Get Mystery Box with random crypto!

#_ለምን_ይሆን? አንተ በውድ ሆስፒታል ተወልደህ ይሆናል ፣ እኔ በቤት ውስጥ ተወልጄአለሁ ፤ | አጫጭር ልብ ወለድ

#_ለምን_ይሆን?
አንተ በውድ ሆስፒታል ተወልደህ ይሆናል ፣ እኔ በቤት ውስጥ ተወልጄአለሁ ፤ ሁለታችንም በህይወት እየኖርን ነው ።

አንተ በግል ትምህርት ቤት ተምረህ ይሆናል ፣ እኔ በመንግስት ትምህርት ቤት ተምሬአለሁ ፤ ሁለታችንም በአንድ ዩንቨርስቲ ጨርሰናል ።

አንተ ከምቹ አልጋ ላይ ከእንቅልፍህ ነቅተህ ይሆናል ፣ እኔ ከመሬት ላይ ፤ ሁለታችንም የሰላም ሌሊት አሳልፈናል ።

አንተ የለበስካቸው ልብሶች ውብና ውድ ይሆናሉ ፣ የኔ ቀላልና ርካሽ ናቸው ፤ ሁለታችንም ራቁትነታችንን ሸፍነናል ።

አንተ ብዙ የምግብ ዐይነቶችን ከጥሩ መስተንግዶ ጋር አማርጠህ በልተህ ይሆናል ፣ እኔ ቤት ያፈራውን ወስጄ በልቻለሁ ፤ ሁለታችንም ግን የምግብ ፍላጎታችንን ለማርካት ስንል ተመግበናል ።

አንተ Land Cruser TurboV8 ፣ Range Rover ፣ Lexus Jeep ፣ Hummer Jeep ወይንም G Wagon...መኪና ትነዳ ይሆናል ፣ እኔ የህዝብ ትራንስፓርት እጠቀማለሁ ፤ ሁለታችንም ግን ወደፈለግንበት መዳረሻ ደርሰናል ።

ምናልባት ይሄንን ልጥፍ (post) እያነበብክ ያለኸው ፤ በSamsung Galaxy 8Edge ፣ በiPhone7s+ ፣ በSony Xperia ፣ በGoldvish Le Million ወይንም በVertu Signature Cobra...ስልክህ ታግዘህ ይሆናል ፣ እኔ ይህንን የምፅፈው ስክሪኑ በተሰበረ ስልኬ ቢሆን እንኳ ሁለታችንም መልእክቱ እኩል ይታየናል ።

ይሀውልህ ፤ በአእርግጥ ህይወት የፉክክር መድረክ ነች ። ነገር ግን ነገሮችን ለማሳካት ብዙ መንገዶች ቢኖሩ እንኳ ሁሉም የህይወት መስመሮች የሚመሩን ወደ አንድ አቅጣጫ ነው ። ይኸውም- ሞት ። ደግሞ ደስታ ሁሉንም ነገር በማግኘት ውስጥ አይመጣም ፣ ካለህ ነገር ውስጥ መልካሙን በማውጣት እንጂ ። ትልቁ ቁምነገር ያለው ራስህን የምታይበት መነጽር ነው ። ደስታ ማለት የምትወደውን ማግኘትም አይደለም ፣ ደስታ ማለት ያገኘኸውን በቂ ነገር መውደድ ነው ። ልብ በል ፤ ያንተ በዚህ አለም መኖር የሚያስደስተው ሌላውን ሲሆን አንተን የሚያስደስትህም የሌላው መኖር ነው ።

የትላንት ትላንት ምንም አልነበረህም ፤ ምንም ሳትይዝ ፣ ራቁትህን ነው ይችን ዓለም የተቀላቀልከው ፤ ይሁንና ትላንት ያጣኸውን ዛሬ አግኝተሃል ፣ ዛሬ ያጣኸውን ነገ ታገኘዋለህ ፣ ሁሉንም ደግሞ የነገ ነገ ታጣዋለህ ። ባጭሩ አንድ ቀን ሁሉንም ትተህ ትሞታለህ ።

#_ከሞትክ_በኋላስ?
ከ3 ቀን በኋላ የጣቶችህ ጥፍሮች መወዳደቅ ይጀምራሉ ። ከ4 ቀን በኋላ የራስ ቅልህና ሰውነትህ ላይ ያሉ ጸጉሮች በሙሉ ይረግፋሉ ። ከ5 ቀን በኋላ አንጎልህ መርገብ ይጀምራል ፣ የሰውነትህ ሥጋ ይጠወልጋል ፤ መቀመጫህ ፣ ጡትና ኃፍረተ-ስጋህ ይበሰብሳል ። ከ6 ቀን በኋላ ቆዳህ መሳሳትና ቀስ በቀስም ከአጥንትህ ላይ መለያየት ይጀምራል ። ከ7 ቀን በኋላ ሆድህ ይቀልጣል ፣ መጥፎ ጠረንም ማውጣት (radiate ማድረግ) ይጀምራል ። ከሞትክ ከ60 ቀን በኋላ መላው የሰውነትህ አካል ወዳልነበር ይለወጥና "አንተ" ማለት "አጥንት" ብቻ ትሆናለህ ።

#ታዲያ
ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ትእቢት ?
ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ራስ ወዳድነት ?
ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ክርክር ፣ ጭቅጭቅና ንትርክ ?
ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ቅናት ?
ለምንስ ይሆን ይሄ ሁሉ ጥላቻ ?
እኮ ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ የክፋት ሥራ ?

ጥለህ ለምትሄደው አለም እስኪ ለሞት ሩብ ጉዳይ እንደቀረው ሰው እንኑር ። ደሃ ሃብታም እያልክ ሳታደላ ፣ የተማረ ያልተማረ ብለህ ሳትለይ ፣ መልከ መልካም መልከ ጥፉ ሳትል ፣ ባለስልጣን ተራ ሰው ብለህ ሳትመርጥ...ሁሉንም በሰው'ነቱ እኩል- ተመልከት ፣ ስማ ፣ እርዳ ፣ አድን
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኛነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ