Get Mystery Box with random crypto!

ከሶማሌላንድ ግጭት ሸሽትው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር ጨመረ ሶማሌላንድ የተከሰተውን ግ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

ከሶማሌላንድ ግጭት ሸሽትው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር ጨመረ

ሶማሌላንድ የተከሰተውን ግጭት በመሸሽ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መሆኑ ታወቀ። ግጭቱ ወደ አርስ በእርስ ጦርነት ከፍ ብሎ ዳፋው ለጎረቤት ሀገሮችም እንዳይተርፍ ተሰግቷል።

ከሁለት ወራት በፊት በኢትዮጵያ አጎራባቿ ሶማሌላንድ በስተደቡብ ክፍል 'ላሳአኖድ' በተባለችው ከተማ አቅራቢያ በመንግስትና በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል በተነሳ ግጭት በርካቶች ሲገደሉ ቁጥሩ ወደ 100 ሺህዎች የሚጠጋ ህዝብ ደግሞ ቀዬውን ለቆ ተፈናቅሏል። በርካቶቹም ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አቋርጠው በመግባት በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ተሰባስበዋል።

በርካታ ሴቶችና ሕፃናት ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን እየገቡ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ዋና ኮሚሽን ከሳምንት በፊት ባወጣው ሪፖርት ላይ አስታወቆ ነበር። እስካሁንም በዞኑ ቦህ፣ ገልሃሙር እና ዳኖድ በተባሉ ሦስት ወረዳዎች አጠቃላይ ቁጥራቸው ከ90 ሺህ በላይ የሆኑ ስደተኞችን መመዝገቡን ኮምሽኑ አስታውቋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ -
https://am.addiszeybe.com/featured/dire-dawa/politics-am/current-affairs-am/economy-am/the-number-of-refugees-fleeing-the-conflict-in-somaliland-and-entering-ethiopia-has-increased