Get Mystery Box with random crypto!

አላማው በዚህ ሰበብ አመፅ መቀስቀስም ጭምር ነበር፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ 'በኮንዶሚኒየም የገጠ | ዜና ቅምሻ

አላማው በዚህ ሰበብ አመፅ መቀስቀስም ጭምር ነበር፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"በኮንዶሚኒየም የገጠመን ነገር አሳፋሪ ነው፡፡ ችግሩ የሶፍትዌር ብቻ አይደለም ፤ ሶፍትዌር እኮ ከባንክ ቁጠባ ያቋረጠ ሰው በድጋሚ እንዲካተት አያደርግም፡፡

ሶፍትዌር 100 ሺህ የሚጠጋ ተጨማሪ ዳታ እንዴት ይዞ ይመጣል?? ከፍተኛ ዳታ መደለዝ መጨመር ነው የተደረገው፡፡

አላማው ሰዎቹ ቤት እንዲያገኙ ነው ወይንስ ቁጣ ለመቀስቀስ??

ምክንያቱም ኮንዶሚኒየም አገኘህ የተባለው ሰው ባንክ አዋውሉኝ ብሎ ቢሄድ ባንክ አያዋውለውም፤ ቁጠባ ስላላደረገ ወይም ስላቋረጠ፡፤ ጥቂት ሰው ቢሆን በግለሰብ መመሳጠር ምናልባት ሊዋዋል ይችላል፡፡ ይሄ ሁሉ ሰው ግን ሊዋዋል አይችልም፡፡ እና አላማው ቤት መስጠት ብቻ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ??

ሃሳቡ በዚህ ሰበብ አመፅ መቀስቀስም ጭምር ነበር። የኮንዶሚኒየም ታሪክ መንግስትና ህዝብ እንደማይተማመን የሚያደርግ ብዙ የኋላ ታሪኮች አሉ፡:

በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩንቨርሲቲ አስጠንተን አረጋግጠናል እሱን፡፡ አብዛኛው ከሰዎች ጋር የሚያያዝ እንጂ የሙያ ጉዳይ አድርገን ሰበብ የምናደርገው አድርገን አላየነውም፡፡

የሚያለማ የነበረው ባለሙያ ዳታውን ቀድሞ እንዳላገኘው ነበር ይሄ አመራር የሚያውቀው፡፡ ያ ሁሉ ታዛቢና ትልልቅ ሰዎች ባሉበት ሙከራ ተደረገ፡፡ ለዚህም ነው አሁን ዳታውና ሶፍትዌሩ ስለተገናኘ ይታሸግ ተብሎ የታሸገው፡፡ ቀድሞ እንደተገናኘ ቢታወቅ ኖሮ ምን መታሸግ ያስፈልግ ነበር፡፡"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምክር ቤት ጉባኤ ላይ ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ