Get Mystery Box with random crypto!

አንዷለም አራጌ እና ኢዜማ ተለያዩ ታዋቂው ፖለቲከኛ እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

አንዷለም አራጌ እና ኢዜማ ተለያዩ

ታዋቂው ፖለቲከኛ እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ(ኢዜማ) አመራር የነበሩት አቶ አንዷለም አራጌ ከፓርቲያቸው መለይየታቸውን ለፓርቲው ባስገቡት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡ አቶ አንዷለም “ አይነግቡ እና ዘመን ተሻጋሪ ለማድረግ” የያዙት ህልም እውን ስለማይሆን ከፓርቲው ጋር መቀጠል አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

አቶ አንዷለም አራጌ ለፓርቲው ባስገቡት እና በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባሰራጩት የመልቀቂያ ደብዳቤ ላይ “ኢትዮጵያ በየትኛውም የታሪክ ድርሳን ላይ ከሰፈረው መከራዋ ሁሉ የከፋውን በምታስተናግድበት በዚህ ዘመን” ለሀገሪቱ እና ለዜጎቿ መድህን ይሆናል የተባለው ፓርቲው “የተሳከረ ሚና” እየተጫወተ ነው ብለዋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/addis-ababa/politics-am/current-affairs-am/arage-and-izema-parted-ways