Get Mystery Box with random crypto!

በሀገር ውስጥ የዘረ-መል ምርመራ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጀመር ተገለጸ በሀገር ውስጥ የዘረ-መል | አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

በሀገር ውስጥ የዘረ-መል ምርመራ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጀመር ተገለጸ

በሀገር ውስጥ የዘረ-መል (ዲ ኤን ኤ) ምርመራ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እንደገለጹት ፥ አዳዲስ የፎረንሲክ ምርመራ ማሽኖችን ተቋሙ ወደ ሀገር አስገብቶ ጥቅም ላይ እያዋለ ነው።

በአስር ዓመቱ ስትራቴጂክ ዕቅዱ ከአፍሪካ ምርጥ አምስት የፖሊስ ተቋማት አንዱ ሊሆን በለውጥ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሰራሮቹን በቴክኖሎጂ እያዘመነ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም ከዚህ ቀደም ወደ ሌላ ሀገራት ተልኮ ይደረግ የነበረው የዲ ኤንኤ ምርመራ ከአንድ ወር በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ ይደረጋል ብለዋል።

ከቴክኖሎጂ ባለፈ ፖሊስ ውጤታማ ስራ ለመስራት ያስችለው ዘንድ አዳዲስ አደረጃጀቶች ማዋቀሩን ኮሚሽነር ጄነራሉ ገልጸዋል።

አዳዲሶቹ አደረጃጀቶች እያደገ የመጣውን የአየር እና የየብስ ትራንስፖርት ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ናቸው ተብሎላቸዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ኢንዱስትሪዎችንና ዩኒቨርሲቲዎችን ትኩረት አድርገው መዋቀራቸውን አስታውቀዋል።

አዳዲሶቹ አደረጃጀቶች የአቪየሽን ፖሊስ፣ የምድር ባቡር ፖሊስ፣ የዩኒቨርሲቲ ደህንነት ፖሊስ እንዲሁም በኢንዱስትሪ እና ቱሪዝም ላይ ትኩረት አድርጎ የሚከታተል የፖሊስ ክፍሎች ናቸው።

@Addis_Tv