Get Mystery Box with random crypto!

👑 አዳም ረታ 👑

የቴሌግራም ቻናል አርማ adamureta — 👑 አዳም ረታ 👑 አ
የቴሌግራም ቻናል አርማ adamureta — 👑 አዳም ረታ 👑
የሰርጥ አድራሻ: @adamureta
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 591
የሰርጥ መግለጫ

ቀንዎን ያሳምሩ
👉የአዳም ረታ እና ሌሎችም እውቅ ደራሲያን ስራዎች
👉ግጥሞች
👉የአማርኛ መፅሀፍት በ pdf
👉 አዝናኝ እና ቁምነገር አዘል ፅሁፎች
👉ሙዚቃዎች እና ሌሎችም የምትፈልጓቸውን አንድ ላይ በ አዳም ረታ ያግኙ።
👉 የመፃህፍት ጥቆማ
@AdamuReta
@AdamuReta
@AdamuReta
For cross promotion contact
@isrik
@isrik

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

3

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-01 09:07:33 አንዳንድ ነገሮች
(በእውቀቱ ስዩም)
ፓስተር ዮናታን “ መልካም ወጣት “ የሚል ስልጠና በመስጠቱ የምትናደዱ ሰዎች ፥ ለምን እናንተ “ መልካም ሽማግሌ” የሚል ስልጠና ጀምራችሁ አትሸቅሉም? እኔና ዮናታን የመጀመርያዎቹ ተመዝጋቢዎች እንደምንሆን ተወዲሁ ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ፡ ፡
ዘግይቼም ቢሆን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንኩዋን ደስ ያለህ ማለት እፈልጋለሁ፤ አንዳንዴ በደስታ ስትሆኑ ብዙ ነገር አይታችሁ ባላየ ታሳልፋላችሁ፤ አትሌቶቻችን ድል ያደረጉ ቀን እጅግ ከመደሰታችን የተነሳ “ እኛም ኮራን “ እሚለውን ዝማሬ እስከመጨረሻው ታግሰን እንሰማዋለን፤
በቀደም እዚህ በረንዳ ላይ ቁጭ ብለን እንቀመቅማለን፤ ከመካከላችን አንዱ፥
“ ትግሬዎች በስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ ያላገኙትን የሩጫ ድል እንዴት ሊያስታቅፉን ቻሉ” የሚል ጥያቄ ጠየቀ፤
የምታስተናግደን ሴት፤ የሰላም ተስፋየን ቅርጽ እና የፍርያት የማነን ፊት አስተባብራ የያዘች ቆንጅየ ልጅ ስለሆነች ፥እስዋን ኢምፕረስ ለማድረግ እየተጭዋጩዋህን እየተሻማን ምላሻችንን አቀረብን፤
አንድ “ መልካም ሽማግሌ” ያቀረቡትን ምላሽ ከታች አስቀምጨዋለሁ::
“ የትግራይ ሰው አትሌቲክስ ከጥንት ጀምሮ መክሊቱ ነው ፤ ደብረዳሞን የመሳሰሉ ተራሮች በሌጣ እግሩ ሲወጣ ሲወርድ ስለኖረ እግሩ ብርቱ ፥ ትንፋሹ የትየለሌ ነው ፤ ግን መንግስትነት ያዘናጋል፤ መንግስት ስትሆን ታሯሩጣለህ እንጂ አትሮጥም፤ ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ”
በነገራችን ላይ ስለምስጋና ያለኝ ፍልስፍና አጭር ነው ፤ የተደረገለት ያመስግን ! የተደረገበት ያማርር!
ለነገሬ ማድመቂያ የሻለቃ ገብረሀናን ተረብ ልንገራችሁ፤( የገብረሀና ማእረግ ዘመኑን እንዲመጥን ሆኖ ተቀይሯል)
ሻለቃ ገብረሀና ደቀመዝሙር አላቸው ፤ ደቀመዝሙሩ ቀኑን ሙሉ ሲዞር ውሎ ከየቤቱ ቁራሽ እና ጥሬ ለምኖ ያቀርብላቸዋል፤ አንድ ምሽት ደቀመዝሙሩ ቀኑን ሙሉ ሲንከራተት ውሎ አልቀናውም፤ ራት ሰአት ላይ ከግብዳ አኮፋዳ ውስጥ ፥ የትራምፕን መዳፍ እምታክል ጢንጥየ ቁራሽ አውጥቶ አቀረበላቸው ፤ ሻለቃ ገብረሀና እያጉረመረሙ መዳፋቸውን ወደ ቁራሺቱ ሰደድ ሲያደርጉ፥ ደቀ መዝሙር እጃቸውን አፈፍ አድርጎ ያዛቸውና፥
“ሻለቃ ከመብላታችን በፊት እናመስግን " አላቸው፤
“
እሳቸው ፈገግ ብለው፤
“ ተው ልጅየ! አሾፋችሁብኝ ብሎ መብረቅ ይጥልብናል”

@AdamuReta
@AdamuReta
69 viewsedited  06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 19:55:26 (ዮሀንስ ደጉ)

ድሮሮሮሮ

ሐበሻ ሆነህ ዮኒቨርስቲ ከገባህ ያመልኩሃል፡፡ ያጨበጭቡልሃል፡፡ ያደንቁሃል፡፡ ጀለስካዎች ይቀኑብሃል፡፡ ጸዴ፥ የተማረች፥ የተቀሸረች ቸከስ ትጠብሳለህ፡፡ ላይፍ ይገባሃል፡፡ ራስህን ትችላለህ፡፡ ሰው አያነብልህም፡፡ በአውራ ጣትህ አትፈርምም፡፡ ፈረንጅ ማውራት ትችላለህ፡፡ ፖለቲካ ታውቃለህ፡፡ የመንግስት ስራ ትይዛለህ፡፡ ኮት ትገዛለህ፡፡ ምናምን ምናምን ብለው ያስባሉ፡፡
ቤተሰቦችህ ደረታቸውን ይነፋሉ፡፡ እህቶችህ የመጠበሻ ክላሳቸው ከፍ ይላል፡፡ ወመኔው ወንድምህ በስምህ ተበድሮ ያጨሳል፡፡ የሰፈሩ ቅያስ በስምህ ይጠራል "ያ ዮኒቨርስቲ የገባው ጨዋ ልጅ ቤት ጋ" ምናምን ነገር፥ የሰፈሩ ሼባዎች ያከብሩሃል፥ ወመኔ ጀለሶችህ በሹክሹክታ ያሙሃል፥ የተለየ ወጥ ይሰራልሃል፥ ትኩስ እንጀራ ይቀርብልሃል፡፡ ትከበራለህ፡፡
የዋለልኝን አርቲክል ታነባለህ፡፡ ጥላሁን ግዛው ይናፍቅሃል፡፡ መንግስትን ትጠላለህ፡፡ ቦርጫም ቢሮክራት ይደብርሃል፡፡ ፀጉርህን ታጎፍራለህ፡፡ ፂም ይኖርሃል፡፡ ፍልስፍና፥ ታሪክ፥ ፖለቲካ፥ ትንሽ ሳይንስ ትለበልባለህ፡፡ ትከራከራለህ፡፡ በካሴት ሙዚቃ ትሰማለህ፡፡ ሲጋራ ታጨሳለህ፡፡ ወሬህ ፀዴ ይሆናል፡፡ አይዲያሊስት ሆነህ ቁጭ ትላለህ፡፡ ምድር ላይ ገነት ትፈልጋለህ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ባንተ ትግል ነፃ እንደሚወጣ ታምናለህ፡፡
ትመረቃለህ፡፡ በት በት ብለህ የመንግስት ስራ ትይዛለህ፡፡ ቤት ትከራያለህ፡፡ ኮት ትገዛለህ፡፡ መፃህፍት ይኖሩሃል፡፡ መንግስትን በጎሪጥ ታያለህ፡፡ እሱም ይገላምጥሃል፡፡ ሲመሽ ቢራ ትጠጣለህ፡፡ መንግስትን በሹክሹኩታ ታማለህ፡፡ መኖር ትጀምራለህ፡፡ ለናትህ ሻሽ ትገዛለህ፡፡ ለአባትህ የጠጅ መጠጫ ትሸጉጣለህ፡፡ ጨረቃን በገመድ ለማውረድ እንደሞከርክ ይገባሃል፡፡ ኒያላ ለኩሰህ ከት ብለህ ትስቃለህ፡፡ ታገባለህ፡፡ እናትህን አያት ታደርጋለህ፡፡ ሰፈሩ ለሚያሰራው መንገድ ሊቀመንበር ትሆናለህ፡፡

ዛሬሬሬሬሬሬ

በእድል ትገባለህ፥ ትኮርጃለህ፥ ወይ ትንሽ ታነብ እና ትገባለህ፡፡ አንዱ ክልል ይወረውሩሃል፡፡ ጉዳይህ አይደለም፡፡ ግቢ ትደርሳለህ፡፡ የሆነ ቋንቋ የሚያወሩ ቢጤዎችህ ይቀበሉሃል፡፡ ያወሩሃል፡፡ ጠላትህን ያሳዩሃል፡፡ ፌሮ የሚቀመጥበትን ቦታ ታያለህ፡፡ ፋራሽህ ስር ቆመጥ ትቀረቅራለህ፡፡ ይሄን ለምን እንደምታደርግ አታውቅም፡፡ አጠይቅም፡፡ አያገባህም፡፡
የሆነ ትምህርት ትጀምራለህ፡፡ ሲመችህ ታነባለህ፡፡ ብዙ ስለማይመችህ አታነብም፡፡ ሌክቸር ያመልጥሃል፡፡ ትናንት ከጀለሶች ጋር አዳር ስለጠጣህ ደክሞሃል፡፡ ትተኛለህ፡፡ ህንዱ ሰውዬ ስለሚደብርህ ከሰዓት ትቀጣዋለህ፡፡ ፈተና ይደርሳል ትፈተናለህ፡፡ እናትህ ስልክ ተውሳ ትደውላለች፡፡ ትንሽ መላ ትቀፍላታለህ፡፡ በሶስተኛው ቀን ይደርስሃል፡፡ ይቃማል፡፡ ይጠጣል፡፡ ቸከስ ትመቻቻለህ፡፡
ቋንቋህን የሚያወራ፥ ጥብቅ ያለ ጨርቅ ሱሪ የለበሰ፥ የተወጠረ፥ አጭር፥ ደማቅ ካናቴራ ያደረገ መንጋ ይከብሃል፡፡ ውሎህ እዛው ነው፡፡ በቋንቋ ተደራጅተህ ትኮርጃለህ፡፡ ታስኮርጃለህ፡፡ ሽመል ይዘህ ትፋለማለህ፡፡ አታነብም፡፡ አትመረምርም፡፡
የእናትህ ሐሳብ ልጄ በየትኛው ብሔር ሽመል ይሞታል የሚል ነው፡፡
ሲኒየር ስትሆን አዲስ ጅንስ ትገዛለህ፥ ጫማ ትቀይራለህ፥ ያንተን ቋንቋ የምታወራ ሴት ትፈልጋለህ፥ በቋንቋህ ሙዚቃ ትሰማለህ፥ የብሔር ፀብ ትሳተፋለህ፡፡ ሙዚቃ፥ ፍልስፍና፥ ሐሳብ፥ ክርክር፥ ሳይንስ አይገባህም፡፡ እየተፋለምክ ትመርቃለህ፡፡ ባንተ መመረቅ ማንም አይገረምም፡፡ መመረቅህን ስታውቅ የራስህን ባዶ ጭንቅላት ይዘህ ትስቃለህ፡፡
ኒቼ፥ አውግስቲን፥ ፕሌቶ፥ ቮልቴር፥ ከበደ ሚካኤል፥ ገ/ህይወት ባይከዳኝ፥ ምናምን ምናምን ላንተ ምንም ናቸው፡፡ የአንተን ቋ ንቋ አያወሩም፡፡ ካንተ ብሄር አይደሉም፡፡ ላንተ ትልቁ ሰው ጃዋር፥ ቬሮኒካ፥ ሚኪ አማራ....ምናምን ናቸው!

'ውነቴን ነው የምልህ አንተን ሳስብ ኤሊ እየጋለብኩ ወደሰማይ መብረር ያምረኛል!
@AdamuReta
@isrik
63 viewsedited  16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 19:50:41 (ይማርህ! አትበይኝ)
ታደሰ ደምሴ

የነፍስ ውዳሴ ፣
ጽድቅ መች ገደደኝ
ያ የደጎች ጉረን፣
ገነት መች ናፈቀኝ
ሲኦል መች አስፈራኝ
ፍቅርሽ አይደለም ወይ ሰብኮ ያቆረበኝ
ምናኔን ቀድሶ ሻሒት ያስወረደኝ
"ታምሜያለሁ" ስልሽ "ይማርህ" አትበይኝ
ጽድቅ ፈውሴ አንቺ ነሽ አንቺ እራስሽ ማሪኝ!

#ሟርርርር

#ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@AdamuReta
@AdamuReta
51 viewsedited  16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 22:06:58 " እሷ ምን ታርግ ፍቅርዋ ነው የገደለኝ ። በሳቁ ፣በለዛው ፣ በጭምትነቱ ጣሬን ሳያበዛ ጭጭ ያረገኝ ። ሰው ለምን ሳቅክ ተብሎ ይከሰሳል ? "

"የቱጋዬን ገድላ ሄደች? "

" ማን ?"

መልስ ፦ ተከሳሽና ተፈቃሪ


ካሊድ አቅሉ


ዳኛው ፦ " ተከሳሽ የክስ ማቅለያ አለሽ ?"

ተፈቃሪ ፦ " አዎ በጣም ያፈቅረኝ ነበር በህይወት ኖሮ ይሄን ቢያይ እንኳን ሞትኩ ነው ሚለው። "

ጠበቃ ፦ " እድሜ ልክ ነው መፈረድ ያለበት ሟችን ከሞት በላይ ገላዋለች "

እሷ የሞት ፍርዱን ትፈልጋለች ።
ለምን ቢባል አፍዋን ሞልታ ምትመልሰው መልስ አላት ።

"ለምን ? "

ከኔ ጋር ሰማይ ቤት ለመገናኘት ቀጠሮ አለን ያውም በግዜ ከሞትኩ ልትከተለኝ ከሄደች ቀድማ ልከተላት ።
" ያፈቀሩትን ሲያጡ ያገኙትን ይለማመጡ " በፍቅር አይሰራም በፍቅር ሚሰራው " የሚያፈቅሩትን ሲያጡ እራስን ማጣት ወይም እውነተኛ አፍቃሪ መፈለግ ነው ። "

አብዝቼ ወዳታለው አልፎም ገነት ላይ እየጠበኳት ነው ። የእሱ ገዳይ ተብላ እጇ ላይ ካቴና ታስሮ ፍርድ ቤት ገትረዋታል ።

እሷ ምን ታርግ ፍቅርዋ ነው የገደለኝ በሳቁ ፣ በለዛው ፣ በጭምትነቱ ጣሪን ሳያበዛ ጭጭ አረገኝ ። ሳቅ አብዝታ ባጠገቤ እኔም ስርዋን ስምግ ሄድኩ እንደ ቀልድ ምድርን ትቼ . . .

ሰው ለምን ሳቅክ ተብሎ ይከሰሳል ?

" ለመሞት ቀድሞ የወጣውም ጥፋተኛ ነው። "

ሊፈርዱባት ዳር ዳር ሲላቸው በድኑ አካሌ በር ከፍቶ ገባ ። " ነፍሴን ሰውታ አካሌን ለማን ነው ያስቀረችው ?"

"እንጃ "

አያለው ግን አላስተውልም ሰማለው ግን አላዳምጥም አለ አካሌ እኔው ጋር እኔው ነኝ እኔው ጋር የሌለውት ።
( ነፍሴ ተነጥቃለች )

አካሌ የሷ ጠበቃ መሆን ዳዳው መቼስ ነፍሴን ሰርቃለች ተብሎ አካልዋ አይቀጣም ።

ዳኛው ጎሮሮዋቸውን ጠርገው " ግራና ቀኙን አይተናል ፍርዱን ለከሰአት ።
አሉ የመዶሻውን ድምፅ በማስከተል ።


ይቀጥላል ክፍል 2 . . . . .

@AdamuReta
62 viewsedited  19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 19:34:43 ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​
ፀሎት አድራሽ ፈለኩ፣
ሰንፌ አይደለም፣
እመኚኝ ግድ የለም፣

ምልጃዬን ተረኩት፣
አጀብ ተባለልኝ፣
መንደርቴ ሲሰማ በቁሜ ለየልኝ!

ይቺ ናት ፀሎቴ፣
አድራሽ የምትሻ፣
ማትከብድ ለትከሻ!
የነገርኩት ሰማ ይቺን ፀሎት ብሎ፣

"መጨረሻዋን አስጀምርልኝ"

የወፈፌ፞፞፞ ፅንፉ ንገሪኝ ምን ይሆን?
እኔ ግን አላብድም፣
አላብድም ሰው ልሆን!
የሆንኩት እንዲህ ነው፣
ያልሆንኩትን እንጃ፣
ሰምተሽ ትሰጫለሽ “አብዷል” የሚል ፍርጃ!
.
.
«..ሲያለቅሱ ሳኩ እንጂ ሲስቁ አልሳኩም፣
«..ሱሪ ባንገት እንጂ በ'ግር አልሞከርኩም፣
«...ውሀ ፈራሁ እንጂ ምግብ አልፈለኩም፣
«..እርቃኔን ሄድኩ እንጂ እራፊ አለበስኩም፣
«..አንቺ'ኳ ተረጂኝ እኔኮ አላበድኩም!

ናታን ኤርሚያስ

#ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@AdamuReta
@AdamuReta
57 viewsedited  16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 07:40:32
#አለ ማወቅ

#ሰው ከአፈር ነው የሚሰራው ካሉኝ ጊዜ አንስቶ፥ ዝናብ በዘነበ ቁጥር በጎርፍ ተሸርሽሬ የማልቅ እየመሰለኝ እሰጋ ነበር - በልጅነቴ።

#የእናቴ ድምጽ እና ንግግር ከነዜማው የመጀመሪያው የርህራሄ ግንኙነቴ ነበር፤ ሰዎች ከርህራሄ ጋር የምንተዋወቀው በእናቶቻችን ድምጽ ነው።

#ረሀብ አንድም የእርዳታ ጥሪ ማቅረቢያ ... በመሰረታዊነት ግን ለመኖራችን የሌሎች ሰዎች መኖር አስፈላጊነት ማስታወሻ ነው።

#መኖር የሚጀምረው አለመኖርን በመፍራት ቢሆንም፥ የመኖር መሰረቱ ግን አለማወቅ ነው። በህይወት ውስጥ ካሉ ጥቂት ቋሚ ሁኔታዎች መካከል አንዱ አለማወቅ ነው።

#ጥልቅ ሃዘን ማለት ማዘን ሲያቅት ነው። ... ማዘን አለመቻል ግን ከሞት ይከፋል። ሰው በመጀመሪያ ስሜት ነው፥ ሌላው ሁሉ ተከታይ ነው። ሰው ስሜቱን ካጣ ጎዶሎ ነው።

#ያልተመለሱ ጥያቄዎች የመኖር ሞተሮች ናቸው።

#የመናገር ነጻነት ሮጦ ከማምለጥ አቅም ጋር ካልተቆራኘ ትርፉ ድካም ነው።

#አለማወቅ
#ዳዊት ወንድማገኝ

https://t.me/AdamuReta
53 viewsedited  04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 13:10:51
እ ግ ዜ ር



ከእግዜር ወዲያ ፈጣሪ፣
ከአባት ወዲያ መካሪ፣
ከእናት ወዲያ መስካሪ።


እግዜር ሲሰጥ፣ እንጀራ በወጥ።


እግዜርን ሳይጨምር የቆጠረ፣
ሁልጊዜ ሲቆጥር ይኖራል።


እግዜር ሲጥል፣ እናት አታነሳም።


እግዜር የተናገረውን አያስቀር፣
የሚያደርገውን አይናገር።


እግዜር በመለኮቱ፣ ጎልማሳ በሚስቱ።


እግዜር እባብን የልቡን ዓይቶ እግር ነሳው።


እግዜር በትር ሲቆርጥ ቆላ አይወርድም።


ለእግዜር የቀነቀነ ለጽድቅ፣
ለጌታ የቀነቀነ ለወርቅ።


እግዜርን ያህል ጌታ፣ ገነትን ያህል ቦታ።


እግዜር ሲቀጣ፣ ልምጭ አይቆርጥም።


እግዜር ባወቀ፣ ሰማይን አራቀ።


በማን ላይ ቆመሽ፣ እግዜርን ታሚያለሽ።


የእግዜር ነገር፣ አይመረመር።


ነገር በምሳሌ
@AdamuReta
54 viewsedited  10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 20:22:15
ጃንሆይ

በአንድ ወቅት የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ ንጉሱን እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል....

“ለመሆኑ ...ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? ”
ጃንሆይም ቆፍጠን ባለ አነጋገር ለዛ...
“ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ትህትና ነው” አሉት።
ጋዜጠኛውም ቢሆን የዋዛ አልነበረምና......
“ይቅርታ ያድርጉልኝና ጃንሆይ ይሄ ሃምብልነስ እና ፕራውድነስ የሚሉት ነገር እርስ በርሱ የሚጣረስ ማንነት አይመስልዎትም?” የሚል ጥያቄ ያስከትላል።

ንጉሱም እንዲህ አሉ .....“አየህ አንድ በጣም ተራ የምትለው ገበሬ ቤት በእንግድነት ብትሄድ ያለውን አብልቶ፤ እግርህን አጥቦ፤ ያጠበውን እግርህን ስሞ፤ አልጋውን ላንተ ለቆ እርሱ ግን መሬት ላይ ይተኛል። በዚያው ልክ በሚስቱ፣ በርስቱና በሃገሩ ላይ ብትመጣበት ደግሞ በግንባርህ ላይ ጥይት ይቆጥርልሃል፤ ስለዚህ አይጋጭም፤ ነገር ግን ይሄንን ነገር ለመረዳት አንተ ራስህ ኢትዮጵያዊ መሆን አለብህ” ነበር ያሉት።
53 views17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 20:20:05 "አሹ ሁለት ብር ይዘሀል?" አለኝ የመንደራችን ቀፋይ፣ ከሁለት ቀናት በፊት
'ምን ይሠራልሀል?' አልኩት የሁል ጊዜ ሠበቦቹ ስለሚያዝናኑኝ
"እራሴን ላጠፋ ፈልጌ አሪፍ ገመድ መግዛት ፈልጌ ነው" አለ ሳቅ እያለ
ከኪሴ ድፍን አሥር ብር አውጥቼ እየሰጠሁት
'ካሚል ሱቅ አሪፍ ሲባጎ ታገኛለህ፤ ሁለት ሜትሩን በሁለት ብር ይሸጥልሀል' አልኩት
"ታድያ አስር ብር ለምን ትሰጠኛለህ?" አለኝ ግራ ተጋብቶ
'በሥድሥት ብሩ ሶስት ሲጋራ አጭስ፤ በአንድ ብሩ መናዘዣ ወረቀት ግዛ' ብዬው ላልፍ ሥል
"የቀረችውን አንድ ብርስ ምን ላርጋት?" አለኝ በጭንቀት
'ወንድ ልጅ ባዶ ኪሱን አይሞትም!' አልኩት ኮሥተር ብዬ

ከሰዓት በሁዋላ ቀፋዬ ራሡን መሥቀሉን ሠማሁ።

ዛሬ፥ በሠልሥቱ ድንኩዋን ውሥጥ ካርታ እየተጫውትኩ ሳስበው የገረመኝ ነገር በኑዛዜው ማብቂያ አካባቢ ሞቱን ሥፖንሠር ሥላደረኩለት ማመሥገኑ ነበር!
.
.
.
.
'ማነህ ... ዳኛው፣ .... እስቲ ቦነስ ጻፍልኝ!'

@AdamuReta
@AdamuReta
@isrik

#Ashenafi_melese
47 viewsedited  17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 20:16:39 ማሸነፍ ፤ መሸነፍ እና መበሻሸቅ
(በእውቀቱ ስዩም)

ከልጅነታችን ባንዱ ቀን፤ እኔ ከማ አቡኔ ቤት ጠላ ገዝቼ ወደ ቤቴ ስመጣ ፤ ሌላው እኩያየ ደሞ ላምባ ገዝቶ ወደ ቤቱ ሲሄድ መስቀልኛ መንገድ ላይ እንገናኛለን ፤ ከዩንበርሱ በጥቂት አመት የሚበልጥ ጥንታዊ ድንጋይ ላይ የተቀመጠ ቦዘኔ ጎረምሳ ይጠራንና “ ትቸለዋለህ?” ይለናል፤
እኔ ወደ ባለላምባው እያየሁ “ከነካኝ አለቀውም “ እላለሁ፤ ባለ ላምባውም ተመሳሳይ መልስ ይሰጣል፤ ‘ከነካኝ አለቀውም” የሚለውን ሰላማዊነትን እና አይበገሬነትን እንዲሁም “ፍትሃዊነትን” አስተባበሮ የያዘ አባባል በልጅነታችን ማን እንዳቀበለን አላውቅም ጎረምሳው በዚህ አባባል ረክቶ አያሰናብተንም፤ ነገር ቆስቁሶ ያፋጥጠናል፤ ዘመዶቼ ሰርግ ላይ ሲሉ እንደሰማሁት” አረንዛው ዳሞቴ “ብየ እፎክርና የጠላ ማንቆርቆሪያየን አስቀምጣለሁ ፤ ባለላምባው ልጅ ጀሪካኑን ማስቀመጥ አይጠበቅበትም፤ ከሳሎን ተነስቶ ምኝታ ቤቱ እሰኪደርስ ደረስ በሩም ግድግዳውም እየገጨው ያደገ የላምባ ሰፈር ልጅ ነው ፤ በቴስታ መታኝ ማለት ጉዳቴን ማቃለል ይሆንብኛል ፤ ጭንቅሎውን እንደ መርግ ደጋግሞ ጣለብኝ ማለት ይሻላል፤

ከሰአታት በሁዋላ አይጠ-መጎጥ ቀምሶ የተወው ቀይ ስር መስየ ቤት ሰመጣ እናቴ
“ ተመተህ ወደ ቤት መጣህ አይደል?” ትለኛለች፤

“ አይ ! ሳልሰናበትሽ መሸፈቱ ከብዶኝ ነው እንጂ በዛው ጫካ ልገባ ነበር” እንድላት ነበር የፈለገችው?
በዘንድሮው ምርጫ ማግስት በተሸናፊዎች ላይ የዘነበውን ብሽሽቅ ሳይ አንድ ነገር አሰብኩ ፤ ለማብሸቅ የማይመች ባህርይ ያላቸው ፍጡራን የታደሉ ናቸው- ልክ እንደ ፈንቴ!

ፈንቴ በጉርምስና ዘመኔ የማውቀው የሰፈራችን ልጅ ነበር፤
አንድ ቀን ረፋድ ላይ ፤ ከተማችን በታወቀ ቡና ቤት በረንዳ ላይ የትምርት ቤት ዩኒፎርም የለበሰች ቆንጆ ኮረዳ ልጅ ጋር ቁጭ ብሏል ፤ ከፊታቸው ሁለት ንብ የሚዞራቸው የተጀመሩ የኮካኮላ ጠርሙሶች ይታያሉ ፤ ተግባሩ የሚባለው የሰፈራችን ነገረኛ ልጅ በዚያ ሲያልፍ ፈንቴን ከኮረዳይቱ ጋራ ሲያየው ተናደደ፤ እድል እንዲህ ናት ፤ ላንዱ Dateቱን ” ለሌላው ንዴቱን ትሰጠዋለች፤

“ ፈንቴ ” ብሎ ተጣራ ፤ ተግባሩ

“ አቤት”

“ ትናንት መኩርያ፤ በቆላ ሽመል ሲያሯሯጥህ ለምን ነው የሸሸኸው ? “ አለና ፈገግ ብሎ ልጂቱን አያት፤

“የቱ መኩርያ? “ አለ ፈንቴ

“መኩርያ የጋሸ ተጫነ ልጅ?”

“የትኛው ጋሸ ተጫነ? ”

“ ያልገባህ ይመስል አታድርቀኝ
“
“ እ መኩርያ ተጫነ አወቅሁት! እና እሱ የት ላይ ነው ያባረረኝ?"

“ ሙስጠፋ ጮርናቄ ቤት አጠገብ "

“ የቱ ሙስጠፋ? “ ፈንቴ ቀጠለ፤

“ አታምታታ! መኩርያ ለምንድነው ሲያባርርህ የሮጥከው? “

“ ዥል! ለምን ይመስልሃል? ሙሉ አካሌን ይዥ ወደ ቤቴ ለመግባት ስለፈለግሁ ነዋ “

........... @AdamuReta ...........
49 viewsedited  17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ