Get Mystery Box with random crypto!

“ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል” የተባለው የቻይናው ሮኬት በህንድ ውቅኖስ ላይ ወደቀ ************** | Addis Idea / አዲስ ሀሳብ

“ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል” የተባለው የቻይናው ሮኬት በህንድ ውቅኖስ ላይ ወደቀ
************************************
“ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል” የተባለው የቻይናው ሮኬት በህንድ ውቅኖስ ላይ መወደቁን መረጋገጡን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት አስታወቀ።

የኢንስትቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ ለኢቲቪ እንደገለፁት የቻይና ሎንግ ማርች 5ቢ ሮኬት ተወሰነ ክፍሉ መሬት ላይ ሳይደርስ የተቃጠለ ሲሆን የቀረው ስብርባሪም በህንድ ውያኖስ ማልዲስቭስ ደሴት አካባቢ ውቅያኖስ ውስጥ ወድቋል።

አቶ አብዲሳ እንዳሉት ሮኬቱ ወደ መሬት ከባቢ አየር በመግባት መምዘግዘግ የጀመረው በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከንጋቱ 11:24 ላይ ነበር።

አሁን የቻይና ይፋዊ ሪፓርት እንዳስታወቀው ሰማይ ላይ ከተቃጠለው ውጭ ያለው የሮኬቱ ክፍል72.47 ምስራቅ እና2.65 ሰሜን አቅጣጫ ላይ ህንድ ውቅያኖስ ላይ ወድቋል

@zenatoday @zenatoday