Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopia today ኢትዮጵያ ዛሬ

የቴሌግራም ቻናል አርማ addisethiopiame — Ethiopia today ኢትዮጵያ ዛሬ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ addisethiopiame — Ethiopia today ኢትዮጵያ ዛሬ
የሰርጥ አድራሻ: @addisethiopiame
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 548
የሰርጥ መግለጫ

ፍቅርን አንድነትን እና ኢትዮጵያዊነትን ማወደስ:: ወቅታዊና አዳዲስ መረጃ ማድረስ። I proud to be an Ethiopian.

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-05 13:31:39
እያንዳንዱ ሰው አንድን ነገር በጥሩ ሁኔታ መሥራት ይችላል። በአንዴ ብዙ ቢሞክር ግን በየትኛውም ልዩነት መፍጠር አይችልም።
~{ከፕላቶ አንደበት}

ትልቁ ቁብነገር ብዙ ነገርን በአንዴ ማድረጉ ሳይሆን፣ አንድን ተግባር በሙሉ ትኩረትና ጥሞና በተመጠነ ሰዓት መከወን መቻል ነው። የጅምር ብዛት ለውጥ አያመጣም፤ ለፍፃሜም አያደርስም። የትኩረት ሃይል እምቅ አቅም ነው። የሚባክነው ሲበታተንና በተገቢው ስፍራ ሳይውል ሲቀር ነው። ያተኮርክበት ሁሉ ፍሬያማ ሲሆን፣ ችላ ያልከውም በምትኩ ፊቱን ሲያዞርብህና ከውጤት ሲያርቅህ ትመለከታለህ። ትኩረትና ጊዜ የሰጠኸው ማንኛውም ነገር የውስጥ ፍላጎትና ውጤትህን የሚወስን ነው።

በአንዴ አንድን ብቻ ተግብር፣ መሰረታዊ ልዩነት ባላቸው የተለያዩ ሃሳቦችህ አዕምሮህን አታስጨንቀው፤ ፋታ አታሳጣው፤ እርጋታ አትንሳው። አንድን ተግባር ብቻ በተወሰነ ሰዓት መፈፀም የሚኖርብህ ዋነኛው ምክንያት የትኩረት አቅምህን፣ እምቅ ሃይልህን በሚገባ ለመጠቀም እንዲያስችልህ ነው። ተግባርህ ምንም ይሁን የውጤታማነቱ ሚስጥር ብዛቱ ወይም መደራረቡ ሳይሆን የተሰጠው ትኩረትና በቂ ጊዜ ነው። ከመዳረሻህ የሚያደርስህ ብዙ መንገድ ቢኖርም አንዱንና በይበልጥ ያመንክበትን ጠንቅቀህ ያዝ፤ በዛው መንገድ እስከጥግ ተጓዝ፤ በሙሉ ትኩረትም አቅጣጫህን ወደ አንደኛውና አዋጭ ወዳልከው አዙር።
46 views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 11:17:02
#Confirmed_የተረጋገጠ
አዲስ አበባ ውስጥ ከ200 በላይ ሰዎች ስልካቸው ከተሰረቁ በኋላ እስከ ግማሽ ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የባንክ አካውንታቸውና CBE የነበረ ገንዘባቸውን ተዘርፈዋል።

* በዚህም በሚሊዮን የሚገመት ገንዘባቸውን አጥተዋል።

የዘረፋ ዘዴያቸው - መደበኛ አካውንትን (ሞባይል ባንኪንግ የተመዘገቡ) እና CBE መግቢያ ማለፊያ Password እንደጠፋባቸው በማስመሰል ስልኩ ላይ Notification (Message) እንዲላክላቸው ያደርጉና ይቀይሩታል። በሌላ አባባል ሁለቱንም አካውንት ይቆጣጠሩታል።

ገንዘቡን በሀሰት ስም በወጣ ሲም ለተመዘገበ CBE አካውንታቸው ሙጥጥ አድርገው ያዛውሩትና ያወጡታል።

መደረግ ያለበት ጥንቃቄ ከባንክ ጋር ለተያያዘ አገልግሎት የምትጠቀሙበት ስልክ መስመር በከፍተኛ ጥንቃቄ ያዙ።

ባንኮችና ቴሌ(CBE) ማለፊያ ቃል (Password) የመቀየር አገልግሎት በአካል(በቅርብ በሚገኝ የባንኮች ቅርንጫፍ) ብቻ ቢያደርጉት መልካም ነው።

በተጨማሪም የATM ማለፊያ ቃል ስልክ ላይ ሴቭ ባታደርጉ ይመረጣል።

** ብዙ ሰዎችም የATM ካርዳችሁ የሞባይል ሽፋን ውስጥ አታስቃምጡ

ሴቭ ከተደረገ ንግድ ባንክ ያለ ካርድ የATM አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ ተጨማሪ የሌብነት መንገድ እንደፈጠረ መረዳት ይገባል።

Social media
የተለያዩ ባንኮች ደንበኞቻቸው ከመሰል የመጭበርበር ድርጊት ሰለባ እንዳይሆኑ በተለያዩ አጋጣሚዎች ግንዛቤ ሲፈጥሩ ይስተዋላል። ሆኖም ግን ዛሬም ድረስ ሰዎች እየተጭበረበሩ ይገኛሉ።
ባንኮችም የደንበኞቻቸውን የባንክ አካውንት እና ገንዘባቸውን ከአጭበርባሪዎች ለመጠበቅ የተለያዩ ጥናቶችን ማድረግ፣ ተሞክሮዎችን ማየት በተለይም ከአሻራ ጋር የተያያዘ ማድረግ ይገባቸዋል የሚል የግል ምልከታ አለኝ።
53 views08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 08:21:51 Vacancy Announcement

Organization: Wollo University
Total Number of Positions: 240+
Location: Wollo, Amhara Region

Professionals needed:-
- Medical doctor (General Practitioner)
- Doctor of Dental medicine
- Nursing, midwifery, Emergency and critical care Nursing (TA)
- BSc in Anesthesia
- BSc in Medical Laboratory Science
- BSc in Emergency and Critical care Nursing
- BSc or post basic BSc in Health informatics
- BSc in Environmental health; Environmental and occupational health
- BSc in Psychiatry nursing
- BSc in Opthalmic Nursing
- BSc in Pharmacy
- Medical doctors with various specialty and Sub specialties
- MSc in biochemistry, HSM, Health promotion, Clinical Midwifery, Ophthalmic nursing or optometry, Emergency medicine and critical care nursing, neonatal nursing, pediatric and child health nursing
- Assistant professor in epidemiology and biostatistics, health informatics, adult health nursing, medical nursing, surgical Nursing, pediatric and child health nursing, neonatal nursing, Emergency medicine and critical care nursing, molecular biology, immunology , clinical chemistry, hematology and immuno hematology, medical anatomy, medical physiology, medical biochemistry, integrated clinical and community mental health

- PHD in Reproductive health, public health Nutrition, medical biochemistry, medical physiology, Water & health...

Minimum Experience: 0 - year up to 2 - years

For requirements and other detail information, please use the following link:
ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
https://bit.ly/3zoBajW
Application Deadline: August 16, 2022
77 views05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 11:39:26
Pi is a new digital currency developed by Stanford PhDs, with over 35 million members worldwide. To claim your Pi, follow this link https://minepi.com/sewa2591 and use my username (sewa2591) as your invitation code.
82 views08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 11:35:00 Pi is a new digital currency developed by Stanford PhDs, with over 35 million members worldwide. To claim your Pi, follow this link https://minepi.com/sewa2591 and use my username (sewa2591) as your invitation code.
73 views08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 09:47:15 According to Psychologists, there are four types of Intelligence:
1) Intelligence Quotient (IQ)
2) Emotional Quotient (EQ)
3) Social Quotient (SQ)
4) Adversity Quotient (AQ)
1. Intelligence Quotient (IQ): this is the measure of your level of comprehension. You need IQ to solve maths, memorize things, and recall lessons.
2. Emotional Quotient (EQ): this is the measure of your ability to maintain peace with others, keep to time, be responsible, be honest, respect boundaries, be humble, genuine and considerate.
3. Social Quotient (SQ): this is the measure of your ability to build a network of friends and maintain it over a long period of time.
People that have higher EQ and SQ tend to go further in life than those with a high IQ but low EQ and SQ. Most schools capitalize on improving IQ levels while EQ and SQ are played down.
A man of high IQ can end up being employed by a man of high EQ and SQ even though he has an average IQ.
Your EQ represents your Character, while your SQ represents your Charisma. Give in to habits that will improve these three Qs, especially your EQ and SQ.
Now there is a 4th one, a new paradigm:
4. The Adversity Quotient (AQ): The measure of your ability to go through a rough patch in life, and come out of it without losing your mind.
When faced with troubles, AQ determines who will give up, who will abandon their family, and who will consider suicide.
Parents please expose your children to other areas of life than just Academics. They should adore manual labour (never use work as a form of punishment), Sports and Arts.
Develop their IQ, as well as their EQ, SQ and AQ. They should become multifaceted human beings able to do things independently of their parents.
Finally, do not prepare the road for your children. Prepare your children for the road."
72 views06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 19:57:47 የአጎቴ አነቃቂ ንግግሮች እና የእኔ መፍዘዝ!

እንደማንኛውም ዕድሜው ለማትሪክ የደረሰ ኢትዮጵያዊ ወጣት ፣ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት መጥቶልኝ፣ ዩኒቨርሲቲ የመግባትና ተመርቆ የመውጣት ዕድል ገጥሞኛል። በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ አጎቴ ብዙ ምክርና ትንሽ የኪስ ገንዘብ በመላክ እያማረረ አስተምሮኛል። (አጎቴ ግን ለሰዎች ሲናገር <እያዝናናሁ አስተማርኩት> ነው የሚለው) የሚልክልኝ ብር በጣም ከማነሷ የተነሳ፣ አንዳንዴ እንደ ደሃ የሻምፖ ዕቃ፣ ኪሴን አለቅልቄ ነበር የምጠቀምባት¡

ተመርቄ እንደወጣሁ አጎቴ ድል ያለ ድግስ ደግሶ፣ ያንን ሁልጊዜ ፍርድ ቤት ሲሄድ የሚለብሰውን ሰማያዊ ኮትና ሱሪውን ለብሶና ነጭ ከረቫት አስሮ ፣ ለታዳሚው ረዘም ያለ የመክፈቻ ንግግር አደረገ ‹‹ አብርሃም ከድሮውም ገና ከልጅነቱ አንጎሉ ለትምህርትና ለነገር እንዲሁም ለእንስቶች ጨዋታ ክፍት ነበር፤ እንሆ አሁንም ከታላቁ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በሳይኮሎጂ ተመርቆ አኩርቶናል›› አለ፡፡ ታዳሚው ቀልቡንም ዓይኑንም ወደተዘጋጀው ቡፌ እንደላከ፣ በየአራት ነጥቡ ያጨበጭብ ነበር፡፡ ወደጆሮው ጠጋ ብዬ ‹‹ሳይኮሎጂ አይደለም አጎቴ ሶሾሎጂ ነው ›› ብዬ አረምኩት! ወደኔ ገልመጥ ብሎ ‹‹ተወው ይኼ ሕዝብ የወሬ ጅራት ይዞ ነው የሚሮጠው … ምናለ በለኝ ‹ሎጂ› የሚለውን ብቻ ነው የሚያስታውሰው›› አለኝ ! እውነትም ታዳሚው ከበላና ከጠጣ በኋላ ‹‹በምን ሎጂ ነበር የተመረቅኸው?›› እያለ ይጠይቀኝ ነበር፡፡ ኑሮና ዕድሜ አጎቴን በሳይኮሎጂ ሳያስመርቁት አልቀሩም!

እንደአብዝሃኛው ኢትዮጵያዊ ተመራቂ ሁሉ እኔም ሥራ አጥቼ ለአንድ ዓመት ተቀመጥኩ፡፡ በዚህም አጎቴ በጣም ከመበሳጨቱ የተነሳ እቤት ተቀምጨ፣ ወይም አየር ልቀበል ብዬ የሰፈራችን ልጆች የሚቆሙባት ሱቅ ቆሜ ባዬኝ ቁጥር ‹‹አሁን እኔ ሰው አስመረኩ ነው የምል ወይስ ሐውልት አስመረኩ?›› እያለ ያጉረመርማል፡፡

እንዲያው 'ጨለምተኛ' አልባልና፣ የአገራችን ሥራ አጥነት በዚህ ከቀጠለ በቅርቡ ተመራቂዎች ‹‹እንኳን ደስ ያላችሁ! ›› የሚለውን መዝሙር እንደሙሾ ደረታቼውን እየደቁ መዘመራቼው አይቀርም!

ሥራ አጥቼ በተቀመጥኩባቸው ጊዚያት ከምንም በላይ ያስመረረኝ እና ያፈዘዘኝ ‹‹የአጎቴ አነቃቂ ንግግር›› ነበር፡፡ አንድ ቀን አዲስ ዘመን ጋዜጣ ይዞ መጣና እፊቴ እንደምንጣፍ ዘረጋግቶ ‹‹ ተመልከት ›› አለኝ፡፡ እኔ ደግሞ የሥራ ማስታወቂያ መስሎኝ ጋዜጣውን አዬት አደረኩት ‹‹ሁለት እጅ የሌለው የእንጨት ባለሙያ ›› ይላል …ጋዜጣው ላይ በአንድ እግሩ ጣቶች፣ ባለባርኔጣውን ሚስማር ፣ በሌላኛው እግሩ፣ መዶሻ የያዘ አካል ጉዳተኛ ኩርሲ ወንበር ሲሠራ ይታያል፡፡ አጎቴ ኮስተር ብሎ ‹‹ አዬህ አብረሃም፣ አንተ በእግርህ ሮጥ ሮጥ ብለህ ሥራ መፈለግ ሰንፈሃል፣ሰው በእግሩ የሚሠራውን ተዓምር አዬህ አይደለም? …እንድትነቃቃ ብዬ ነው ጋዜጣውን የገዛሁት …በእርግጥ አዋጅም ታትሞ ከሆነ ብዬ ነበር፤ አለና ጋዜጣውን አጣጥፎ ሄደ ።

ሌላ ቀን ወደቤት ስገባ፣ አጎቴ በእጁ በያዘው ሪሞት ወደ 15 ኢንች ቴሌቪዥኑ እየጠቆመኝ ‹‹ና ተቀመጥ ! እግርህ ጥሩ ነገር ላይ ነው ዛሬ የጣለህ …. ተመልከት …እየው ይኼ ሰውዬ እንዳንተው ሰው ነው …ግን በምን እንደሁ እንጃ እንደምታየው እግሩ አይሠራ ፣እጁ አይንቀሳቀስ ፣ አፉ አይናገር፣ ከንፈሩ አይላወስ …. ዓይኑ ብቻ ናት የምትርገበገበው:: አንተ በጥቅሻ የሰፈሩን ልጃገረድ ስታማልል ፣ እሱ በጥቅሻ ሰማዬ ሰማያት ዘልቆ፣ ፀሐይ አልቀረው ጨረቃ ….እስተ ሰባተኛው ሰማይ ዘልቆ ስንት ሳይንስ፣ ስንት ምርምር ሠራ !…አሁን አንተ ተሱ ታንሳለህ አብርሃም ? እንድትነቃቃ ነው ይኼን የምነግርህ …አዚምህ እንዲለቅህ ›› ቴሌቪዥኑ ላይ ፈጥጨ ቀረሁ ፡፡ ከሱ አታንስም ያለኝ ታዋቂው እንግሊዛዊ ፊዚስት እና ኮስሞሎጅስት ስቴፈን ሃውኪንግን ነው! የፊቱን ስሜትና የዓይኑን እንቅስቃሴ እየተረጎመ በሚተነትን የዘመነ ዊልቸሩ ላይ እጥፍጥፍ ብሎ ተቀምጦ ስለብላክ ሆል የሠራው ምርምር ይተረክለታል … ምነው ይቺን ዊልቸር ባገኘኋትና ሸጨ የዶሮ እርባታ በጀመርኩ እላለሁ በውስጤ!

ሌላ ቀን ሥራ ፍለጋ ስንከራተት ውዬ በድካም ወደቤት ስንከላወስ…አጎቴ ከኋላ ጠራኝ ‹‹አብርሃም …ጠብቀኝ አንዴ የማሳይህ አለኝ …›› ኮቱ እስኪውለበለብ እየገሰገሰ መጣና ቁና ቁና እየተነፈሰ፣ በእጁ የያዘውን የግል ጋዜጣ ነፋስ ጋር እየታገለ መንገድ ላይ ዘረጋጋው …‹‹ስኬታማ ሥራ የሠሩ የዓለማችን አስደናቂ የአካል ጉዳተኞች›› ከሚል ርእስ ሥር አንዷን እየጠቆመ …. ‹‹ይችን ሴት ታያታለህ ?….ይች ሴት…እ… ?ሁለት እጅ የላትም ….አዬህ … ! እጇን አጣጥፋ እንዳንተ እቤት ቁጭ አለች ?…አለች ወይ? ››
‹‹እጅ ከሌላት እንዴት እጇን አጣጥፋ ቁጭ ትላለች አጎቴ? ››
ጥያቄዬን እንዳልሰማ አለፈኝና ….
‹‹ምን እያረገች ነው ….?አንብብልኛ?! ›› ብሎ አፈጠጠብኝ፡፡ ጀሲካ የምትባል በእግሮቿ አውሮፕላን የምታበር ሴት ታሪክ ነበር…ጭራሽ ጋዜጣው ‹‹ብዙዎች እግርና እጅ እያላቸው ለሥራ በሰነፉበት ዘመን …ይች አሜሪካዊት አካል ጉዳተኛ ግን ››….ይላል ! ጸሐፊው አጎቴ መሰለኝ! እንዳቀረቀርኩ ወደቤት መንገዴን ልቀጥል ስል...

‹‹ቆይ! ይኼን ደሞ ተመልከት!›› አለና ከሥር ሌላ ፎቶ ጠቆመኝ …ይኼንኛው ሁለት እጅም፣ ሁለት እግርም የለውም …ኒኮላስ ጀምስ የሚባል አውስትራሊያዊ ነው ….አጎቴ አንዴ እኔን በትዝብት፣ አንዴ ደግሞ በአድናቆት ጋዜጣውን እያዬ …‹‹ ሥራ ከመያዝ አልፎ ሁለት ወርቅ የመሳሰሉ ልጆች ወልዷል …አዬህ? …እያት ሚስቱ ማማሯ … አንተ ሥራው እንኳን ቢቀር፣ ሙሉ አካል ይዘህ ደህና ሴት ጓደኛ አታደርግም! ዝም ብለህ ከዚች ከቦጋለች ልጅ ጋር ትጓተታለህ! …ይኼን የማሳይህ ሮጥ ሮጥ ብለህ ሥራ እንድትፈልግ ለማነቃቃት ነው ….ለሌላ አይደለም …››

ምርር አለኝ …‹‹ አጎቴ! …ለምንድነው አንዴ እግር አንዴ እጅ የሌላቸው ሰዎች እያመጣህ የምትነዘንዘኝ? …እዚህች አገር ላይኮ ደህና ዘመድ ካለህ ፣ እንኳን እግርና እጅ ጭንቅላት ባይኖርህ ራሱ ጥሩ ሥራ ታገኛለህ! ›› ብዬ አጎቴን በቆመበት ትቼው ወደኋላዬ ተመለስኩ፡፡

ከኋላ ድምፁ ይሰማኛል ‹‹እኔ እንድትነቃቃ ብዬ ነው አብርሃም …››

አሌክስ አብርሃም
89 views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 16:40:31 ዓ ባ ይ
ዓባይ የኔ ነው፣ የኔ ነው የኔ
ዓባይ ቅኔ ነው፣ ቅኔ ነው ቅኔ
የእናት ኢትዮጵያ፣ የአብራኳ ክፋይ
የሚፍለቀለቅ፣ ከአምባዎቿ ላይ
ዓባይ የኔ ነው፣ ህያው ታሪኬ
የተኳለበት፣ ኩራቴ መልኬ
------- ❶ --------
ከተራራው አምባ - ከእናት ሀገር ጡቶች፣
ያጋቱ ውሃዎች - የሚፈልቁ ምንጮች፣
ጣና ደረቷ ላይ - በፍቅር ተሽኳልለው፣
ከየሰርጣሰርጡ - ከጅረት አብረው
የሚፈሱት ወንዞች - በአንድነት ተጣምረው፣
የጦቢያ ወዘና - የኔው መልክ ናቸው።
---------- ❷ ---------
ዓባይ - መልከኛ ነው
ዓባይ - የሀገር መስታወት
ዓባይ - የሥልጣኔ ምንጭ
ዓባይ - የብርሃን ነው ጅረት
ዓባይ - ፀጋዋ ነው
ዓባይ - የእናት ሀገር ውበት
ዓባይ - የብርታቷ መክሊት
ዓባይ - የፅናት መቀነት
--------- ❸ -----
ውሃ ብቻ አይደለም - ፈሳሽ ወራጅ ውሃ
የሀገር ምሶሶ ነው - የትውልድ አምሃ
የሀገር መስታወት ነው - የመልኳ መታያ
የፀጋ ልብሷ ነው - የእምዬ ኢትዮጵያ
-----------
ዓባይ የኔ ነው - የኔ ነው የኔ
ዓባይ ቅኔ ነው - ቅኔ ነው ቅኔ
የእናት ኢትዮጵያ - የአብራኳ ክፋይ
የሚፍለቀለቅ - ከአምባዎቿ ላይ
ዓባይ የኔ ነው - ህያው ታሪኬ
የተኳለበት - ኩራቴ መልኬ
------- ❶ -----
አኮቦና ባሮ - ዳቡስ እና ደንድር
ከጉያዋ ፈልቆ - አባይና ሆኖ ሲሰምር
በውሃው መስክ ላይ - የሚያንፀባርቀው
ኢትዮጵያዊነቱን - ሀበሻ መልኩን ነው
በውሃው ገፅ ላይ - የሚያንፀባርቀው
ጥቁር ማንነቴን - ሀበሻ መልኬን ነው
--------- ❷ ---------
ዓባይ - መልከኛ ነው
ዓባይ - የሀገር መስታወት
ዓባይ - የሥልጣኔ ምንጭ
ዓባይ - የብርሃን ነው ጅረት
ዓባይ - ፀጋዋ ነው
ዓባይ - የእናት ሀገር ውበት
ዓባይ - የብርታቷ መክሊት
ዓባይ - የፅናት መቀነት
-------- ❸ ----
ውሃ ብቻ አይደለም - አባይ ገራገሩ
ሲፈስ የሚያስቀና - ላምባ ነው ለሀገሩ
ከነዳጅ የሚልቅ - ቅኔ ነው ሚስጢሩ፣
አንድም የሚጠጣ - አንድም ማሾ ሆኖ - ያበራል ላገሩ፤
_
ዓባይ የኔ ነው - የኔ ነው የኔ
ዓባይ ቅኔ ነው - ቅኔ ነው ቅኔ
የእናት ኢትዮጵያ - የአብራኳ ክፋይ
የሚፍለቀለቅ - ከአምባዎቿ ላይ
ዓባይ የኔ ነው - ህያው ታሪኬ
የተኳለበት - ኩራቴ መልኬ

ግጥም፦ ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን
ዜማ፦ ቢንያም ከበደ

የዓባይ ልጆች ቴቪ
#የዓባይልጅ

#HornOfAfrica #GERD
100 views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 13:53:02 የህይወት መዳረሻችንን ዲዛይን የምናደርገው እኛው ነን፣ ደራሲው እኛ ነን፤ ታሪኩን የምንፅፈው እኛው ነን። የመፃፊያ ብዕሩ በእጃችን ነው፤ በህይወታችን የምናገኘውም ነገር ምርጫችንን ነው! የሊዛ ኒኮልስ አባባል ነው በራሷ አባባል ያለችውን ልንገራችሁ 'You are the designer of your destiny. You are the author. You write the story. The pen is in your hand, and the outcome is whatever you choose.'
ታዲያ አሁን ያለንበት ሁኔታ የመረጥነው ነው? ደስተኛ ነን? ካልሆንን መጀመሪያ ምርጫችን ምን እንሆነ አስበን እንወስን...በህይወት ከሚንፈተንባቸው ነገሮች አንዱ ማመንታት ነው...ላድርገው አላድርገው፣ ልጀምረው አልጀምረው እያልን ማመንታት የሁልጊዜ ልማዳችን ከሆነ ለመወሰን አሁኑኑ በቁርጠኝነት ይነሱ/ይወስኑ!!!!
92 views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 10:30:12 ለመንግሥት ሠራተኞች የሚሰጥ የወሊድ ፈቃድ
==================
ለአንድ የመንግስት ሰራተኛ የተለያዩ ዕረፍት ዓይነቶች ያሉ ስሆን በፌደራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010” አንቀጽ 43 ላይ የተደነገገው የወሊድ ፈቃድ ነው።
ነፍሰጡር የሆነች የመንግሥት ሠራተኛ፣ ከእርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ ሐኪም በሚያዘው መሠረት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣታል፤
1. ከመውለዷ በፊት ዕረፍት እንድታደርግ ሐኪም ካዘዘ ደመወዝ የሚከፈልበት ዕረፍት ይሰጣታል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተው ፈቃድ እንደ ህመም ፈቃድ አይቆጠርም፡፡
3. ነፍሰጡር የሆነች የመንግሥት ሠራተኛ መውለጃዋ ሲደርስ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት 30 ተከታታይ ቀናት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ፣ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 90 ተከታታይ ቀናት፣ በአጠቃላይ 120 ተከታታይ ቀናት ደመወዝ የሚከፈልበት የወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት ሠራተኛዋ የተሰጣት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከማለቁ በፊት ከወለደች ያልተጠቀመችበትን ቀሪ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወለደች በኋላ እንድትጠቀምበት ይደረጋል፡፡
5. ሠራተኛዋ የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ ያልወለደች እንደሆነ እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት የምትቆይበት ዕረፍት በበጀት ዓመቱ ካላት የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ወይም በበጀት ዓመቱ የዓመት ፈቃድ የሌላት እንደሆነ ከሚቀጥለው የበጀት ዓመት የዕረፍት ፈቃዷ ይተካል፡፡
6. ሠራተኛዋ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) የተወሰነውን የወሊድ ፈቃድ ከጨረሰች በኋላ ብትታመምና ተጨማሪ ፈቃድ የሚያስፈልጋት መሆኑ በሀኪም ከተረጋገጠ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 43(1) በተደነገገው መሠረት የሕመም ፈቃድ መውሰድ ትችላለች፡፡
7. ማንኛዋም ስድስት ወር የሞላት ነፍሰጡር የሆነች የመንግስት ሠራተኛ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከመውሰዷ በፊት ጽንሱ የተቋረጠባት ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የህክምና ማስረጃ ስታቀርብ የ60 ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
8. የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወሰደች በኋላ የጽንስ መቋረጥ ካጋጠማት የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃዷ ተቋርጦ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) የተመለከተው የ90 ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
9. ከሦስት እስከ ስድስት ወር ባለው የእርግዝና ጊዜ ውስጥ የፅንስ መቋረጥ ያጋጠማት የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ የሚከፈልበት 30 ተከታታይ ቀን ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
10. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ የትዳር ጓደኛው ስትወልድ ደመወዝ የሚከፈልበት 10 የሥራ ቀን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
103 views07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ