Get Mystery Box with random crypto!

addicted to holy spirit

የቴሌግራም ቻናል አርማ addictedtoholyspirit — addicted to holy spirit A
የቴሌግራም ቻናል አርማ addictedtoholyspirit — addicted to holy spirit
የሰርጥ አድራሻ: @addictedtoholyspirit
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 108
የሰርጥ መግለጫ

addicted to holy spirit

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-12 07:51:35
63 viewsAbigû, 04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 13:58:19 ክርስቶስ የተወለደው የሚሞት፣ የሚደማ፣ የሚቦጨቅ ስጋ ለመልበስ ነው ውልደትን enjoy እንድናደርግ የሚያደርገን ሊሞት ስለሆነ ነው መወለድ አንድ ደስታ አለው ከሁሉም በላይ የሚያስደስተው ግን የተወለደበት ሰው የሆነበት ምክንያቱ እኛን ከእርሱ ጋር ለማኖር መሆኑ ነው በክርስቶስ ልደት ውስጥ የዘላለም ውልደት ስላየንበት ነው enjoy የምናደርገው መሲሁ ኢየሱስ ተወልዶአል
123 viewsAbigû, 10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-25 22:56:22 እንዴት አላችሁ
ዛሬ አንድ ስሰማው በጣም ያስደነቀኝን እና ያስገረመኝን ታሪክ ልንገራችሁ

በአንድ አገር ውስጥ የሚኖሩ አንድ የተለመደ ስርዓት ያላቸው ህዝቦች ይኖሩ ነበር። በዚህ ስርዓት መሰረት አንድ ልጅ ወይም ወጣት ለአቅመ አዳም መድረሱን ለማረጋገጥ እና ከዚያም እንደ አዋቂ እንዲታይ አንድ ለሊት ብቻውን ጫካ ውስጥ እንዲያድር ይደረግ ነበር። ያቺን ለሊት ተቋቁሞ ማለፍ ከቻለ የትልቅነት ማዕረግን ይገኛል። እናም በዚህ ስርዓት ውስጥ ማለፍ የነበረበት አንድ ወጣት ተራው ይደርሳል ። እንደተለመዱው ዐይኑን ታስሮ በዚያ ጨለማ ወደ ጫካ አባቱ ይዞት ይሄዳል። እናም በአንድ ዛፍ ግንድ ስር እጁን እና እግሩን በገመድ ያስረው ጀመር። ገና ታስሮ ሳይጨርስ እንኳን የተለያየ የአውሬ ድምፅ ይሰማው ነበር። በጣም ፈራ ይንቀጠቀጥ ጀመር ከፍርሀቱ የተነሳ ሰውነቱ በላብ ተጠመቀ ነገር ግን ላሰበው ክብር ለመብቃት የግድ ያ ለሊት ሲነጋ ነው የታሰረው ዐይኑን እና እጁን መፍታት የሚችለው ። አንበሳ ሲያገሳ፣ ጅብ ሲጮህ እና እባብ በአጠገቡ እየተሳበ ሲያልፍ እየሰማ እንዲው እንደተሳቀቀ እያለቀሰ...... እይነጋ የለምና ነጋ።
የፀሀይዋ ብርሃን በታሰረው ዐይኑ ላይ ሲያርፍ ትልቅ ደስታ እና ኩራት ተሰማው ወዲያውም እጁን ቀጥሎም ዐይኑ ላይ ያለውን ጨርቅ መፍታተ ጀመረ ። ዐይኑን ሲገልጥ ግን ያልጠበቀውን ነገር ነበር የተመለከቱው የሆነ ሰው ጦር ይዞ አጠገቡ ቆሞ ነበር.... ይህም ሰው አባቱ ነበር ።ለካ በራሱ አልነበረም የተረፈው፣ ለካ ሊበሉት የነበሩትን አውሬዎች አባቱ ነበር የከለከለለት፣ ለካ አባቱ ጥሎት አልሄደም ነበር፣ ለካ እርሱ ማየት ተስኖት እንጂ አባቱ አጠገቡ ነበር ። አባቱም እነሆ ልጄ አለሁልህ ብሎ አቀፈው ።
እህት ወንድሞቼ በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳላችሁ አላውቅም ግን አንድ ነገር ልበላችሁ ዛሬን ማየት የቻልነው እግዚአብሔር ስለጠበቀን ነው እንጂ በራሳችን አይደለም እናም አሁንም በጭንቅ ብቻዬን ነኝ ላላችሁ እርሱ የናንተን ጥንካሬ እንጂ ክፉ አይሻምና አሁንም አጠገባችሁ ነው። ስለ መልካም አባትነቱ እግዚአብሔር ይመስገን ።
እዚህ ላይ አበቃሁ ተባረኩልኝ
@ addictedtoholyspirit
234 viewsAbigû, edited  19:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-14 21:36:02 ይፃፍልኝ amezing song

ይቀዳ መልዕክቴ ለትዉልድ ይለፍ
እንደምትረዳ እንደምታሳርፍ
ይፃፍልኝ ቃሌ ይተረክ ለሌላዉ
የሕይወት ቃል እንደሆንክ እንደምትበላ

ይቀዳ መልዕክቴ ለትዉልድ ይለፍ
አባት እንደምትሆን እንደምታሳርፍ
ይፃፍልኝ ቃሌ ይተረክ ለሌላዉ
የሕይወት ቃል እንደሆንክ እንደምትበላ

እንዳይደለ ተረት ተረት
እንዳየሁ በኔ ህይወት
እንዳይደለ ሰሞንኛ
እንደምትሆን ወዳጅ ቤተኛ

እንዳይደለ ተረት ተረት
እንዳየሁ በኔ ህይወት
እንዳይደለ ሰሞንኛ
እንደምትሆን የልብ ጓደኛ

ከልጅነቴ ጀምሮ በማውቀው
ኮልታፋ አንደበት በሚገባኝ
በራሴ ቋንቋ መርቶኛል ያንተ እረኝነት

ምክርህ ፍቅር አለበት ቁጣም ፍቅር አለበት
ማን ተወቀሰ ባንተ አድጎ?ጥጉነህ ያባትነት
ማንተሰደበ ባንተ አድጎ? ጥጉነህ ያባትነት

እንዳይደለ ተረት ተረት
እንዳየሁ በኔ ህይወት
እንዳይደለ ሰሞንኛ
እንደምትሆን ወዳጅ ቤተኛ


እስከዛሬ በተጓስኩት
በመጣሁት ሁሉ መንገድ
ከምዳስሰው ሰው ሁሉ ይልቅ
ህያውነህ አንተ በኔ ዘንድ
እስከዛሬ በተጓስኩት
በመጣሁት ሁሉ መንገድ
ከምጨብጠው ሰው ይልቅው
እርግጥ ነህ አንተ በኔ ዘንድ
ለማለት ያህል አልልም
ስላየውነው በዘመኔ
ለማበረታታት ለማጀገን ማን
ሊቆም እንዳንተ ለኔ?

HELINA DAWIT NEW SONG
ይፃፍልኝ amezing song
@yegetahayalan
108 viewsAbigû, 18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-28 15:24:44 ጉዳዩ መኖሪያህን ማወቁ ነው።

“ሽኮኮዎች ያልበረቱ ሕዝቦች ናቸው፥ ቤታቸውን ግን በቋጥኝ ድንጋይ ውስጥ ያደርጋሉ።”
— ምሳሌ 30፥26
“እንሽላሊት በእጅ ይያዛል፥ በነገሥታት ግቢ ግን ይኖራል።”
— ምሳሌ 30፥28

እዚህ ክፍል ላይ በጣም የሚገርሙኝ እነዚህ ጥቃቅን እስሶች ናቸው።

ሽኮኮ የሚኖሩት በህብረት ነው/ህዝብ/ ሆነው ማለት ነው፤ ነገር ግን ያልበረቱ ህዝቦች ናቸው። እነዚህ እንስሶች ጠቢብ ያደረጋቸው ነገር መኖሪያቸውን መምረጣቸው ነው። የሚኖሩት #በቋጥኝ ድንጋይ# ውስጥ ነው።

ወዳጄ አስተውል ብርቱ አለመሆንህ አያሳስብህ፤ ብርቱ አለመሆንህን አውቀህ መኖሪያህን #በቋጥኝ ድንጋይ# ውስጥ አድርግ። የኔ እና ያንተ የቋጥኝ ድንጋይ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሽኮኮዋ ከቋጥኝ ድንጋዩ የተነሳ አትፈራም፣ አትሰጋም፤ መተማመኛዋም ድንጋዩ ነው። እኔና አንተ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ስለሆንን ከምንሰማው ከምናየው ነገር ተነስተን አንናወጥም፣ አንፈራም፣ አንሰጋም። አሜን!!!

እንሽላሊት ራሷን የምትከላከልበት አቅም የላትም፤ በቀላሉ በእጅ የምትያዝ ናት። ነገር ግን ጠቢብ ናት ምክንያቱም አቅሟን አውቃ መኖሪያዋን #በነገስታት ግቢ# ውስጥ አረገች። ወዳጄ እንሽላሊቷ ምንም ያለመሆኗ ምስጥር ከራሷ ብቃት አይደለም ከመኖሪያዋ አንጂ።

ወዳጄ በአለም ላይ ምንም አይነት ነገር ሊፈጠር ይችላል የማንፈራው፣ የማንሰጋው ሰው ስላልሆንን አይደለም መኖሪያችንን መምረጣችን ነው። መኖሪያችን #የዘላለም አምላክ እግዚአብሔር# ነው።

ወንድሞቼ አንድ ነገር ላሳስባችሁ ከሁለቱ ጠቢብ ጥቃቅን እንስሶች አንድ ነገር ተማሩ በመረጣችሁት መሮሪያ መታመን ይሁንላቹ። መኖሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። አሜን።
@addictedtoholyspirit
126 viewsAbigû, edited  12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-22 05:32:46
https://t.me/heyawyeegezeyabehermenegest
94 viewsF@$¡k@ G€b€¥€hµ, 02:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-07 11:09:32 ወዳጄ ሆይ በምን ሰከርክ?
************************
አብዝተህ የጠጣኸው ነገር ያሰክርሀል.....ትንገዳገዳለህ.......ከቁጥጥርህ ውጭ ሆነህ ያሰከረህ ይቆጣጠርሀል!!

የምትሰክርለት አብዝተህ ለጠጣኸው ጉዳይ ነው!!

ቀንህን የምታሳልፈው ምን እየጠጣህ ነው?

ያልጠጣኸውን መስከር የጠጣኸውን አለመስከር አትችልም!!

አብዝቶ ፖለቲካ የጠጣ ሰው ሰክሮ የሚንገዳገደው ለፖለቲካ ነው!!

አብዝቶ ኳስ የጠጣ ሰው ሰክሮ የሚንገዳገደው ለኳስ ነው!!

አብዝቶ ጥላቻ የተጋተ ሰው ሰክሮ የሚንገዳገደው ለጥላቻ ነው!!

አብዝቶ ክርስቶስን የጠጣ ሰው ሰክሮ የሚንገዳገደው ለክርስቶስ ነው!!

ወዳጄ አብዝተህ የምትጠጣው ምንድን ነው?

ስትሰክር የምትተፋው የጠጣኸውን ነው........በፖለቲካ ሰክረህ ያገኘኸው ሰው ሁሉ ላይ ፖለቲካ እንጂ ኢየሱስ ካፍህ አይወጣም.........በክርስቶስ ስትሰክር ያገኘኸው ሰው ሁሉ ላይ ክርስቶስ እንጂ ጥላቻ ካፍህ አይወጣም!!

የሰከርከው በምንድን ነው?

በክርስቶስ ስትሰክር ስካር ራሱ ያምርብሀል? መንፈስ ሞልቶብህ የምትሰክረው ስካር ለሕይወት የሆነ ትርፋማ ስካር ነው!!

የሰከርከው በክርስቶስ ካልሆነ ሰክረሀል ሳይሆን ከስረሀል ነው የሚባለው!!

እናልህ ወዳጄ ሰክረሀል ወይስ ከስረሀል?


@addictedtoholyspirit
115 viewsAbigû, 08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-23 19:05:09 bezeh mezmure resersu
tebarkulg wedachewalwe
@addictedtoholyspirit
109 viewsAbigû, edited  16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-21 10:22:52
“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 6፥2
https://t.me/heyawyeegezeyabehermenegest
114 viewsF@$¡k@ G€b€¥€hµ, 07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-15 22:44:38 የማያምን አማኝ
*****************
የችግሩን ባህር እንደቀልድ ከፍለኸው
ፊልም በሚመስል ተራምዶ እያለፈው
ተርቢያለሁ ቢልህ መና ብትመግበው
ተጠማሁኝ ቢልህ ከአለት ብታጠጣው
እግሩ እየረዘመ ጫማዎች ባያጥሩት
ሰውነቱ ሲገዝፍ ልብሶቹ ባይጠቡት
ጠላቶቹን ሁሉ ብታሸንፍለት
ፅልመቱን አንስተህ ጎህ ብትቀድለት
"የማያምን አማኝ"
እንቅፋት እያየ በልቡ ያምፃል
ለተድላ ቢታጭም ባርነት ይመኛል።

Share &join
@eyobapoem

#ኢዮብ ጥላሁን።
113 viewsAbigû, 19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ