Get Mystery Box with random crypto!

የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ የፊታችን መስከረም 10 ቀን፤ ለ5 ሺሕ የአገር ውስጥ ሮስካ ተመዝጋቢዎች ዕጣ | Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ የፊታችን መስከረም 10 ቀን፤ ለ5 ሺሕ የአገር ውስጥ ሮስካ ተመዝጋቢዎች ዕጣ የማውጣት ሥነሥርዓት እንደሚያከናውን አሰታወቀ

ሐሙስ ነሐሴ 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ ትሬዲንግ ከዚህ ቀደም ጳጉሜ 03 ቀን 2014 አከናውነዋለሁ ብሎት የነበረውን የዕጣ ማውጣት ሥነሥርዓት ወደ መስከረም 10 ቀን 2015 መቀየሩን በዛሬው ዕለት አስታውቋል።

በዕጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓቱ ላይም 5 ሺሕ የአገር ውስጥ ሮስካ ተመዝጋቢዎች እንደሚሳተፉበት ገልጿል።

የጎጆ ሃውሲንግ ትሬዲንግ መሥራችና ምክትል ዳይሬክተር ናደው ጌታሁን ዕጣ የሚወጣበት ጊዜ የተራዘመበትን ምክንያት ሲያስረዱ፤ በተመዝጋቢ አባላት የይራዘምልን ጥያቄና በአባላቱን ቁጥር በመጨመር የዕጣ ብዛቱንም ከፍ ለማድረግ በመታሰቡ መሆኑን ተናግረዋል።

በዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይም የ5 ሺሕ የአገር ውስጥ ሮስካ ተመዝጋቢዎች እጣ እንደሚወጣ፣ 4 ያለቁ ሳይቶችን ካርታ ለህብረት ሥራ ማህበራት የማስረከብ፣ 4 ያለቁ ሳይቶች የግንባታ ፍቃድ ርክክብ እንዲሁም አዲስ ለተመዘገቡ 4 መቶ አባላት የሚደራጁበትን ቦታ የማሳወቅ መርሃ ግብሮች እንደሚከናወን ምክትል ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

በተጨማሪም በዕለቱ ከጤና ሚኒስቴርና ከዳሽን ባንክ ጋር ለጤና ባለሙያዎች የመኖሪያ መንደር ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት እንደሚያደርግም ተገልጿል።

ጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ የተቋቋመው የዜጎችን የቤት ችግር ለመፍታት ቤት ፈላጊዎችን በህብረት ሥራ ማህበራት አደራጅቶ የቤት ባለቤት ማድረግ ነው ያሉት የጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ የማህበራት ማደራጀት ክፍል ሀላፊ አጋ ፉፋ ሲሆኑ፤ እነዚህንም ማህበራት ጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ የራሱን የማህበራት ክፍል በማቋቋም ክትትል እና ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የህብረት ሥራ ማህበራቱ የራሳቸው የክትትል እና ቁጥጥር ኮሚቴ እንዳላቸው የገለጹት አጋ በማህበር መደራጀታቸው በህብረት ሥራ ማህበረት አዋጅ መሰረት የግንባታ ቦታን የማገኘትና የግንባታ እቃዎችን ከግብር ነፃ የማስገባትን ዕድል ይሰጣቸዋል ብለዋል።

ጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ እስካሁን ድረስ 4 ሳይቶች፣ 8 ማህበራት እና 1 ሺሕ 55 አባላትን ማፍራት መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፤ መስከረም 11 በሚጀመረው አዲስ ምዝገባም የተሻሻለውን የሮስካ ክፍያ እና አሠራር ለተጠቃሚ በማስተዋውቅ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት 55 ሺሕ ብር የነበረወሰ ቅድመ ክፍያ ወደ 59 ሺህ ብር እንዲሁም በየወሩ ለ10 ዓመታት ይቆጠብ የነበረው የ2 ሺሕ ብር ወርሃዊ መዋጮ ወደ 2 ሺሕ 200 ብር ማሳደጉን አስታውቋል።
_____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n