Get Mystery Box with random crypto!

ምስለ አድባራት ወገዳማት

የቴሌግራም ቻናል አርማ adbaratwegedamat — ምስለ አድባራት ወገዳማት
የቴሌግራም ቻናል አርማ adbaratwegedamat — ምስለ አድባራት ወገዳማት
የሰርጥ አድራሻ: @adbaratwegedamat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.32K
የሰርጥ መግለጫ

"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን" "ስለ ቅዱሳን እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል" ሊቁ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 21:11:53 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 1
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






39 views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 23:20:38 ክብርት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስርዓትሽ ልዩ
እኔ ኦርቶዶክስ የሆንኩት ተመርጬ እንጂ መርጬ አይደለም የሚል ብቻ ወደዚህ ቻናል ይግባ ምክንያቱም ቻናሉ ስሙ ራሱ ናታኒም ስለሆነ

ናታኒም ማለት ደግሞ የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነው
እርሶም ወደዚህ ቻናል በመግባት
ኦርቶዶክሳዊ ስርዓት የጠበቁኪነጥበብ
መዝሙር
ትምህርት በዕንቁ መምህራን
እያሳቁ ሚያስተምሩ ምክረ አበው
መንፈሳዊ
ግጥሞች
መነበናብ
ኦርቶዶክሳዊ ስም ትርጉሞች


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲   █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ናታኒም TUBE oN YOUTUBE
በማርያም ሰብስክራይቭ ያድርጉን






20 views20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 15:04:20
2.5K views12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 15:03:48 #በተድባበ_ማርያም_ብቻ_የሚገኙ_ቅርሶች፦
ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ለእመቤታችን ከሳላቸውና ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ከ4ቱ ምስለ ፍቁር ወልዳ ስዕለ አድኅኖዎች ውስጥ አንዷ ስዕለ አድኅኖ ባለ 3 ተከፍች የገበታ ስዕልና ጥንታዊና ስነ ጥበባዊ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡
የንጉሥ ዳዊት ወንበር፣
ሥዕርተ ሐና (የእመቤታችን እናት የእናታችን የቅድስት ሐና ፀጉር) በገዳሙ ይገኛል። ይህ ጸጉር የተቀመጠበት የሽክላ ገንቦ እጅግ ጥንታዊና በስነ ጥበባዊ ይዘቱ የሚያስገርም ትእይንት ይፈጥራል።
በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ወንድማማቾቹ ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሐ ያነጹት ስውር ቤተ መቅደስ፣
አዛዥ ጌራና አዘዥ ዘራጉኤል በእጃቸው ያመለከቱት ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም ያስተማሩበት ድጓ፣
የጥንታዊያን ነገሥታትና ጳጳሳት ከወርቅና ከብር የተሰሩ በወቅቱም ለገዳሟ የተበረከቱ የክብር አልባሳትና የነገሥታት ዘውድ እንድሁም አጼ ገላውዴዎስ ታቦተ ተድባበ ማርያምን ይዘው ዘምተው አላዊው ግራኝ አህመድን ሲያሸንፉት ከአላዊው ግራኝ የማረኳቸው አልባሳትና አንድ ሰው ተንገዳግዶ የሚያነሳው የግራኝ የበቅሎው ቃጪል
የበግ ምስልና የተቁለመለመ የበግ ቀንድ ያለበት መስቀል በዚያ ይገኛል፡፡ የዚህ መስቀል ብርሀን የሚያስገርምና ዓይንን የሚያንፀባርቅ ሲሆን ከምን አይነት ማዕድን እንደተሰራ አይታወቅም፡፡
ከጥንታዊያን ነገሥታትም መካከል ዐፄ ካሌብ ወደ ደቡብ አረቢያ የናግራንን ክርስቲያኖች ለመርዳት ሲዘምቱ ፓትርያርክ ዘሙሴ እሱም የኦየሩሳሌምን ገዳም ያቀናና በመጨረሻም በአባ ጴንጠሌዎን ገዳም ገብቶ ያረፈ አባት ጋር ዘምተው ድል አድርገው ሲመለሱ ይዘው የሄዱትን ጋሻ በስዕለት ለተድባባ ማርያም አስገብተውት በቦታው ይገኛል፡፡
የዕብራይስጥ ሲኖዶስና የአረማይክ ቅዳሴ እግዚእ በቦታው ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ገዳም ከ1000 ያላነሱ የብራና ጥንታዊያን መጻሕፍት ይገኛሉ፤ እነዚህም መጻህፍት ክፊሎቹ በጥንታዊት የአክሱም ዘመን መንግስት የተጻፉ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግም በመካከለኛው ዘመን የተጻፉ ናቸው፡፡
በአረማክ ቋንቋ የተጻፉ የሰሌዳ መጻሕፍት፣
በዐረብኛና በግእዝ የተጻፉ በርካታ ጥንታዊያን መጻሕፍት፣
ወንጌል ዘወርቅ እየተባለ የሚጠራ ትልቅ የወርቅ ጉብጉብታ ያለበት የወንጌል መጽሐፍ ቅዱስ፣
ገድለ ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ፣
ገድለ አዳም ከታላቅነቱ የተነሳ ሁለት ሰው ከቀኝ ከግራ ሆኖ የሚዘው ባለ ገበታ የብራና መጽሐፍ፣ እና ሌሎች በርካታ ጥንታዊያን መጻሕፍት በቅርስነት ተመዝግበው በተድባበ ማርያም የሚገኙ የመንፈሳዊ እሴት ማንጸባረቂያዎች ናቸው። በተጨማሪም ገዳሟ ሌሎችንም በርካታ ቅርሶችን በክብር ጠብቃ ይዛለች።

#መስቀል_በተድባበ_ማርያም፦
በርካታ ጥንታዊ የእጅና የመጾር መስቀል ይገኛሉ። ከእነዚህም መካከል፦
የመጀመሪያው የኢትዮጵያዊ ጳጳስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የቀደሰበትና ለተድባበ ማርያም የሰጡት "ነዋ በግዑ" የእጅ መስቀል እና "ዘይቄድስ ኩሎ" የተባለ ቅብዓ ሜሮን፣
የመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ መስቀል፣
የእጨጌ ዮሐንስ በትረ ሆሣዕና እና የእጅ መስቀል፣
የአቡነ አኖሪዎስ የእጅ መስቀል፣
የአቡነ ቄርሎስ የእጅ መስቀልና ሌሎች ከወርቅ የተሰሩ ጥንታውያን መስቀሎች ናቸው፡፡

#በገዳሟ_ከሚገኙ_አጽመ_ቅዱሳን_መካከል፦
ሄሮድስ የጨፈጨፋቸው ሕጻናት ዓጽም በከፊል፣
የቅዱስ ጊዮርጊስ አውራ ጣት
በአጠቃላይ የ28 ሰማእታት ዓጽም የሚገኝ ሲሆን እንዲሁም በልዩ ስፍራ የሚገኘው መካነ መቃብር የዐፄ ገላውዴዎስን ጨምሮ የ6 ነገሥታትና የ4 እጨጌዎች ተሰብስቦ ይገኛል፡፡

ከ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ እሰከ 11ኛው ድረስ የጨለማው ዘመን በመባል ይታወቃል፡፡ ይህም የግእዝ ሥነ ጽሁፍ የተዳከመበት ዮዲት ከተከታዮቿ ጋር በመሆን ባደረሰችው ወረራ ሰነ ጽሁፍ የጠፉበት የትርጉም ስራዎች እንደቆሙ ተደረገበት ወቅት ነበር፡፡

ከ9-15ኛው ክፍለ ዘመን በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን 40 ዓመታት መሉ ቤተ ክርስቲያንን ስታቃጥል መጸህፍትንና ሌሎችንም የቤተ ክርስትያን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ ተደምሰሱ፡፡ አያሌ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት (ካህናት) አብረው ተቃጠሉ፡፡ በዚህም ጊዜ በኢትዮጵያ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕጅጉ ተዳክሞ ነበር። ነገር ግን በዚህች ጥንታዊት ገዳም ምንም አይነት ወረራ አልደረሰባትም።

በ15ኛው ክፍለ ዘመንም ግራኝ የተነሳበት በመሆኑ ቱርክ እየተላላከ ባስመጣው መሣሪያና በድብቅ ያስለጠነውን ወታደር አሳልፎ ኢትዮጵያን መውረር ሲጀምር 15 ዓመት ያህል ያለማቋረጥ በኢትዮጵያ ላይ የቱርክ ጥይት እንደ እሳት ሲነድ ከዮዲት ጉዲት ወራራ ተርፈው የቀሩና ከእርሷም በኋላ የተተኩት የቤተክርስቲያን ቅርሶች በግራኝ ወራራ ጨርሰው ሲወድሙ የግራኝ ወራራ በቤተክርስቲያንና በምዕመናን ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያስከትል አያሌ ገዳማትና አድባራት ሲቃጠሉና ሲመዘበሩ ይህቺ ታላቅ የታሪክና የቅርስ ባለቤት የሆነችው ርእሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ምንም አይነት ቃጠሎና የቅርስ ዝርፊያ አልደረሰባትም፡፡

ከዚህም አልፎ በአጼ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት ካቶሊካዊያን በየገዳማቱና በየአድባራቱ እንዲሁም በየቤቱና በየለቅሶው ቤት በየገበያው እየዘሩ የካቶሊክን ሃይማኖት ለማስፋፋት ሲጥሩ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ዓጽም ካረፈበት እየወጣ መቃጠል ሲጀምር ብዙ ካህናትና መነኮሳት ሊቃውንትና ምእመናን ልጅ አዋቂ ሳይባል የተዋህዶ ሃይማኖት ልጆች የሆኑ ሁሉ ባሉበት እየታደኑ አሰቃቂ ድርጊት ሲፈጸምባቸው የርእሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ሊቃውንትና ካህናት መነኮሳት ግን እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ በፆምና በፀሎት ፀንተው መከራውንና ችግሩን በመቋቋም ተዋህዶ ሃይማኖታቸውን አቅንተው እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ታሪካቸውንና ቅርሳቸውን በመጠበቅ ይገኛሉ፡፡

ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት እንዲሁም ምእመናንና ምእመናት ሁላችሁም ይህንን አስደናቂ የሆነውን የርእሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ታሪክ አንብቦ (ሰምቶ) በመረዳት ልዑልና ቅዱስ እግዚአብሔር ፍቅዶላቸሁ ከያላችሁበት ወደ ቦታዋ ድረስ በመሄድ በረከት እንድታገኙ አደራችን የፀና ነው፡፡
☞ ምንጭ ማህበረ ፊልጶስ ወአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
1.8K views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 15:02:24
819 views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 16:42:41 ###ታላቅ የመንፈሳዊ ጉባኤ ጥሪ ፦
እሑድ: ግንቦት 7 :2014 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ

አዘጋጅ:- በኢ/ኣ/ተ/ቤ/ክ/በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ አንድነት ገዳም።

ቦታ:-በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሁለገብ አዳራሽ።

ስለ ገዳሙ አጭር መግለጫ
1)የቦታው ቃልኪዳን
* "ቦታህን የረገጠውን፣በአማላጅነትህ የተማፀነውን ኃጢአቱን በንሰሓ እስከሚያስወግድ ድረስ እድሜ ሰጥቼ እጠቡቀዋለሁ"
* "ከኢየሩሳሌም አምጥተህ በአዋሐድከው አፈርና ውኃ አምነው የተጠመቁትንና የተቀቡትን እየሩሳሌም እንደደረሱና በዮርዳኖስ ውኃ እንደ ተጠመቁ እቆጥርላቸዋለሁ።

2)አቡነ ዜና ማርቆስ ተጋድሏቸውን ፈጽመው በ14ዐ ዓመታቸው ታኅሣሥ 3ቀን በዚሁ ገዳም አርፈዋል።

3)አቡነ ተክለሃይማኖትን ተከትለው የሔዱ የደብረ ብሥራት ዛፎች፣እንጨቶችና ድንጊያዎች ከወንድሜ አባ ዜናማርቆስ ገዳም አትሔዱም የተባሉት እዛው በ ደብረ ብሥራት ይገኛሉ።

4)ማኀሌተ ጽጌ የተደረሰበት ቅዱስ ሥፍራ ነው።

5)የተሰነጠቀ ድንጋይ የአጣብቂኝ ዋሻ።

6)የገዳሙ በረከቶች
*ከሰማይ የወረደላቸው መስቀል።

*የዓመት ቡኮ(የ 464 ዓመት ቡኮ):- በግራኝ ወረራ ጊዜ ተሰደው የነበሩት የገዳሙ አባቶች ከ 27 ዓመት በኋላ በተመለሱ ጊዜ ያኔ ትተውት የሔዱት ሊጥ የእለት ሥንዴ ብኮ ሆኖ ሳይበላሽና ሳይኮመጥጥ አግኝተው ተመገቡት።ይህንንም እስከ ዛሬ ድረስ በመተላለፍ ለገዳሙ በረከት ሆኖ ይታደላል።

*የመቃብራቸው አፈር፦ብዙ ተአምራትን ያደረገና ሙት ያስነሳ በገዳሙ የሚታደል በረከት ነው።

*አጸደ ፂማቸው፤ ፈዋሹ ጸበላቸው፤እና ሌሎች ብዙ በረከቶች በገዳሙ ይገኛሉ።

እርሶም በዚህ ጻድቁን አቡነ ዜናማርቆስንእና ገዳማቸውን ደብረ ብሥራትን በሚያስተዋዉቅ ታላቅና ታሪካዊ መርሐግብር ላይ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

በጉባኤው ላይ የገዳሙ በረከቶች የሚታደሉ ይሆናል።

የጻድቁ አባታችን አቡነ ዜናማርቆስ ረድኤትና በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን።አሜን!!!

ለበለጠ መረጃ፦0921325839
0940852119
0911636177
896 views13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 17:08:32 Channel photo updated
14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 07:24:27
1.2K viewsNatnael Jordan, 04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 08:01:33
እንኳን ለአቡነ ፄዋ ለጽድቅ ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። ወር በገባ በ29 መታሰቢያቸው ነው
1.2K viewsNatnael Jordan, 05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 08:01:23
የአቡነ ፄዋ ለጽድቅ ቤተ ክርስቲያን: ቤተልሔም
1.1K viewsNatnael Jordan, 05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ