Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ነገር በኢትዮጵያ🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ adis_neger_ethio — አዲስ ነገር በኢትዮጵያ🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ adis_neger_ethio — አዲስ ነገር በኢትዮጵያ🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @adis_neger_ethio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.00K
የሰርጥ መግለጫ

🇪🇹እንኳን ወደ አድስ ነገር በኢትዮጵያ ቻናል በሰላም መጡ!🇪🇹
መረጃዎች በትኩሱ ሳይውል እንዲሁም ሳያድሩ በቀጥታ በቻናላችን በኩል ወደ እናንተ ይደርስሎታል!
ቻናላችንን Share & Join በማድረግ ይተባበሩን🙏
ለአስተያየት ወይም ጥያቄ እንዲሁም ለማስታወቂያ ስራዎች በውስጥ👉 @Zednengbot ያድርሱን🙏

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

3

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-12 22:18:24 በጎንደር ከተማ ኤርትራውያንን የጫነ የመከላከያ መኪና ከፍተሻ አካላት ሲያመልጥ በቁጥጥር ስር ዋለ!!

ከጎንደር ከተማ በቅርብ ርቀት ከምትገኘው አምባ ጊዎርጊስ ከተማ ከ 31ኛ ክፍለ ጦር እንደመጣ በመግለፅ ሶስት ኤርትራውያንን የጫነ ኮድ 06580 መ.ከ ሰሌዳ የመከላከያ ሰራዊት መኪና ለመፈተሽ ፈቃደኛ ባለመሆንና ኬላ በመጣስ ለማምለጥ ሲሞክር በቁጥጥር ስር ውሏል።

ወደ ጎንደር ከተማ እየገባ የነበረው ይህ መኪና የአካባቢው የኬላ ተቆጣጣሪዎች ሊያስቆሙት በሚሞክሩበት ጊዜ በቦታው የነበሩ እንስሳትን በመግጨት ሊያመልጥ ሙከራ አድርጓል።

በማምለጥ ላይ ያለው ተሽከርካሪ ከጎንደር ከተማ በ 3 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ወለቃ ቀበሌ ላይ 3 ኤርትራዊያን የጫነው ሹፌር ከነመኪናው በመከላከያ ሰራዊት ኃይል ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ሶስት ኤርትራውያንና የመኪናው አሽከርካሪ በጎንደር ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ አዲስ ዘይቤ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

SHARE & JOIN
@Adis_Neger_Ethio
@Adis_Neger_Ethio
49 viewsedited  19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 19:20:49 የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ፍርድ ቤት ቀርበው በሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው የዕርሻ መሳሪያና የመርከብ ግዢን ክስ ክስ ላይ የመከላከያ ምስክርነት ቃላቸውን ሰጡ።

አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀርበው ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በተከሰሱበት የዕርሻ መሳሪያና የመርከብ ግዢ ሙስና ክስ ላይ በተቆጠሩበት የመከላከያ ምስክርነት በዕውነት ለመመስከር ቃለ መኃላ ፈጽመው ነው የመከላከያ ምስክርነት ቃላቸውን የሰጡት።

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የፍትህ ስርዓቱን አክብረው የመከላከያ ምስክርነታቸውን ቃላቸውን ለመስጠት ፍርድ ቤት በመቅረባቸው ከችሎቱ ዳኞች እና ከሜ/ጀ ክንፈ ጠበቆች ሀፍቶም ከሰተና ከዘረሰናይ ምስግና እንዲሁም ከዓቃቢህግ ጌታሁን ተሰማ በኩል ከፍ ያለ ክብርና ምስጋናና ተችሯቸዋል።

ቃለ መኃላ ከፈጸሙ በኋላ በጠበቆች በኩል አቶ ሀይለማርያም መከላከያ ምስክርነታቸው እንዲሰማ የተፈለገው ጭብጥ ለችሎቱ ተመዝግቧል።

ጠበቆቹ በቀዳሚነት ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው የተከሰሱበት በዕርሻ መሳሪያ ግዢን በተመለከተ የብረታብረትና ኢንጂነሪግና ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለማቋቋም ያስፈለገበት አስረጂ ምክንያቱ ምን እንደሆነ :የትራክተር (የዕርሻ መሳሪያ) በከፊልና በሙሉ ተገጣጣሚ አካላትን እንዲገዛ የተደረገበትን : ሜቴክ የዕርሻ መሳሪያ ለገበሬዎች ሊያቀርብ የፈለገበትን ምክንያት : ፖሊሲው ምን እንደነበር የቴክኖሎጂው ሽግግርን በተመለከተ ሜቴክ እንዲሰራ የተፈለገበትን ምክንያት :በአጋርነት መርህ ላይ ተመስርቶ የሚሰራው አሰራር ከየትኛው ፖሊሲ የመጣ እንደሆነ እና ቴክኖሎጂ በጨረታ የሚገዛበትን ሁኔታን እንዲሁም በኛ ሀገር ደረጃ ቴክኖሎጂ የሚገዛበትን ሂደትን በተጨማሪም ሜቴክ በተቋቋመበት አዋጅና ደንብ መሰረት የሚነሳበት ቅሬታና ችግር ሲኖር ለመፍታት በምን መልኩ አቅጣጫ ተሰቶ እንዲፈታ እንደሚደረግ ገልጸው እንሰዲያስረዱላቸው ጠበቃ ዘረሰናይና ሀፍቶም ጭብጣቸውን አስመዝግበዋል።

አቶ ሀይለማርያምም በተያዘው ጭብጥ መነሻ ከጠበቆች የተነሳላቸውን ዋና ጥያቄ ላይ የመከላከያ ምስክርነታቸው ቃልን ሰተዋል።

አቶ ሀይለማርያም በነበሩበት የሀገር መሪ ሀላፊነት ወቅት በሜቴክ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ የታዩ ጉድለቶች እንዲስተካከሉ የሰጡት አቅጣጫ አላስታውስም ማለታቸውን ተከትሎ ማስታወስ እንዲያስችል ተብሎ በወቅቱ አቶ ሀይለማርያም ከጉብኝት በኋላ ያደረጉትን ውይይትና የተሰጠ አቅጣጫን በተመለከተ በጠበቆች በመከላከያ ማስረጃ የተመዘገበ ቪዲዮን በላፕቶፕ ኮምፒዩተር ለ3 ደቂቃ እንዲመለከቱ ተደርጓል።

በጠበቆች የቀረበ ዋና ጥያቄ ከተጠናቀቀ በኃላ የዓቃቢህግ መስቀለኛ ጥያቄ በተጨማሪም የፍርድ ቤቱን ለተነሳ የማጣሪያ ጥያቄ ላይ አቶ ሀይለማርያም መልስ ሰተዋል።

የዕርሻ መሳሪያ የመከላከያ ምስክርነት ከተጠናቀቀ በኋላ የችሎቱ ዳኞች አቶ ሀይለማርያምን ለ5 ደቂቃ በመኪናቸው ውስጥ እንዲያርፉ አድርገዋል።

ከአምስት ደቂቃ በኋላ ደግሞ በመርከብ ግዢ ክስ ላይ የመከላከያ ምስክርነት ቃላቸው ተሰምቷል።

በመርከብ ግዢን በተመለከተ የሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ጠበቆች ጭብጣቸውን አሲዘዋል።

የአባይና ህዳሴ መርከቦች በመንግስት ውሳኔ ግዢው እንዲፈጸም ከተደረገ በኋላ መርከቦችን ማስተዳደር ጋር በተያያዘ ከኢትዮጲያ ባህር ትራንዚት ጋር እና ከማሪታይም ጋር የነበረ ሰጣ ገባ በተመለከተ ለጠ/ሚኒስትሩ ይጻፍ የነበረ ደብዳቤ ስለመኖሩ ማረጋገጫ ጥያቄ እና መርከቡን አሰርቶ ለማንቀሳቀስ ወይም በስክራፕ ቆርጦ ለማንቀሳቀስ የነበረው ችግርን መንግስት መፍትሄ እንዲሰጥበት ለጠ/ሚ የተጻፈ ደብዳቤ ስለመኖሩ እንዲሁም መርከቦቹ ተገዝተው ከተጠገኑ በኋላ ማሪታይም ከመንግስት አቅጣጫ ካልተቀመጠ ፍቃድ አልሰጥም ማለቱን ተከትሎ ለአቶ ሀይለማርያም የተጻፈ ደብዳቤ መኖሩ ወይም አለመኖሩን እንዲያስረዱላቸው እንደሚፈልጉ ገልጸው ጭብጥ አስመዝግበዋል።

በዚህ ጭብጥ መነሻ ከጠበቆች በቀረበላቸው ዋና ጥያቄ የመከላከያ ምስክርነት ቃላቸውን ሰተዋል።

በወቅቱ የተጻፈ ደብዳቤ እንዳልደረሳቸው የሰጡትን ቃል ተከትሎ በችሎቱ ፍቃድ መሰረት በመንግስት የመፍትሄ አቅጣጫ እንዲሰጥ ከባህር ትራንዚት በጥር 16 ቀን 2006 ዓ/ም ከሜሪታይም ደግሞ ጥቅምት 1ቀን 2006 ዓ/ም የተጻፈ ደብዳቤ በችሎት ቀርቦ እንዲመለከቱ ተደርጓል። ከጠበቃ የተነሳላቸውን ዋና ጥያቄ ካጠናቀቁ በኋላ የዓቃቢህ መስቀለኛ ጥያቄ ሆነ የፍርድ ቤቱ የማጣሪያ ጥያቄ አልቀረበላቸውም።

አቶ ሀይለማርያም በዕርሻ መሳሪያም ሆነ በመርከብ ግዢ ጉዳይ የሰጡት መከላከያ ምስክርነት ቃል ከድምፀ መቅረጫ ወደ ጽሁፍ እንዲገለበጥ ፍርድ ቤቱ አዟል።

አቶ ሀይለማርያም የፍትህ ስርዓቱን አክብረው ፍርድ ቤት መቅረባቸው የዳኝነት ሂደቱን ለመታዘብ እንደሚያስችላቸው የችሎቱ ዳኞች ገልጸው አመስግነዋቸዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

SHARE & JOIN
@Adis_Neger_Ethio
@Adis_Neger_Ethio
89 viewsedited  16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 10:27:29
" የተጭበረበራችሁ በስልክም ፤ በአካልም እየቀረባችሁ አመልክቱ " - የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በተለያዩ የኦንላይን ማጭበርበሪያ ድርጊት ገንዘባቸውን ያጡ ሰዎች በ991 ወይም 987 ላይ መረጃ መስጠት ይችላሉ አለ።

ፌዴራል ፖሊስ ይህን ያለው ለኢቢሲ በሰጠው ቃል ነው።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጄይላን አብዲ ፤ " የማህበራዊ እና የኦንላይን ሚዲያዎችን በመጠቀም የበርካታ ሰዎችን ገንዘብ ከሰበሰቡ በኋላ አድራሻቸውን በማጥፋት የተሰወሩ አካላት መኖራቸውን ከደረሰ ጥቆማና ከተለያዩ ምንጮች መረዳት ችለናል " ብለዋል።

ይህን ጉዳይ አስመልከቶ ከተለያዩ የህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር መረጃ የማጣራት እና የምርመራ ስራ እየተሰራ ይገኛል የማጭበርበር ድርጊት የተፈፀመባቸው እና የተመለከቱ ከላይ ባሉት ስልኮች እየደወሉ ማመልከት ይችላሉ ብለዋል።

ከስልክ በተጨማሪ ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ የኢንተለጀንስ ቢሮ በመቅረብ መረጃ መስጠት እንደሚችሉ ኃላፊው ለኢቢሲ ተናግረዋል።

ልክ እንደ FIAS 777 አሁን ላይ የተመሳሳይ የማጭበርበር ስራ ከሚሰራባቸው ድረገፆች መካከል hulu61፣ HDU፣ workxo፣ Crowd 1፣ vemo1፣ Alpha Breakthrough፣ FNB እና ሌሎችም ተጠቃሽ መሆናቸው ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም በFIAS 777 እና መሰል ድርጅት ነን ባዮች ከ1 ሺ ብር አንስቶ ከ100 ሺህ ብር በላይ የተጭበረበሩ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይፈልግላቸው ዘንድ ጥሪ ሲያቀርቡ እንደነበር አይዘነጋም።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

SHARE & JOIN
@Adis_Neger_Ethio
@Adis_Neger_Ethio
177 views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 09:14:14 #አስቸኳይ_ማሳሰቢያ

ለ2014 የትም/ት ዘመን 12ኛ ክፍል ማጠቃለያ (ሀገር አቀፍ ) ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ

በ2014 ዓ.ም የመደበኛም ይሁን የግል ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና ምዝገባ ሂደት በሁለት(በዳርማሎግ/online/ እና በ"DRS"/በወረቀት) አማራጮች እየመዘገብን መቆየታችን ይታወሳል።

ሆኖም ግን ጥቂት ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች የአንደኛውን አማራጭ ምዝገባ ብቻ በመመዝገብ ቀሪውን እንደዘለሉት ከመዋቅሮች የሚመጡ መረጃዎች ያሳያሉ ፤ ስለሆነም ማንኛውም ተማሪ የ2014 12ኛ ክፍል ፈተና መፈተን የሚችለው ሁለቱንም የምዝገባ አማራጮችን አሟልቶ ሲጠቀም ብቻ እነደሆነ በአፅንኦት እየገለፅን ፤ የDRS ምዝገባ ያልተመዘገባችሁ በሙሉ ቀሪ ሁለት ቀናትን (ከሀምሌ 04 እስከ 05/11/2014) በመጠቀም ቀደም ስል በተመዘገባችሁበት ትምህርት ቤት በአካል በመቅረብ አሰፈላጊውን እንድታሟሉ እናሳስባለን።

ትምህርት ሚኒስቴር

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

SHARE & JOIN
@Adis_Neger_Ethio
@Adis_Neger_Ethio
166 viewsedited  06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 11:49:12
ሩሲያዊው ፖለቲከኛ ጦርነቱን በማውገዛቸው የሰባት ዓመት እስር ተፈረደባቸው

በሞስኮ ምክር ቤት አባል የሆኑት አሌክሲ ጎሪኖቭ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ተቃውመው በመናገራቸው የሰባት ዓመት እስር ተፈረደባቸው። ግለሰቡ በተቃዋሚዎች ላይ ያነጣጠረ ነው በተባለለት አዲስ ሕግም የመጀመሪያ እስር የተፈረደባቸው ፖለቲከኛ ሆነዋል።

የ60 ዓመቱ ፖለቲከኛ በከተማዋ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ወረራውን ሲነቅፉ በተንቀሳቃሽ ምስል ከተቀረጹ በኋላ ሚያዝያ ላይ ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት። ከወረራው በኋላ በወጣው ሕግ መሠረት ስለ ወታደራዊ ኃይሉ "ሐሰተኛ ዜና" የሚያሰራጭ ማንኛው ግለሰብ እስከ 15 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ይጠብቀዋል።

ሩሲያ ዩክሬን ላይ ወረራ ከከፈተች በኋላ የአገሪቱ ዜጎች ወረራውን "ጦርነት" ብለው እንዳይገልጹ ክልከላ ተጥሎባቸዋል። ከዚህ ይልቅ ግን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱን ለመግለጽ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" የሚል አገላለጽን አስተዋውቀዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

SHARE & JOIN
@Adis_Neger_Ethio
@Adis_Neger_Ethio
199 viewsedited  08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 11:47:04
በአማሮ ልዩ ወረዳ በሰኔ ወር ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ ስድስት አርሶአደሮች እንደተገደሉ ተነገረ!!

ከምዕራብ ጉጂ አማሮ ልዩ ወረዳ ወደሚገኙ ቀበሌዎች ይገባሉ የተባሉት ታጣቂዎች በተደጋጋሚ በአርሶአደሩ ላይ ተኩስ በመክፈት ግድያና ዝርፊያ እንደሚፈፅሙ የልዩ ወረዳዉ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር አራርሶ ነጋሽ ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል። ትላንት በዶርባዴ ቀበሌ የአካባቢው ነዋሪዎች "የሸኔ ታጣቂዎች" በማለት የሚጠሯቸዉ ሰዎች በአርሶአደሮች ላይ በደፈጣ በወሰዱት ተኩስ የተገደለን አንድ አርሶ አደር ጨምሮ በአጠቃላይ በሰኔ ወር ስድስት አርሶ አደሮች ሲገደሉ ሶስት ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ለግጭቱ መነሻ ምክንያት ለአማሮ ልዩ ወረዳ አጎራባች የሆነዉ የጉጂ ኦሮሚያ ነዋሪዎች በሚያነሱት "የወሰን ይገባኛል" ጥያቄ በተደጋጋሚ እየወሰዱት የሚገኘዉ የድንበር ማስፋፋት እርምጃ ሲሆን ከጉጂ ኦሮሚያ በሚመጡ ታጣቂዎች ባሳለፍነው ወር ከ 100 በላይ ከብቶች ሲዘርፉ በብርሃን ሃይል የሚሰሩ 14 የኔትዎርክ ማማዎች ማዉደምና መዘረፉቸውን ም/ኢንስፔክተር አራርሶ ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

SHARE & JOIN
@Adis_Neger_Ethio
@Adis_Neger_Ethio
171 viewsedited  08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 20:13:12
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ማህሙድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኤርትራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ማህሙድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ኤርትራ አስመራ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ማህሙድ÷የኤርትራ አቻቸው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት ነው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ ያመሩት፡፡

የሶማሊያ አዲሱ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ማህሙድ አስመራ ሲደርሱም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

SHARE & JOIN
@Adis_Neger_Ethio
@Adis_Neger_Ethio
199 viewsedited  17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 20:11:43 ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን አልምቶ ለመጠቀም ስምምነቷን ከሶማሊላንድ ጋር ዳግም ማጽናቷ ተሰምቷል!

ኢትዮጵያ ቀደም ሲል የነበረውን በበርበራ ወደብ አልምቶ የመጠቀም መብቷ እንደማይነካባት በሶማሊላንድ ፕሬዚደንት በኩል ይፋ ሆኗል ሲል የምሥራብ የሬድዮ መጽሔት አስነብቧል፡፡

ከትናንት በስቲያ ወደ ሶማሊላንድ ከተማ ሐርጌሳ የኢትዮጵያ ልዑክ ማቅናቱንና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንዲሁም በአምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተመራ የልዑካን ቡድን ከሶማሊላንድ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ጋር መነጋገሩን የሶማሊላንድ ብሔራዊ ጣቢያ ተናግሯል፡፡

ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ለማልማት ከሶማሊላንድና ከዲፒ ወርልድ ኩባንያ ጋር የጋራ ስምምነት እንደነበራት ይታወቃል፡፡ በዚህ ስምምነት 19 በመቶ የወደቡና ድርሻ የምትይዝ ሲሆን ባለፈው ወር ክፍያ ባለማጠናቀቋ ድርሻዋ ተነጥቋል ሲሉ የሶማሊላንድ የገንዘብ ሚኒስቴር መናገራቸውም ይታወሳል፡፡

ይህን የተናገሩት ሚኒስትር ጭምር በተገኙበት ፕሬዚደንታዊ የእራት ግብዣ የተደረገለት የኢትዮጵያ ልዑክ ስምምነቱ ባለበት አንደሚቀጥል ማስተማመኛ ተሰጥቶታል፡፡

(ኤሊያስ-መሰረት)

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

SHARE & JOIN
@Adis_Neger_Ethio
@Adis_Neger_Ethio
190 viewsedited  17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 12:24:50
በመዲናዋ 1443ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል የሶላት ሥነ ሥርዓት በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

1443ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በላም እንዲከበር የፀጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ወቅታዊውን የፀጥታ ሁኔታ ያገናዘበ ዕቅድ በማውጣት ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱ የሚታወቅ ነው፡፡

ኅብረተሰቡንና የዕምነቱ ተከታይ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር በተሰራው ሥራ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ዙሪያ የተከናወነው የሶላት ሥነ ሥርዓት በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ሥነ ሥርዓቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የበዓሉ ታዳሚዎች ላሳዩት ቀና ተባባሪነት እና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ተግባራቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ በፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ስም ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ቀሪው የበዓል አከባበር ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል በየአካባቢው በቂ የፀጥታ ኃይል ተመድቦ ተግባሩን እየተወጣ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኅብረተሰቡ ከፀጥታ ጉዳይ ጋር ተያያዥ መረጃ ወይም ጥቆማ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮች እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97 መጠቀም ይችላል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

SHARE & JOIN
@Adis_Neger_Ethio
@Adis_Neger_Ethio
217 viewsedited  09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 12:23:02
1443ኛው የኢድ አልአድሀ (አረፋ) በአፋር ክልል በአል በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1443ኛው የኢድ-አልአድሀ (አረፋ) በአል በአፋር ክልል ሰመራን ጨምሮ በዱብቲ፣ በሎግያ እና በተለያዩ የክልሉ ከተሞች እና አካባቢዎች በድምቀት ተከብሯል፡፡ በበዓሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች እና ተከታዮች በተገኙበት ነው የተከበረው፡፡ በበአሉ የተገኙ የሃይማኖቱ አባቶች እንደገለጹት÷ በዓሉ ለመላው የሙስሊሙ ማህበረሰብ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እንዲሆንላቸው መልካም የምኞታቸውን ገልፆዋል ።

መልካም በዓል

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

SHARE & JOIN
@Adis_Neger_Ethio
@Adis_Neger_Ethio
195 viewsedited  09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ