2021-09-20 17:23:40
#መንፈስቅዱስ
መንፈስ ቅዱስ -የሪቫይቫል ምንጭ ባለቤትና ኃይል
“እግዚአብሔር ይላል ፡- በመጨረሻው ቀን እንዱህ ይሆናል ፤ ሥጋ በሇበሰ ሁለ ሊይ
ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤”-የሐዋ 2፡17
አማኝ በክርስቶስ ኢየሱስ ሲያምን ሕያው የሚያደርገውንና ለዘላለምም በሕይወት
እንድኖር የሚያስችለውን የሥላሴን ሶስተኛው አካል (ደረጃን አያመለክትም)
ክቡሩና አስደናቂው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስጦታ ሆኖ ይሰጠዋል ፡፡ ይኸው
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከአማኙ የግል ሕይወት መዳንና መለወጥ ባለፈ
በቅድሳን ሕብረት (በቤተክርስቲያን) ውስጥ ጥበብንና ኃይልን በመግለጥ
ቤተክርስቲያንን በትውልድ መካከል የታመነ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምስክር አድርጎ ያቆማታል ፡፡
እርሱ መንፈስ ቅዱስ ከዘላለም የነበረ ለዘላለምም የሚኖር ሁለን የፈጠረ እና
ለሙታንም ሕይወትን የሚሰጥ የሥላሴ ሶስተኛ አካል የሆነ የእግዚአብሔር
ሕይወት ነው፡፡ እርሱ ባለበት ሁለ ሕይወት አለ ፡፡ በእርሱ መገኘት ውስጥ ሞትና
ጭንገፋ አይሰራም፡፡ ያስባል፣ ይናገራል፣ ያዳምጣል ፣ ይሸከማል፣፤ያስተምራል ፣
ይመራል ፣ ያስተጥቃል። እግዚአብሔር እርሱ በላከው በኢየሱስ ክርስቶስ
ለሚያምኑ ያዘጋጀው ስጦታ መንፈስ ቅደስ መሆኑ ምን ያህል ፍቅር እና ቸር
መሆኑን ያሳያል፡፡ መንፈስ ቅደስ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ ነው፤ የምክር እና
የኃይል መንፈስ ነው፤ የእውነት እና የቅድስና መንፈስ ነው፤ የትንሣኤ እና የክብር መንፈስ ነው…፡፡
ይህ እንዲለ ሆኖ መንፈስ ቅዱስንና ሪቫይቫል ምንድን ነው የሚያገናኛቸው? ጌታኢየሱስ ሐዋሪያቱን ለወንጌል ሥራ ከመላኩ በፊት በሐዋ 24፡49 “ከላይ ኃይልን
እስክትለብሱ ድረስ …” ብሎ በመናገር ያለ መንፈስ ቅደስ ለመንቀሳቀስ እንኳ
እንዲይሞክሩ አስጠንቅቋቸዋል ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እግዚአብሔር በመጨረሻው
ዘመን ሥጋ በለበሰ ሁለ ከመንፈሱ እንደሚያፈስ እና ምልክቶችና ድንቆች
እንደሚሆኑ ተናግሯል (ኢዩ 2፡ 28-30) ፡፡ ጌታ ኢየሱስም በግልጥ ሲናገር “ያለእኔ
ምንም ልታደርጉ አትችሉመምና” ብሏል (ዮሐ 15፡5) ፡፡ እነዚህ እና ሌሎች
የእግዚአብሔር ቃል ጥቅሶች የሚያስረዱት እግዚአብሔር የሚያደርገውን ነገር ሁሉ
የሚያደርገው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መሆኑን ነው፡፡
የእግዚአብሔር ስራ ያለ መንፈስ ቅድስ የማይሞከር፣ ጭራሹንም የማይታሰብ
ነው፡፡ ይልቁንም ጉዲዩ ሪቫይቫል ሲሆን መንፈስ ቅዱስ እና መንፈስ ቅዱስ ብቻ
የሪቫይቫሉ ምንጭ፣ ባለቤት እና ኃይል በመሆን ዋነኛ ድርሻውን ይወስዲል፡፡
ቤተክርስቲያን ለመንፈስ ቅዱስ ዕውቅናን መስጠትና በእርሱም ለመመራት እራሷን
ማስገዛት ይጠበቅባታል በመንፈስ ቅዱስ መመራት እና በመፅሃፍ ቅዱስ እውነት
መመራት የሚጋጭበቸው ሰዎች ልኖሩ ይችላሉ ፡፡ መንፈስ ቅዱስ መፅሃፍ
አይደለም፡፡ መፅሃፍ ቅዱስንም ያዘጋጀልን እርሱን እንድተካልን አይደለም ፡፡
ይልቁንም በእርሱ መሪነት እግዚአብሔርንና በክርስቶስ በኩል ያደረገልንን በማወቅከእርሱ ከራሱ ጋር ቀጥተኛ ሕብረት እንዲኖረን እና ከምድር ባልሆነ የእርሱ ኃይል
ወንጌልን በድንቆችና በምልክቶች፣ በፈውስና በተአምራት መስበክ እንዴንችል
ነው፡፡ መንፈስ ቅደስ የሪቫይቫል ምንጭ፣ ባለቤት እና ኃይል ነው፡፡
በብለይ ኪዳን መፃህፍትም ሆነ በአድስ ኪዳን ሲያልፍም በቤተክርስቲያን ታሪክ
ውስጥ ተፅዕኖን ፈጥረው እና የእግዚአብሔርን ክብር ገልጠው ያለፉ የእግዚብሔር
ሰዎች ትልቁ ምስጢራቸው ከዚህ የእግዚአብሔር መንፈስ መንፈስ ቅዱስ ጋር የነበራቸው ጥብቅና ጥልቅ ቁርኝት ነው፡፡ እርሱን ማስተዋል የጀመሩ ጊዜ
ሕይወታቸው ተቀየረ፤ አካሄዳቸውንም ከእርሱ ጋር ባደረጉ ጊዜ ከፍ ሊለ ዓላማ
ሲጠቀምባቸው ታየ፡፡ ሪቫይቫልን የሚያደርገው የእግዚአብሔርንም ክብር ኢየሱስ
ክርስቶስን የሚገለጠው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው፡፡ ክብር ሁሉ…
ለእርሱና እርሱ ብቻ ይሁን!!!!! ሃሌሉያ!!!!!!!
ይድረስ የእግዚአብሔርን ክብር ለተራቡት please share በማድረግ ተባበሩኝ
@Acts_Revival
@Acts_Revival
@Acts_Revival
2.0K views14:23