቃ ስነ-ስርዓቱ አካል እንደሚደረግ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር ገልጿል።

ማህበሩ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመከረበት ወቅት ለምንድነው exit exam ያለፉትን ብቻ የምታደርጉት? እነዚህም ቢሳተፉ ምን አለበት? የሚል ጥያቄ አቅርቦ "ይሄ የናንተ ጉዳይ ነው" መባሉን አሳውቋል።

በዚ የመውጫ ፈተና ያላለፉ የሴኔት ውሳኔ ያገኙ በስነ-ስርዓቱ ላይ ይሳተፋሉ። ነገር ግን ዲግሪ/ ጊዜያዊ ዲግሪውን ጭምር አያገኙም ተብሏል። በዚህ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

ምረቃት ላይ ከባችለር ውጭ የመውጫ ፈተና የማይመለከታቸው የማስተርስ ተመራቂዎች ይሳተፋሉ ፤ በዚህ ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ላይ የጨረሱ በሴኔቱ ውሳኔ መሰረት ይሳተፋሉ፤ የመውጫ ፈተና የሚወስዱም የሴኔቱን መስፈርት እስካሟሉ በምረቃ በዓሉ ላይ እንዲሳተፉ ይደረጋል ተብሏል።
@Adis_Media
@Adis_Media