Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ' የሀገሪቱን የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ይረዳኛል ፤ ትውልድ እና ሀገርን | 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ " የሀገሪቱን የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ይረዳኛል ፤ ትውልድ እና ሀገርንም ከውድቀት ይታደጋል " በሚል ዘንድሮ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መስጠት ይጀምራል።

ለዚህ ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ለሁሉም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች በኦንላይን ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና 180 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ፈተናው ላይ ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ተቋማት ለፈተናው ተማሪዎቻቸውን ዝግጁ እያደረጉ ይገኛሉ።

ከዚህ የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ ፈተናውን የማለፍ የማይችሉ ተማሪዎች ፈተናውን ደጋግመው እንዲወስዱ ዕድል ያላቸው ሲሆን በተማሪዎች ምረቃ ላይ ግን የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ ናቸው።

ይህን የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ሁሉም ተቋማት ለማስፈፀም እየሰሩ ይገኛሉ።

ለአብነት ፤ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ " የመውጫውን ፈተና ያለፉ ብቻ " የመመረቂያ ጋዎን እንዲሰጣቸው ክትትል እንዲደረግ አሳስቧል።

የተቋሙ የሬጅስትራር እና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ሰኔ 9 ቀን 2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን በሚመለከት ለሁሉም የተቋሙ አካዳሚክ ክፍል ሬጅስትራሮች በፃፈው ደብዳቤ የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው " የመውጫ ፈተና አፈፃፀም መመሪያ " መሰረት ፤ ኮርስ አጠናቀው ያልተመዘገቡ እንዲሁም ያልተመዘገቡትና ያልፋቁት " F " ያላቸው ተማሪዎች በስህተት ለመውጫ ፈተና ዝርዝራቸው የተላኩ ካሉ የመውጫ ፈተናውን እንደማይፈተኑ ከወዲሁ እንዲነገራቸውና የመውጫ ፈተና ኮርስም እንዳይመዘገቡ አዟል።

የመውጫ ፈተና " መመዝገብ የሚችሉት " ብቻ ኮርሱን እንዲመዘገቡና የምዝገባ ስሊፕ ለመውጫ ፈተና መግቢያ እንዲያገለግላቸው ከወዲሁ ለተማሪዎች እንዲሰጣቸውም ብሏል።

ከዚህ ባለፈ ዳይሬክቶሬቱ ፤ ለምረቃ መሟላት ከሚገባቸው መመዘኛዎች በተጨማሪ የመውጫ ፈተና ያለፉ (50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ) ብቻ ለምረቃ እንዲቀርቡ ፤ የምረቃ መስፈርቱን ያሟሉና የመውጫ ፈተና ያለፉ ብቻ የመመረቂያ ጋዎን እንዲሰጣቸው ክትትል እንዲደረግ ዳይሬክቶሬቱ አሳስቧል።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዘንድሮ የተማሪዎችን ምረቃ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ማካሄድ ይችላሉ።
@Adis_Media
@Adis_Media