Get Mystery Box with random crypto!

በኬንያ የታገተው ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ክስ መሰረቱ ከአንድ ዓመት ከስድስ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

በኬንያ የታገተው ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ክስ መሰረቱ

ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በፊት ኬንያ ውስጥ “የፖሊስ ደንብ ልብስ” በለብሱ ሰዎች ተወስዶ እስካሁን ያለበት አልታወቀም የተባለው የአቶ ሳምሶን ተክለሚካኤል ቤተሰቦች የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ላይ ክስ መሰረቱ።

የመንግስት አካላቱ ላይ የተከፈተውን ክስ በተመለከተ በዛሬው እለት የአቶ ሳምሶን ባለቤት ወ/ሮ ሚለን ሀለፎም እንዲሁም በፌደራል እና በኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች ጠበቃ የሆኑት አቶ ዳባ ጩፋ (ዶ/ር) በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

ወ/ሮ ሚለን ሀለፎም እንደተናገሩት ከባለቤታቸው መሰወር በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት የተወሰኑ ጥረቶች ቢያደርግም አንድ ዜጋ በውጭ ሀገር መብቱ ሲጣስ ማድረግ ከሚገባውው አንፃር በቂ ባለመሆኑ ክስ መክፈቱ አስፈላጊ ሆኗል ብለዋል።

ጉዳዩን የያዙት የህግ ባለሞያ አቶ ዳባ ጩፋ በበኩላቸው “ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የመጣበት ምክንያት እነዚህ የተከሰሱ አካላት ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ነው። ፍርድ ቤት በህግ አግባብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማስገደድ የሚችል በመሆኑ እንደሚያስገድዳቸው እንጠብቃለን” ሲሉ ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/addis-ababa/%E1%8B%9C%E1%8A%93/politics-am/current-affairs-am/business-am/the-families-of-the-ethiopian-kidnapped-in-kenya-filed-a-lawsuit-against-the-ethiopian-government