Get Mystery Box with random crypto!

Booney Pictures

የቴሌግራም ቻናል አርማ adadis_mezmur — Booney Pictures B
የቴሌግራም ቻናል አርማ adadis_mezmur — Booney Pictures
የሰርጥ አድራሻ: @adadis_mezmur
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 728
የሰርጥ መግለጫ

@yoni5341

@Boni_53_bot

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-10-29 11:05:12
219 views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 23:43:00
521 views20:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-12 19:35:23 (6) ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም በሄደ ጊዜ ዋንኞች የሆኑት የቤተክርስቲያን መሪዎች በእርሱ መልእክት ላይ አንዳችም ነገር አልጨመሩም ነበር ። ጳውሎስ የተሰጠውን ስልጣን ተቀብለዋል ። ከአሕዛብ ወገን የመጡ ክርስቲያኖች የአይሁድን ሕግ የግድ መጠበቅ አለባቸው አላሉም ። በኢየሩሳሌም የነበሩት የቤተክርስቲያን መሪዎችና ሐዋርያትን ጳውሎስ ከእርሱ በላይ አድርጎ አልቆጠራቸውም ። ጳውሎስ የሐዋርያነቱን ስልጣን የተቀበለው ከእነዚህ ሰዎች ሳይሆን በቀጥታ ከእግዚአብሔር እንደሆነ እናውቃለን ። እግዚአብሔር ሰዎችን የሚያየው በዓለም ውስጥ ያላቸውን ስፍራ ሳይሆን በውስጣቸው ያለውን መንፈሳዊ ሁኔታ ነው ። ጳውሎስ በዚህ ቦታ የጸፈው ለመሪዎቻችን እንዳንታዘዝ ወይም እንዳናከብራቸው ሳንሆን እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት እነርሱ መሪና ሐዋርያ እንደሆነ ማሳየቱ ነበር ። ስለዚህም የእነርሱ ወሳኔ ለመከተል ግዴታ አልነበረበትም ። ይሁን እንጂ ዋንኞች ያልሆንን ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያን ያሉንን ልንታዘዝ ይገባናል ።

(7-8) ጴጥሮስና ሌሎቹ የእየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መሪዎች ለወንጌል ሥራ አደራ እንደተሰጣቸው ጳውሎስም እንዲሁ ተሰጥቶታል ። በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያት ለአይሁድ ወንጌልን እንደሰበኩ ጳውሎስ ለአሕዛብ ወንጌልን እንዲሰብከ ተሹሟል ። ሰለዚህ እግዚአብሔር በሌሎቹ ሐዋርያት እንደሰራ በጳውሎስም ይሰራ ነበር ። ጳውሎስና ሌሎች ሐዋርያት የሰበኩት አንድ ወንጌል ነው ።

(9) የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መሪውች በደስታ የጳውሎስና የበርናባስን ሐዋርያነት ተቀብለው ለመስማማታቸው ቀኝ እጃቸውን ሰጧቸው ። ጳውሎስ የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው ይላል ። ይህም የሐዋርያነት ጸጋ ነበር (ኤፌ 3÷7-8)። የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ዋና መሪዎች ያዕቆብ ፣ ጴጥሮስ (ኬፋ ) እና ዮሐንስ ነበሩ ። እነዚህ ሰዎች ጳውሎስ የቤተክርስቲያን አዕማድ ይላቸዋል ። ዮሐንስ የኢየሱስ ተወዳጅ ደቀመዝሙር በመባይ የሚታወቅ ሲሆን የዮሐንስ ወንጌልና በስሙ የተጻፉትን ሦስት የአዲስ ኪዳን መልእክቶች ጽፎአል ። እነዚህ የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መሪዎች ጳውሎስና በርናባስ ለአሕዛብ እነርሱ ደግሞ ለአይሁድ ወንጌልን ሲሰብኩ ተስማምተዋል ። ይህም ጥሩ ቅንጅት ነበር ። አንዳንድ ክርስቲያኖች ለአንድ ሥራ ይጠራሉ ። ልሎች ደግሞ ለሌላ ስራ በእግዚአብሔር ይጠራሉ ። እግዚአብሔር ወደሚልከን ቦታ ለመሄድ ዝግጁ መሆን ይገባናል ።

(10) የእየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መሪዎች ጳውሎስን አንድ ነገር እንዲያደርጉ ለመኑት ይህም ድሆችን እንዲያስብ ። መሪዎች ይህን ሲሉ በኢየሩሳሌም ያሉ ችግረኞች ክርስቲያኖች ማለታቸው ነበር ። በአዲስ ኪዳን መጸሐፍት በአንዳንድ ስፍራ ጳውሎስ በአሕዛብ ክርስቲያኖች ዘንድ እየዞረ በኢየሩሳሌም ለነበሩ ችግረኞች ክርስቲያኖች ገንዘብ እንዳሰባሰበ ተጠቅሷል ። (የሐዋ 11÷29-30 ፣ ሮሜ 15÷25-26 )

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

አንዳንድ ገለጻዎች
ቁጥር (6 ) ላይ ጴጥሮስ በሚለው ስም ፋንታ አንዳንድ ትርጉሞች «ኬፋ » ይላሉ ። ኬፋ በግሪክ ቋንቋ ጴጥሮስ ማለት ነው ።
(7) ኪልቅያ የአሁኗ ደቡብ ቱርክ ስትሆን ፥ በደቡብ ሶሪያ የምትገኝ የሮም ግዛት ነበረች ።

(9) አንዳንድ የአይሁድ ወንዶች በስምንተኛው ቀን መገረዝ ይጠበቅባቸዋል ።( ዘፍ 19÷9-14) ። ጳውሎስ በነበረበት ዘመን መገረዝ አይሁድ መሆንን የሚያረጋግጥ ወጫዊ ማስረጃ ነበር ።

(10) የግሪክ ሰዎች በደቡባዊ አውሮፓ በምትገኝ አገር የሚናሩ ናቸው ። በአዲስ ኪዳን ዘመን ግሪክ የሮም ግዛት እንዶ ክፍል ነበረች ። የግሪክ ሰዎች አይሁዳውያን አልነበሩም ። የዳበረ ባሕልም አልነበራቸውም ። በዚህም ዘመን በመካከለኛው ምሥራቅ የነበሩ አብዛኞዎቹ ሙሁራ የግሪክ ቋንቋ ይናገሩ ነበር ። አዲሰ ኪዳን በመጀመሪያ የተጻፈ በግሪክ ቋንቋ ነው ።

ይቀጥላል ..............

ሕያው ቃል ቴሌ ግራም ቻናል
3.4K views16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ