Get Mystery Box with random crypto!

የመንግሥት ቃል አቀባይ ለገሠ ቱሉ የአሜሪካው ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ ዕርዳታ | አዲስ ሪፖርተር - NEWS

የመንግሥት ቃል አቀባይ ለገሠ ቱሉ የአሜሪካው ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ ዕርዳታ መስጠት ማቋረጡ "ፖለቲካዊ ውሳኔ" ነው በማለት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ መናገራቸውን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ለገሠ የድርጅቱ "የጅምላ ውሳኔ" በመንግሥት ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጠው፣ ውሳኔው ሰብዓዊ ገጽታ የለውም ማለታቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። ድርጅቱ በምግብ ዕርዳታ ዝርፊያ ዙሪያ በመገናኛ ብዙኀን በኩል ባወጣው መረጃ፣ የፌደራል፣ የክልልና መንግሥታትንና የመከላከያ ሠራዊትን ስም አጉድፏል ሲሉ ቃል አቀባዩ ወቅሰዋል ተብሏል። መንግሥትና ድርጅቱ በምግብ ዕርዳታ ዝርፊያው ላይ የጋራ ምርመራ ለማድረግ ከትናንት በስቲያ መስማማታቸው ይታወሳል(ዋዜማ)።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter