Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ታሪኮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ achacher — ግጥምና ታሪኮች
የቴሌግራም ቻናል አርማ achacher — ግጥምና ታሪኮች
የሰርጥ አድራሻ: @achacher
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.01K
የሰርጥ መግለጫ

በዚ Channel ★የራሴን የግጥም ስራዎችና በሌሎች ገጣሚያን የተሠሩ አሪፍ አሪፍ የግጥም ስራዎች★ እንዲሁም ተከታታይ መሳጭ ታሪኮችየምታገኙ ይሆናል አብራቹኝ ሁኑ★ግራፋክስ ዲዛይን ማሰራት የምትፈልጉ @darkniha ላይ አውሩን
★ Anything አስተያየት እና ሀሳብ ካለዎት💛 for any comment
@darkniha
@dark_niha_bot
@Hanan_Akmel

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-10 18:37:46 ትኬቱን ለማግኘት
ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ 10ኛ ፎቅ ቢቁ 1017
0937060707
ቡራዩ አከባቢ ለምትገኙ
በ 0921125054
ቤተል
0919870615
ዘነበ ወርቅ አከባቢ ለምትገኙ
በ 0912456163
አየርጤና አለም ባንክ አከባቢ
በ 0911 13 72 07 /0963 352736
አጠና ጠራ እና ጠሮ አከባቢ ለምትገኙ
0910182476
ገርጂ እና አከባቢዋ
0914298759
አተውቢስ ተራ እና ስድስት ኪሎ ለምትገኙ
0928281261
ቦሌ እና ደምበል አካባቢ
0922880282
ካራ ወለቴ እና ጦርሀይሎች
0939871138 ወይም 0988155879
አሸዋ ሜዳ እና ሜክሲኮ
0912402886
መርካቶ እና አከባቢዋ 0911727326/0911872237
ቀራንዮ እና ጋርመንት
0916799802
አዳማ
0938936677
66 viewsɖąཞƙŋıɧą, 15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 18:37:31
61 viewsɖąཞƙŋıɧą, 15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 20:36:42 ውድ የግጥምና አጫጭር ታሪኮች ተከታታዮች ከሌሎች ቻናሎች ስንተያይ በጣም ሚጢጢ ነን እኮ ምን አለበት ቢያንስ ለ5 ሰው እያንዳንዳችን @achacher ኢቺን ሊንክ ብንልክ አሁን ያለነውን ሜምበርስ በ5 ስታባዙት በጣም እንበዛለን እንዲስተካከል ምትፈልጉትን በcomment አድርሱኝ!!
ለ ፈጣሪ ብለን ሁላቹንም ሳናዳላ በፍቅር በእኩል እኖዳቹዋለን
@achacher
125 viewsɖąཞƙŋıɧą, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 10:14:58 ማስነሳት አይችልም!።

፨ እነ ዕዝራ ቤት ሰራተኛዋ ብና እያፈላች ነው። የዕዝራ አባት እና እናት ፊት እዝን ብሏል አስሚ ሶፍው ላይ ለተኛው ዕዝራ ቀስ እያረገች ሾርባ በማንኪያ በትንሽ በትንሹ እያጠጣችው ነው። የሙና ሞት ሶስት ወራት ቢያስቆጥረም የዕዝራ አይኖች ግን አንባ ማፍሰሳቸውን አላቆሙም። አስሚ ሾረባውን ስታጠጣው አፉ አልችል ብሎት የሚያፈሰውን በትንሽዬ ፎጣ እየጠረገችለት። "አይዞህ ለትንሽ ጊዜ ነው እሺ" አለችና በያዘችው ማንኪያ ሾረባ ቀነስ አረጋ ወደ አፉ ስታደረግለት አፉን ግጥም አረጎ ዘጋው። ይህ ማለት በቅቶታል ማለት ነው። አስሚ "እሺ በቃህ ማለት ነው በቃ ትንሽ ነው የቀረህ እሺ እሱን ደሞ እናትህ ሲረብህ ያጎረሱሀል። ከእንግዲህ የምንገናኘው ከሳምንት በኋላ ነው። ለምን መሰለህ ልጆችንን ወደ ሀኪም ቤተሰቦች ይዘናት ልንሄድ ነው ከተወለደች ጀምሮ አኮ አይተዋት አያውቁም በወሬ ብቻ ነው እንጂ የሚያውቁት።" ስትለው የግዱን ትንሽ ፈገግ አለላት። አስሚም "ሀዘን ላይ ሆነህ እረሱ ትሰቅልኛህ አደል ለእኔ ብለህ የኔ ምስኪን በቃ እቤት ሄጄ ልብሳችንን ማስተካከል አለብኝ ሀኪሜ ማታ መጥቶ ይጠይቅሀል እሺ ከስራ በኋላ" ብላ ተነሳችና እናት እና አባቱን እንዲሁም ሰራተኛዋን ተሰናብታቸው ልትወጣ ስትል "አስሚ ልጅሽን ሳም አረጊልኝ ሰራተኛችሁንም ሰላም በያት"አሉዋት። የዕዝራ እናት "እሺ አደርሳሁ" ብላ ወጣች።
፨ አስሚ ከሄደች በኋላ ዕዝራ አይኑን ጭፍን አረጎ። የተወሰነ ከቆየ በኋላ እንቅልፍ ወሰደው። እናቱ ቀስ ብለው የለበሰውን ጋቢ አመቻችተው አለበሱትና ብናቸውን መጠጣት ጀመሩ። አባቱ "ወይ ፈተና ወይ ጊዜ" አሉ። የዕዝራ እናት "ተው እባክክ እንዳታማርር" አሉ። "እሺ ተመስገን በሉ ብናው ካለቀ እኔም ወደ ስራዬ ልመለስ ከመኝታ ቤት ፎጣ አምጥተሽ እስቲ ደረብ አረጊለት እንዳይበረው" ብለው ለመውጣት መዘገጃጀት ጀመሩ። የዕዝራ እናትም ወደ መኝታ ቤት ሄደው። ለዕዝራ የሚደረብ ቀለል ያለ ፎጣ ይዘው መጥተው ሊያለብሱት ሲሉ ከእዚራ አፍንጮ በሁለቱም ጎን ደም እየፈሰሰ አሉ። "ወይኔኔ ልጄጄጄ" ብለው ጮሁ የዕዝራ አባት የሚስታቸውን ጩከት ሰምተው ከበር እየሮጡ ወደ ቤት ተመለሱ ዘበኛውም ሮጦ ሳሎን ገባ። ስራተኛዋ ግን ሀገር ሰላም ብላ እቃ እያጠበች ነው




ክፍል 40(አርባ) ይቀጥላል....

ተፃፈ ፣ ተደረሰ በቀድሞዋ የአለሜ ነሽ እና የፅናት ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ) biz gitar
143 viewsɖąཞƙŋıɧą, 07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 10:14:43 Biz Gitar:
ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ)biz gitar





ሳልሳዊ





ክፍል 39(ሰላሳ ዘጠኝ)





፨የህይወት ፈተና በተለይ ህይወት ፊቷን ካዛረችብን ከባድ ይሆናል። በዕዝራ ህይወት ውስጥም ፈተናዎች ተደራረበዋል። ዕዝራ ከቀናት በኋላ እራሱን ያገኘው ሆስፒታል አልጋ ላይ ነው። ቀስስ አረጎ አይኑን ገለጥ አረገው። ወዲያው ለመጨረሻ ጊዜ እስራሱን ሳይስት በፊት የት እንደነበረ አስታወሰ። እጆቹን ማንቀሳቀስም አልቻለም እግሮቹም ልክ እንደ እጃቹ ሊታዘዙት አልቻሉም። እንባ ብቻ ከአይኑ ለጉድ ይዘንባል። ለሁለተኛ ጊዜ የሚፈልጉትን አግኝቶ ማጣት ይከብዳል። ከዛም በላይ ደሞ አካላችን ታዞ ጫኸን እሮጠን አልያም ተንፈራፍረን የውስጣችንን ስሜት ማውጣት አለመቻሉ ውስጥን ጎድቶ በጣሙንም ያማል። ዕዝራ አፉንም ለማንቀሳቀስ ጥረት አደረገ ግን ሊንቀሳቀሱ አልቻሉም። ውስጡ ያለውን ሀዘን በእንባ ብቻ እንዲያወጣው የተፈቀደለት ዕዝራ የማያቋረጥ እንባውን ለጉድ እያወረደው ነው።
፨ያለበት ክፍል በር ሲከፈት ተሰማው ዞር ብሎ በመከራ ለማየት ቢሞክረም አልቻለም። ዶክተር ማህሌት ናት። "ቀስ ብላ እንባውን ጠረገችለት እና "አዝናሁ" አለችው። ዕዝራም አይኑን ጭፍን በማረግ አመሰገናት። "በህክምና ቀስ በቀስ ትድናለህ ውስጥህን ማከም ቢያቅተኝም ለጥቂት ሰአት ላሳየከኝ ሰወዊ ትህትና ስል የምችለውን ሁሉ ነገር አረግልሀለው" ዕዝራ በዝምታ የዶክተሯን አይኖች ከማየት ውጪ ቢፈልግም መናገር አልቻለም። ቃል ከአፉ ለማውጣት ሲቸገር "ቆይ ቆይ አሁን ለማውራት ያስቸግረሀል ግን አታስብ ይሻልሀል የነረቭ ችግር ነው የያዘህ አሁን ስለነቃህ እናት እና አባትህን አስገብቼያቸው ታያቸዋለህ አስሚ እና ሀኪምም አሉ። ማን እንደሆነ አላውቅም ግን ስዩም ነኝ ያለ አንድ ጓደኛህም አለ ሁሉም በተራ በተራ እየገብ ያዩሀል አታስብ እንድትድን የተቻለንን ሁሉ እናደረጋለን" ብላው። በድጋሜ እንባውን ጠረጋለት ወጣች።
፨አንድ ጊቢ ውስጥ ሀይለኛ የለቅሶ ድምፅ ይሰማል። ለእቅሶ ላይ ከተሰበሰብት መሀል "ልጄ ልጄ ሙናዬ ልጄ እኔን ልጄ እኔ አፈር ልሁንልሽ" እያሉ የሚያለቅሱ ሴት አሉ። የሙና እናት ናቸው። "ልጄ ልጄ" እያሉ እሪሪ እሪሪ ሲሉ ላያቸው ሰው ሀዘኑ ልባቸው ውስጥ ገብቶ እንደጎዳቸው በግልፅ ይታያል። "ብቸኛዋ ልጄ እኔን እኔን እኔን" እያሉ ደረታቸውን በሀያሉ ሲደቁ አቤት ሲያሳዝኑኑኑ። ፊታቸውን ሲፎጭሩ ፤ አቅም አጥሯቸው ድክም ሲሉ ሆዳቸውን እየደበደቡ ወደ ፈጣሪያቸው አንጋጠው "ምን አረኩህ ምን በድዬ ነው እንዲህ አይነት ስቃይ ያሸከምከኝ እኔን ብትወስደኝ አይሻልም?" እያሉ ድምፃቸው እስኪዘጋ ሲያለቅሱ ላያቸው ሰው ያማል። አስተዛዛኝ ጎረቤቶች ሁሉ የሚያስለቅሳቸው ከሙና ሞት ባሻገር የሙና እናት ቃላቶች እና አለቃቀሰሰ ነው።
፨እዚህ ደሞ የመጀመሪያ ፍቅሩ መካሻ የነበረችውን ሙናን አጥቶ በእሷ መሞት ውስጥ የሚሰቃይ ሊላ ፈጥረት አለ። ዕዝራ!
እናቱ ቁልቁል ወደ ተኛበት አልጋ እያዩት እንባቸውን ያወረዱታል። "ልጄ ምን ብዬ ላፅናናህ? ልጄ ምን ቃል ነው አንተን ሊያፅናናህስ የሚችለው?" እያሉ እሪሪ አሉ። ዕዝራ እናቱን ሲያያቸው እንባው በፍጥነት መውረድ ጀመረ። የእንባው ፈሳሾች ጆሮ ውስጥ ያለ ከልካይ ጥልቅ ጥልቅ ጥልቅቅ ይላሉ። "እኔን ልጄ እኔን እኔ እንዲህ ስቅይት ልበልልህ፤እኔ እንዲህ እዝን ልበልህ ልጄ" ብለው ወለሉ ላይ ተደፍተው እሪሪ አሉ። ዶክተር ማህሌት መጥታ "እባኮትን አያስጨንቁት" ብላ ይዛቸው ወጣች።
፨እሳቸው ከወጡ በኋላ አባቱ መጡ። አባቱም "ልጄ የኔ ጠንካራ ልጅ አይዞህ ሁሉም ነገር ያልፍል ልጄ ጠንካራ ነህ አውቃለሁ ይህንንም አልፈህ ጥሩ ህይወት ትኖራለህ"ብለው እንባ ሲተናነቃቸው ወጡ። እሳቸው ሲወጡ። አስሚ እና ሀኪም ገብ። አስሚ "ዕዝራ ወንድሜ የኔ ምረጥ እባክክን በአላ አታልቅስ" አለችው። እሷ እያለቀሰች ሀኪምም "ዕዝራ ሁሉም ሰው ይፈተናል እንደነገረኩህ ያንተ ግን እንደ ሰወኛ ስናስበው በጣም ከባድ ነው። እንደ ፈጣሪ ግን ለበጎ ነው ወንድሜ አይዞህ በቃ አስሚ ነይ አናድክመው ስዩም ስላለ እሱ ብዙ የሚነግረው ነገር አለ" ብሎ አስሚን አቅፎ ይዞት ሲወጣ አሰሚ ዞር ብላ "የኔ ዕዝራ ወንድሜ በጣም እንወድሃለን እሺ" ብላው ወጣች።
፨ከወጡ በኋላ አስሚ እና የዕዝራ እናት እያለቀሱ በባሎቻቸው በመባበል ላይ ናቸው። ዶክተር መሀሌትም "ስዩም መግባት ትችላለህ" ብላ ወደ በሩ ጠቆመችው። ስዩምም ገባ። ወደ ዕዝራ ጠጋ አለ የዕዝራ እንባ አሁንም እየፈሰሰ ነው ስዩም ጥቁር በጥቁር ለብሷል በጣም እንዳዘነ ከፊቱ ያሳብቅበታል። "ስላም ዕዝራ ጓደኛዬ አንዴት ነህ መቼስ ይሄ ልጅ አንዴት ከዛ ጊቢ ወጣ ብለህ ለእራስህ እየጠየከው ነው አደል? የምነግረህን በትኩረት አድምጠኝ እሺ። እኔ ሳይካትሪስት ስዩም እባላለሁ አንተን በማዳን ውስጥ የራሴ ተልኮ ነበረኝ። ምን መሰለክ ተልኮዬ አንተ እየተሻለክ በመጣህበት ወቅት እና ሲማይን እንደረሳት ከታወቀ በኋላ በህይወት ተስፋ አለህ ወይስ የለህም የሚለውን አስተሳሰብ ለመፈተን ነው ወደ አንተ የመጣሁት ሙና አንተ ፊት በህይወት ተስፋ የቆረጠውን ማለቴ ሙናን የወጋት ሰው አወከው አደል። የእሱን አስተሳሰብና በትንሹ ወስጄ አንተ ጋር ማውራት እና ስለ ህይወት ያለህን አቋም ማወቅ ነበር ተልኮዬ ስእል ስለምስል ሙና እኔን ካንተ ጋር የምታስተዋውቅበት ስበብ ሆነ። እንጂ እኔ በጣም የማፈቅራት ሚስት እና አራት ልጆች አሉኝ። ሊላው ልነግረህ የምፈልገው ነገር የሙና ገዳይ ታውቃ በእስር ላይ ናት። አንተ እራስህን ስተህ ሙና ደሞ ሞታ ነው የተገኛችሁት እሷም እዛው ጭንቅላቷ ላይ ተኩሳ ነው የሞተችው" ሲለው ዕዝራ አይኑን በደብ ጨፍኖ ደቂቃ አስቆጠረ።
፨ስዩም ንግግሩን አላቆሙም "ማለቴ ስትከታተልህ የነበረችው ሳይኮ በሙና በጣም ትቀና ነበር። በእረግጥ የሙና በጣም የልብ ጓደኛ ነበረች ሙናን ደጋግማ አስቀይማት ሙናም ደጋግማ ይቅር ብላታለች። ግን ደሞ በድጋሜ መጥፎ መሆኖን ቀጠለች ሙና እንድትወጋ ያረገችው እና ሙናን ለማስወጋት ለወጊው የተቆለፈውን በር የከፈተችለት እሷ ነበረች። የወጋበትን ካቻቢቴ ሁሉ እሷ ናት እንደሰጠችው ለእሱ በሩን ከፍታ ከወደድካት ግደላት ያንተ አስተሳሰብ ልክ ነው ጥሩ ሰዎች እዚህ ሲኣል ውስጥ መኖር የለባቸውም ብላ ለሁሉም ነገር መነሻ የሆነችው እሷ ናት ይህንን ጭንቅላቷ ላይ ሽጉጥ ደቅና ነው የተናገረችው አያይዛም ሙናን የወጋትን ሰውዬ በመረዝ እንደነገችው እና ምንም ቢሆን እና ቢመጣ እንደማትቀየር ቅናትዋ የማይጠፋ እንደሆነና መኖረም እንደሊለባት ብትኖረም ብዙ ሰዎች በእሷ ምክንያት እንደሚሞቱ እሷ ከሞተች ግን ለሁሉም ነገር መፍትሄ እንደሆነ ሙናን መግደሉዋ በመቅፅፈት እራስዋን እንዳስጠላት እና ሙናን በጣም ስለምትቀናባት እንጂ ጠልታት እንዳልሆነ ተናግራ እራስዋ ላይ ተኩሳ ሞተች" አለ ስዩም። ከዛ ግን ስዩም "ወይኔ ሙና ጓደኛዬዬ" ብሎ እሪሪ አለ። ዕዝራ በማልቀስ ብዛት አይኑ ቀልቶ በጭስ የተጎዳ እና በጭስ ምክንያት ሊጠፋ የደረሰ አይን መስሏል። አለመናገር ይጎዳልና ዕዝራ መናገር ባለመቻሉ እጅጉን ተጎድቷል። ስዩም ዕዝራን አየው ዝም ብሎ እንባው እየፈሰሰ ነው በጣም አሳዘነው ቢችልና ሙናን የተፈለገውን መሰዋትነት ከፍሎ ከመቃብር ፈንቅሎ አውጥቶ የዕዝራን ልብ ጮቤ ቢያስረግጠው ደስሰ ይለው ነበር። ግን ትልቁ ችግር እሱ ፍጥረት እንጂ ፈጣሪ አደለም ለዛም ሙናን ከሞት
122 viewsɖąཞƙŋıɧą, 07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 17:03:00 ብላቸው። ቁጭ አለች።

፨ አስሚ ልክ ዕዝራ ሊቀመጥ ሲል "እእ ዕዝራ ሙና ደውላ ነበር ቤት ሲገባ ይደውልልኝ ብላለች ሳትቀመጥ ብትደውልላት ጥሩ ነው" አለችው። ዕዝራ "የምር? እሺ" ብሎ ጥድፍ እያለ ወደ ስልኩ ሄዶ ደወለ ትንሽ ጠረቶ ተነሳ "ሄሎ" የሙና ድምፅ ነው። "ሙኔ"...... "ወዬ እንዴት ነህ ትደውላለህ ብዬ ቁጭ ብዬ ስልክ ስልኩን እያየውት ነበር"....... "እኔም መደወልሽን ስሰለማ ተጣድፌ ነው የደወልኩልሽ ለምንድነው ግን እንደዛ ተጣድፈሽ የሄድሽው?"......" እሱን ነገ ስትመጣ ነው የምነግረህ በጣም ስለናፈከኝ ድምፅህን ሳልሰማ ምንም ማሰብም መስራትም አልቻልኩም"......."እንዲህ ስትይኝ ይበልጥ እንደምትናፍቂኝ ታውቂያለሽ?"....... "እህ በቃ አሁን መዝጋት አለብኝ ነገ በጠዋት ና እሺ"... "እሺ ሙኔ ማታም እደውልልሻለሁ"..... "እሺ እጠብቃለሁ" ስልኩ ተዘጋ።
፨ ቁረስ እየበሉ ሲጨዋወቱ ሲሳሳቁ በጣም ያስቀናሉ። ዶክተር ማህሌትም ከእነሱ ጋር ተዋህዳለች። ዕዝራ ትናት ማታ በሆነው ነገር በጣም እየተዝናኑ ነው። "እናንተ ሳቁ ምን አለባቹ የእኔ ውድ ሙና ሞታለች ብዬ ደንግጫለሁ በሰአቱ እኮ አስብት አይኑዋ አይረገበገብም ከዛ ቆየት ብላ ነካ አረጌያት ሙኔ እላታለሁ እገለዋለሁ ብላ እረፍ ለካ ቅዠቱ ነው ያስፈጠጣት። እሷ መጥታ ማደንዘዣው ሊያቃዣት ስለሚችል እንዳደነግጡ ስትለኝ እኮ ነው በራሴ እኔ እረሱ የተዝናናውት" አለ ወደ ዶክተር ማህሌት እየጠቆመ። በጋራ ስቀው ተጫውተው ብና ጠጥተው ፤ ምግብም በልተው ሲጨረሱ። ዕዝራ "እእ እማማ ማበጠሪያ የት ነው ያለው" አላቸው። የዕዝራ እናት "ለምንህ ነው ልጄ" ሲሉት። "መሀሌትን ማለቴ ዶክተር ማህሌትን ፀጉሯን ልሰራት ነው" አላቸው። እናትየው "እሺ በረንዳ አለልህ" ሲሉት። ዕዝራ "ጥሩ በቃ እዛው እሰራታለሁ ዛሬ ከምታፈቅረው ስው ጋር ቀጠሮ አላት ላሳምራት በይ ነይ በረንዳ" ብሎ ወደ ውጪ ሲወጣ ዶክተር ማህሌትም ተከትላው ወጣች። ዱካው ጋር አስቀምጧት ቆንጆ አረጎ ሰራትና በመስታወት አሳያት "ወይኔ አምላኬ ሲያምር ልክ ከጠበኩት በላይ ነው የሰራከኝ ወይኔ ግን ሰአቱ ሄደ ከእሱ ጋር ከመገናኘቴ በፊት መሄድ ያለብኝ ቦታ አለ" ስትለው ዕዝራ "እሺ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ቻው ብለሻቸው እኔ እሸኝሻለሁ በዛውም እኔ ለማፈቅራት ሴት የምገዛው እቃ አለ" ብሎት ውስጥ ገብታ ሁሉንም ተሰናብታቸው ወጣች። ዕዝራም ወደ አባቱ ጆሮ ጠጋ ብሎ "አባባ ብር ስጠኝ ለሙና የምሰጣትን ስጦታ ልግዛላት" ሲላቸው ሰጡት። ወደ ሀኪም ዞር ብሎ "አንተ ደሞ መሀሌትን የምሸኝበት የመኪና ቁልፍ ስጠኝ" ሲለው ከነ ሹፌሩ አይሻልህም ብሎት አብሯቸው ወጣ።
፨ ጠዋት አደለም ለሊት ላይ ነው ዕዝራ ወደ ሙና ለመሄድ የተነሳው እስኪያያት በጣም ጉጉት ብሏል አልነጋለት ብሎ በመከራ ነጋለት ጨለማው ለአይን ያዝ ማረግ ትቶ ለቀቅ ሲያረገው ዕዝራ ዘበኛውን ቀስቅሶ የመኪና በር አስከፍቶ የሙናን ስጣታ እና መዳኔቶች ይዞ ወደ ሙና በረረ። ሲደረስ ከጠዋቱ አንድ ሰአት ሆኖል። ዘበኖቹ ስለሚያውቁት ከፍተው አስገብት።
፨ ዕዝራ በቀጥታ የሄደው የሙና መኝታ ክፍል ነው። አንኳኳ በደብ አንኳኳ የሚከፍትለት ሲያጣ ሊመለስ ሲል በሩ ተከፈተ። ሙና ልክ ዕዝራን ስታየለው ደስታዋ ወደር አልነበረውም። ዕዝራ እቅፍ አረጎ ሰላም አላት። ሙናም ጉንጩን ሳመችው። በውስጡ ዛሬማ ከስጦታው ጋር እንደማፈቅረሽ እነግርሻለሁ ከቻልኩ ግን ሲማይ ጋረ ይዤሽ ሄጄ እዛው የምነግረሽ" አለ። "ና ግባ" ብላ ክፍሉዋ አስገባችውና ፀሀይ በደብ እስኪወጣ የሙና አልጋ ላይ ጋደም አሉ። "ሙኔ ግን ተሻለሽ አሁን እንዴት ነሽ"......"ደና ነኝ"........"እሺ መድሀኒትሽን አምጥቼለሻለሁ ነይ ቆይ ፋሻውን ልቀይረልሽ"......"አሁን?" ....... "አዎ አሁን በይ በጀረባሽ ተኒ"......."ካልክ እሺ"...." ብላ በጀረባዋ ተኝታለት ጃኬቷ አውልቃ በቦዲ ሆና ቁስሉዋን አጥቦ ቀየረላት። ዕዝራ "ደሞ ሹረባውን መፍታት ጀምረሽ ነበር?"...."አዎ ሲጨንበኝ"..... "ቆይ እኔ ልጨረስልሽ" ብሎ ፈታትና እያበጠረላት ፍቅሩን ሊገልፅላት ፈለገ ከዛ ደሞ ቆይ ፁጉሯን ጨረሼ ከስጦታው ጋር ግን ሲማይ ጋር ወስጃት ይሻላል ብሎ አራዘመው። ፀጉሯን ፈቶላት አበጥሮላት ሲጨረስ አልጋው ላይ ወጥተው ፊት ለፊት በትይዩ መልኩ ተቀመጡ። አይን ለአይን ተገጣጠሙ ሳያሰሰብት ቀስ በቀስ ተጠጋግተው ሊስማት ሲል ያሉበት ክፍል በሀይል ተከፈተ። ሳይካትሪስቷ ነበረች። ሙና እና ዕዝራ እኩል "በስማም" አሉ። የሶክትሪስቷ አስተያየት ያስፈራ ነበር ምንም ነገር ሳትናገር ከጋውንዋ ትንሽዬ ሽጉጥ አውጥታ የሙና ጭንቅላት ፣ አንገት ፣ ደረት እና ሆድ ላይ ደጋግማ ተኮሰችባት ዕዝራ በድንጋጤ ሙና ሞተች እያለ እራሱን ሳተ።




ክፍል 39 (ሰላሳ ዘጠኝ)ይቀጥላል.....
139 viewsɖąཞƙŋıɧą, 14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 17:02:50 Biz Gitar:
ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ)biz gitar




ሳልሳዊ




ክፍል 38(ሰላሳ ስምንት)




፨ "ዕዝራዬ ነገ ከሰአት ላይ ጊቢ ናና እናወራለን በጣም አስቸኳይ ነገር ስለሆነብኝ ነው እሺ ተመለስ" አለችው። ዕዝራ "ካልሽ እሺ ሙኔ" ብሎ ተመለሰ። ሀኪምም "ና በቃ ሂሳብ ዘግተን እንውጣ"። ብሎት ሂሳብ የሚከፈልበት ጋር ሄዱ እና ሁሉንም ሂሳብ ዘግተው ፤ መዳኒቱን ተቀብለው ሊወጡ ሲሉ ዶክተሯን አገኑዋት እየወጣች እንደሆነ ያስታውቃል። ዕዝራ "ዶክተር እየወጣሽ ነው እንዴ?" አላት። "አዎ የምጠብቃቸው ታካሚ ነበሩ ቀጠሮውን ለነገ ስላረጉት ልወጣ ነው።" አለችው። "ጥሩ ስለዚህ ነያ አብረን ሄደን ፁጉረሽን ሰረቼሽ ትሄጃለሽ" አላት። ዶክተሯም ሳታቅማማ "እሺ ደስስ ይለኛል" አለች። ሀኪም እጅ በደረት አረጎ በግምት አንገቱን ወዘወዘ። ዕዝራም "ሀሚሞ በቃ ስልክክን ስጠኝ እነ እማማን ላዋራቸው ለሳይኮዋ ዶክተር ደውዬም ጠዋት እመጣለሁ ስላለች ልደውል ብሎ ስልኩን ተቀበለውና ወደ ኋላ ቀረት ብሎ ቤት ደውሎ "ሄሎ" አለና "ሂዱ እየሄዳቹ" አለ። ዶክተሯ እና ሀኪም ከፊት ከፊት ዕዝራ ከኋላ ሆኖ መሄድ ጀመሩ። "እማማ ልንመጣ ነው አንድ እንግዳም አለን ስለዚህ ጥሩ ቁርስ እና ብና አዘጋጅታቹ ጠብቁኝ።"........."አዎ እማማ አንድ ሰው ነው ይዘን እምንመጣው"...... ደና ነኝ ስመጣ እናወራለን።" ስልኩን እንደዛ ብሎ ዘጋውና ከስልኩ ኮንታክት ውስጥ የዕዝራ ዶክተር የሚለውን አግኝቶ ደወለ። "ሄሎ ዶክተር"......."ዶክተር አደለሁም ዕዝራ ነኝ"......."እእ ዕዝራ አንዴት ነህ"... "ደና ነኝ ይቅርታ በጠዋት ደወልኩኝ" አለ ስቅቅ እንደማለት ብሎ። "ችግር የለም ቀደም ብዬ ተነስቼ ስለነበር አረበሽከኝም ሙና መድረስ እና አለመድረሷን ለመጠየቅ ነዋ አደዋወልህ"........" እንደሱ እንኳን አልነበረም ጠዋት እመጣለሁ ስላልሽ እኛ ወተናል አትልፊ ልልሽ ነበር አደዋወሌ"...... " አይይ አውቃለሁ"...... ግን ሙና እንደዛ ተጣድፋ የወጣችው ለምንድነው?" .... " እሱን እራስዋ ትነግረሀለች"...... " ግን በሰላም ነው"......."አዎ አንድ መረዳት የነበረባት እና የእሷ እረዳታ የግድ የሚያስፈልገው ታካሚ አለ ለእሱ ብላ ነው"...... "እሺ እነደዛ ከሆነ በቃ ነገ ጠዋት የታዘዘላት መዳኒቶች ስላሉ ይዤላት እመጣለሁ"....... "እሺ ነገ ጠዋት መምጣት ትችላለህ መልካም ቀን"....... "ላንቺም እንደዛው" ስልኩ ተዘጋ ዕዝራም በዱብ ዱብ ሀኪም እና ዶክተሯ ላይ ደረሰባቸው።
፨ ሀኪም መኪናውን አየሾፈረ ዕዝራ ጋቢና ዶክተሯ ደሞ ከኋላ ሆነው መንገድ ላይ ናቸው። ዕዝራ ወደ ዶክተሯ ዞር ብሎ "ዶክተር ስምሽን ግን እኮ አልነገረሽኝም" አላት። " ማህሌት" እባላለሁ" አለችው ፈገግ ብላ። "እሺ ዶክተር መሀሌት" አላት። የዶክተሩ ስልክ ጠራ "ዕዝራ እስቲ ማነው የሚደውለው ኪሴ ውሰጥ አለልህ አውጣና አናግራቸው ወይ ላውድ ላይ አረገው" ዕዝራ "እሺ" ብሎ ከሀኪም ኪስ ስልኩን አወጣው። ስሙ ሀኪም የሚሰራበት ሆስፒታል ነው። ዕዝራ ወደ እሱ ዞር አረጎ አሳየው " ኦ ከስራ ቦታ ነው አንሳውና ላውድ ላይ አረግልኝ" አለው። ዕዝራ እንዳለው አደረገለት። "ሄሎ" አለ ሀኪም ትህትና በተሞላበት መልኩ። ወፈር ያለ የወንድ ድምፅ ነበር። "ሄሎ ዶክተር ሀኪም እንዴት ነህ"........."አልሀምዲዲላሂ እረሶ እንዴት ኖት"........"ደና ነኝ ክብሩ ይስፋ እኔ እምልህ?"......"ወዬ ዶክተር".........."አሁን እኮ ነው የምሰማው ከእረፍት ስመለስ የልጅ አባት ሆንክ አደል"......."አዎ አልሀ ምን ይሳነዋል".........."ልክ ነው ልክ ነው ደስ ብሎኛል"..........."እእ ሙሉ ለሙሉ ተሽሎት ስራ ጀመሩ እንዴ"........."አዎ ጀምሬያለሁ ከተልኮ መመለሰሰህ ነው አሉ ሜቢ ነገ ከመጣህ ሚስትህ እና ልጅህን ከስራ በኋላ አያቸዋለሁ"...... "እሺ ዶክተር አመሰግናለሁ አሁን እየነዳው ስለሆነ ነው ቤት ስገባ በሰፊው እናወራለን"........"እሺ መልካም መልካም" ስልኩ ተዘጋ። ዶክተር ማህሌትም "እንዴ ዶክተር ነህ እንዴ?" አለችው። "አዎ ሳካትሪስት ነኝ"......."ኦኦኦ ይገረማል በጣም አሪፍ ሙያ ነው ያለህ እኔም በጣም የምወደው ሙያ ነው".. ...." እና ለምን አልተማረሽም እሱን"....."ያው አሁን ላይ ጎን ለጎን እየተማረኩት ነው"..... "ጥሩ ፍላጎቱ ካለሽ" በድጋሜ የሀኪም ስልክ ጠራ ስልኩ ዕዝራ እጅ ላይ ስለነበር አየው የዕዝራ አባት ይላል። ዕዝራ "ሀኪሞ አባባ ነው የሚደውለው" አለው። "አንሳዋ ታዲያ" አለ ሀኪም። ዕዝራ ስልኩን አነሳውና "ሄሎ አባባ.....አዎ አዎ እየመጣን ነው አባባ......ኧረ ልንደረስ ነው..... እሺ እሺ" ብሎ ስልኩን ዘጋው። ዶክተሯ የዕዝራን ንግግር ብቻ ስለሰማች ግራ ተጋብታ ዝም ብላ ጋደም አለች።
፨"ዕዝራ እየመጣን ነው አለ እንዴ የዕዝራ አባት?" አስሚ ናት ጠያቂዋ የዕዝራ አባትም ከሳሎን ሆነው "አዎ ልጄ እየመጣን ነው ብሎኛል"....... "ማንን እንደሚያመጣ ነግሮታል ወይስ"...... "ኧረ አልነገረኝም" ሳሎን ብና ቦታው ላይ የተቀመጡት የዕዝራ እናት "ምን አልባት ሙናን ይሆናል ይዞ የሚመጣው" አሉ። አስሚ ከመኝታ ቤትዋ እየወጣች። "ውይ ቢሆንማ ጥሩ ነው እንደውም እኔም ባለፈው ስለተናጉ
ገረኳት አላስፈላጊ ቃሎች ይቅርታ እጠይቃታለሁ" አለች። የቤታቸው ስልክ ጠራ አስሚ ልጅዋን ሶፋው ላይ አንጋላት እኔ አነሳዋለሁ ብላ ሄደች። ስልኩን አንስታ "ሄሎ" አለች። "እእ ሄለው"...... "አቤት ማን ልበለል"......."ሙና ነኝ"......."ውይ ሙና አንቺ ነሽ እንዴ?"........"አዎ ዕዝራ የለም እንዴ"......"አይ የለም እሱ፤ ያው ግን እየመጣ ነው። ግን አሁን እንዴት ነሽ ተሻለሽ.... " አዎ በጣም ደና ነኝ"......." አውቀሽኛል አደል?".... " አዎ በደብ ይህንን ድምፅ ልረሳው አልችልም"...... "እንዴት ማለት አልገባኝም?"...... "እሱን ተይው በቃ ዕዝራ ሲመጣ እንዲደውልልኝ ንገሪው" ብላ ስልኩን ዘጋችውና የቢሮውን ጠረጴዛ በጣቶቿ ጣጣጣ አረገቻቸውና "አረሳሽም" ብላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተያዩ ቀን ያለችውን አስታውሳ ፈገግ ብላ "ይቅር ብዬሻለሁ" አለች። ሳይካትሪስቷ "ማንን ነው ይቅር ያልሽው" ስትላት "አስሚን አወቅሻት ነገሩ ታቂያታለሽ እንጂ እሷ ያኔ የመጀመሪያ ቀን ስታየኝ የነበረውን አስተያየት እና ቃላት አረሳውም" አለች።
፨ "በቃ ደረሰናል ውረጅ ዶክተር ማህሌት" አላት። ዶክተሯ ተኝታ ነበር። ስትነቃ ያለችበትን መኪና የመኖሪያ ቤት ጊቢ ውስጥ ነው። "አልገባኝም እዚህ ነው?"..... "አዎ የእኛ ቤት ነው ነይ ውረጂ ብና ጠጥተሽ ቁረስም በልተሽ አረፍ ብለሽ ትሄጃለሽ" አላት እና ከመኪናው ወረደ። ሀኪምም ወረደ። ዶክተሯ "ወይኔ ማህሌት ቅሌትሽ" ብላ ከመኪናው ወረዳ መኪናውን ዘጋ አረጋ ዕዝራ እና ሀኪምን ከኋላ እየተከተለቻቸው ልክ የሳሎኑ መግቢያ በር ላይ ሲደረሱ በረንዳው ላይ ቆመች። ዕዝራ "ነይ አትፍሪ ነይ" ብሎ እጅዋን እየጎተተ ቤት አስገባት። ሀኪም "እንዴት ናቹህ ሰዎች አለ። አስሚ ከኩሽና ድምፁን ስሰማ ፈጥና ወጣችና "ሀኪሜ ብላ ተጠመጠመችበት። እቅፍ አረጎ ሳማትና "እንዴት ነሽ የኔ ውድ ሚስት" አላት። "ደና ነኝ ኦ እንግዳችን እንኳን ደና መጣሽ ብላ ሰላም አለቻት። ዶክተሯ ተደነባብራለች። እንደምንም ሁሉንም እየዞረች ሰላም
104 viewsɖąཞƙŋıɧą, 14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 17:02:32 ሄር) እያወጣላት።

፨ ጠዋት ላይ ዶክተሯ የሙናን ሁኔታ ልታይ ስትመጣ። ሀኪም ወንበሩ ላይ ዕዝራ ወለሉ ላይ በትራስ ተቀምጦ ለጥ ብለዋል ሙናም አልጋዋ ላይ ናት። ለጥ ብላለች ዶክተሯም ሙና ላይ የሙቀት መለኪያውን ጣቷ ላይ ስታረገው ነቃች። "ዶክተር ደና አደረሽ" አለቻት። "ይመስገነው አሁን እንዴት ነሽ ሙና"........" አሁን ደና ነኝ ዶክተር"........."ጥሩ ከሰአት በኋላ መውጣት ትችያለሽ ቁስልሽ ላይ የሚቀባ ነገር እና ማጠቢያ እስጥሻለሁ ከዛ ደና ትሆኛለሽ በጣም ህመም ከተሰማሽ እና ቁስሉ ካመቀዘ ግን ትመጫለሽ ፈጣሪ ጨረሶ ይማረሽ" ብላ ሄድ አለችና ተመልሳ" በነገራችን ላይ የፀጉርሽ አስራር በጣም ያምራል" አለቻት። "ሙናም አመሰግናለሁ እሱ ነው የሰራኝ" ብላ ወለሉ ላይ ትራስ አረጎ የተኛውን ዕዝራን አሳየቻት። ዶክተሯ "ይገረማል በጣም ጎበዝ ነው" ስትል ዕዝራ እየተንጠራራ "ከፈለግሽ አንቺንም ልሰራሽ እችላለሁ" አላት። ሀኪምም ከእንቅልፉ ተነሳና "ደና አደራቹ" አለ። ሶስቱም "ይመስገን እንዴት አደረክ?" አሉት። ዶክተሯ "በነገራችን ላይ ከማፈቅረው ሰው ጋር ዛሬ ማታ ቀጠሮ አለኝ ፀጉሬ እረዘም ያለ ስለሆነ ሊያስቸግረህ ይችላል። ግን ብትስራኝ ደስ ይለኛል ከአንድ ሰአት በኋላ ከስራ እወጣለሁ ሲመስለኝ የፀጉር ባለሙያ ነህ አደል የት አከባቢ ነው ፀጉር ቤትህ" አለችው። ሀኪም ሳቁ መጣ ዕዝራም የመኖሪያ ቤታቸውን ቦታ ነገራትና ስደረሺ ደውልኝ አላት። "እሺ አመሰግናለሁ ስልክክን" ስለው የቤታቸውን ስልክ ሰጣት። ዶክተሯ "እሺ" ብላ ወጣች።
፨ "ምን እየሆንክ ነው ቆይ ለምንድን ነው ስልክ የሰጠሀት " አለው። ሙና "እውነትም ዉይ ጉድ" አለች። ዕዝራም "አስቡት እስኪ አንዲት ሴት ከምታፈቅረው ሰው ጋር ስትሄድ ተውባ ሲያያት ያለውን ደስታ የዛ ደስታ ምክንያት ደሞ እኔ ስሆን" ሲል ሀኪም "እና ምን ልታረግ ነው?" አለው። "ሙኔ ዛሬ ነው የምትወጣው እኮ ሙኔን ጊቢ እናደረሳታለን ከዛ እነ አባባ ጋር ሄደን ተጫውተን ብና ጠጥተን እስከዛ ከመጣች ቤት ፀጉሯን እሰራትና ወደ ፍቅረኛዋ ትሄዳለች።"..... " ኧረ አንተስ ትለያለህ እሺ ሙናን ካደረስናት በኋላ እናወራለን" አለ። የክፍሉ በር ተከፈተና በሩ ላይ ቆመው የነበሩት ሰዎች ገብተው አንደኛው "ለሙና በጆሮዋ ጠጋ ብሎ የሆነ ነገር ነገራት ሙና ደነገጠችና "እሺ በቃ አሁኑኑ እንሂድ ዕዝራዬ በቃ ጊቢ ና እሺ እስከዛ ትናፍቀኛለህ" አለችው። ዕዝራ ግራ ገብቶት ምን ማለትሽ ነው ጊቢ አብሬሽ ልምጣ እንጂ" ሲላት። "አይሆንም በቃ አሁን ልብሴን ልልበስ ስጠኝ" አለችው አንደኛውን ጠባቂ በፊስታል የያዘውን ሰጣት። እሷም እነሱ ፊት የሀኪም ቤቱን ልብስ አውልቃ የሰጧትን ለበሰች። ሀኪም እና ዕዝራ ደነገጡና ዞር አሉ። ሀኪም ሙስሊሞች በድንጋጤ ጊዜ የሚጠቀሙትን ቃል ደጋግሞ አለው። "ኢናሊላሂ ወኢናኢለይሂራጂኡን" የሚለውን ቃል። ጠባቂዎቹም ዞር አሉ። ሙና ጫማዬስ።" አለች። "ጮማሽ መሬት ነው አላት። ሙና አንደኛውን ጥበቃ ተደግፋ ወረደችና ጫማዋን አረጋ ደግፈዋት ከክፍሉ ወጡ። ዕዝራ "ሙኔ ሙኔ ምንድነው እያለ ተከተላት። ሙና እረብሽብሽ ብላለች።



ክፍል 38 (ሰላሳ ስምንት) ይቀጥላል......
102 viewsɖąཞƙŋıɧą, 14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 17:02:19 Biz Gitar:
ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ)biz gitar



ሳልሳዊ




ክፍል 37 (ሰላሳ ሰባት)



፨ እንደምንም ተጠግቶ የእግሯን ታፋ ነካ አረጎ "ሙኔ" አላት ፈራ ተባ እያለ። ሙና ፍጥጥ እንዳለች "እገለዋለው" አለች። ዕዝራ "እ" አለ ደንግጦ። "ከነ ውሾቹ እደፋዋለው"..... "ሙኔ ማንን ነው የምትደፊው ስለ ምን ውሻ ነው የምታወሪው ምን ነክቶሻል ሙኔ በፈጠረሽ"..... "ዕዝራዬ"..... "ወዬ ሙኔ"...... "ተኛ" አለችና ገልበጥ ብላ ተኛች። ዕዝራ ፈገግ ብሎ "አሀ ቅዠት ነበር እንዴ" አለ። የክፍሉ በር ተከፈተ ዕዝራ ዞር አለ። ዶክተሯ ነበረች። የሙናን ደህንነት ካየች በኋላ "እእ አስታማሚ ነህ አደል" አለችው "አዎ ነኝ ምነው ዶክተር ችግር አለ?" አላት። ዶክተሯ "አይ በጭራሽ ምንም ችግር የለም የለም የሰጠናት ማደንዘዣ ከባድ ስለሆነ ያቃዣታል እንዳደነግጡ ለማለት ነው" ብላ ወጣች።
፨ዕዝራ ተመስገን አለ። ዶክተሯ ልክ ስትወጣ ሀኪም ገባና። "እ አናገረካት?" አለው። ዕዝራ "ወይ ማናገር ብሎ የገጠመውን ሁሉ ነገር ነገረው ሀኪምም "ወይ ጉድ ይገረማል የምር በጣም ነው የሚገረመው ሰው ሁሉ ይፈተናል ሲመስለኝ ያንተ ግን በዛ" አለው የሀኪም ስልክ ጠራ እጁ ላይ ስለነበር አየት አረገውና "ኦ" ብለሎ አነሳው ና "ሄሎ" አለ። ሶይካትሪስቷ ናት። "ሄሎ እንዴት ናችሁ"..... " ደና ነን አንቺስ"......"እኔም እንደዛው ሙና እንዴት ናት"...... " ደና ናት አሁን እንቅልፍ ላይ ናት"......"ጥሩ ዕዝራስ?"...... "አለ እሱም ደና ነው"......" እና ተረጋጋ አደል እስቲ ስጠው ላውራው"......" አዎ ተረጋግቷል ዕዝራ እንካ"..
፨"ሄሎ ዶክተር"......" ዕዝራ እንዴት ነህ"...... "ደና አደለሁም ሙኔን አስከፋዋት" ብሎ ከክፍሉ ወጣና እራቅ ብሎ እየተንጎራደደ ማውራት ጀመረ። "ዕዝራ የት ሄድክ ሄሎ ይሰማሀል"....." አዎ አዎ ይሰማኛል ሙኔን እንዳረብሻት እራቅ ብዬ ወጥቼ ላውራሽ ብዬ ነው" ..... "እሺ ግን ምን ተፈጥሮ ነው የተረበሽከው"..... "ኧረ የእኔ ጉድ ተወረቶም አያልቅም".... "እሺ ለምን አሁን የሆናችሁትን አነግረኝም".... "ዛሬ ሙኔ አፍቅረሻለሁ እንድላት ፈልጋ ነበር ግን በቃ ቃሉን ማውጣት በጭራሽ አልቻልኩም"..... "ለምን ማለቴ ካፈቀረካት"..... "አዎ አፍቅራታለሁ ግን ለእሷ ከነገረኳት እማጣት ሁሉ እየመሰለኝ ቃሉን ለማውጣት በጣም እፈራለሁ" ......"ይህ ማለት በጣም ቀለል ያለ ነገር ነው ሀኪም እንዲረዳህ እነግረዋለሁ"..... "እሱማ እረዳካለሁ ብሎኛል".... "ስለዚህ በቃ አታስብ እኔ ነገ እመጣለሁ ደና እደሩ".... "እሺ ደና እደሪ" ብሎ ስልኩን ዘግቶ ወደነ ሙና እና ሀኪም ተልሷ በሩን ከፍቶ ሊገባ ሲል ሙና ስትስቅ ሰማት። በሩን ቀስ አረጎ ከፍቶ ገባና በሩን ይዞ ቆመ ሙና "ውይ ዕዝራዬ ሙጣህ እንዴ ና እስቲ ና እዚህ ጋር ተቀመጥ ብላ ከተናችበት አልጋ ጠጋ አለችለት። ዕዝራ ግራ ተጋብቶ እንዴ ሙናን አንዴ ደሞ በሳቅ የደከመ ፊቱን ይዞ የአስታማሚ ወንበር የተቀመጠውን ሀኪም ያያቸዋል። ሙና "ና የእኔ ደንባራ" አለችው። ቅድም ተቀምጦበት የነበረውን የአልጋውን ቦታ እዩተመተመች። ዕዝራ ቀስ ብሎ እየተራመደ ሙና የጠቆመችው ቦታ ላይ ቁጭ ሊል ሲል ሙና እጅዋን ብድግ አረገችለትና ቁጭ አለ። አንገቱን ድፍት አረጎ "ሙኔ ይቅር በይኝ በናትሽ" አላት። ሙናም "ለምኑ?" አለችው ፈገግ እንዳለች። "ለቅድሙ ነዋ ሙኔ አስከፋውሽ ፣ አሳመምኩሽ ግን ሆን ብዬ አደለም"....."እና ሆን ብለህ ላላጠፋከው ጥፋት ለምንድነው ይቅረታ እየጠየከኝ ያለከው?" ስትለው ቀና ብሎ ሆዶ ላይ ያሳረፈችውን እጅዋን ያዛትና "በዛም ተባለ በዛ አስከፍቼሻለሁ" አላት። "ኧረ እኔ እኮ ነኝ አንተን ያልተረዳውህ ግን በቃ አልፎል አደል አንተም ይቅር በለኝ" አለችው። "ውስጥሽ ቅሬታ አለው እኔ ላይ! ግን መኚኝ ለትንሽ ጊዜ ነው" አላት። ሙና "ኧረ እኔ አልተቀየምኩህም በቃ አሁን በደብ ጠጋ ልበልልህና አጠገቤ ተኛ። ሀኪም እሱ ጋርርርር" ስትለው። "አዎ እዚህ እተኛለሁ እኔ እናንተ እሱ ጋር ተኑ" አላቸው።
፨ሙና ጠጋ እያለች "ውይይ ደሞ በቲሸረት ሆነህ በረደህ አደል ና በል ውስጥ ግባ" አለችና የለበሰችውን ብረድ ልብስ ገፈፍ አረገችለት። ዕዝራም ጫማውን እያወለቀ "ግን ዶክተሮች ቢመጡ?" አላት። "ይምጡዋ በል ና" አለችው እና አልጋው ላይ ወጣ ና መልሶ ወረዶ "አይ ሙኔ ይጠብሻል" ብሎ ወረደ። ሙናም ነገሩ ተሸማቀህ ከምተኛ" አለችው። ዕዝም "ሙኔ ፀጉረሽ ጉምዱም ብሏል እኮ ሚዶሽስ?" አላት። "እኔ ምን አውቄ ወይ እዛ ጥዬው ወድቆብኝ ነው የሚሆነው" ስትል ሀኪም "ቆይ እስቲ የድንገተኛ ህመምተኛ ሲመጣ እቃ የሚቀመጥበት ቦታ የሚል ነገር አይቼያለሁ ቅድም ኧረ እንደውም ብኒ ኒዶ ማበጠሪያም አለ" ብሎ ሄደ።
፨ዕዝራ "ፀጉረሽን አበጥረልሻለሁ ከዛ ልስራሽ ሙኔ" አላት። ሙና "አንዴ ፁጉር መስራት ትችላለህ አንዴ?" ስትለው "አዎ እችላለሁ ድሮ እማማን እኔ ነበር የምሰራት"......."ዕዝራዬ እየቀለድክ መሆን አለበት"......"ኧረ እማማ ትሙት እችላለሁ እማማ የሴቱንም ስራ ጨምራ ነው ያስተማረችኝ" አላት። ሀኪም በሩን ከፍቶ ገባና "ይሄ ነው ማበጠሪያው" አላቸው ብኒ ማበጠሪያ ይዞ እያሳያቸው። ሙና "አዎ አዎ አመሰግናለሁ" አለችው። ሀኪምም "ምንም አደል" ብሎ ለዕዝራ ሰጠው። ዕዝራም ተቀብሎ "ሙኔ ወደ እዛኛው ግድግዳ ዞር በይልኝ እንዲመቸኝ" አላት። ሀኪም ግረም ብሎት የአስታማሚ ወንበር ላይ ተቀምጦ በእጅ መደገፊያው አገጩን በመዳፉ ተደግፎ እያየው ነው። ሙና እንዳላት ተመቻችታ ተቀመጠች ። ዕዝራም ቀስስስ እያለ የሙናን ፁጉር እያበጠረላት። "ሙናዬ" ሲላት። "ወዬ" አለችው "ፀጉርሽን ስትሰሪ አይቼሽ አላውቅም ሁሌም አንጨባረሽው በሚዶሽ ስታበጥሪው ነው የማይሽ ለምንነው አላት። ሙና "ለማሰብ እንዲረዳኝ እና ሲጨንቀኝ ጭንቀቴን ለማራገፍ ስለሚጠቅመኝ። ማለቴ ስጨነቅ ወይም ማስታወስ የምፈልሰገው ነገር ሲኖር አልያም ስናደድ ፀጉሬን ሳበጥረው እረጋጋለሁ" አለችው። ሀሚም "ይገረማል!"። አለ። ዕዝራ "በጣም እንዲህ ምክንያት ያዘለ ነገር አይመስለኝም ነበር" አላት።
፨ ዕዝራ የሙናን ፀጉር አበጥሮ ሲጨረስ እየከፈለ ወደ ታች መስራት ሲጀምር ሀኪም " እንዴ ፀጉር መስራት ትችላለህ እንዴ?" አለው ግረም ብሎት። "አዎና የዛሬን አያረገውና እማማንም እኮ እኔ ነበረኩ ፀጉሯን ከሆነ ጊዜ በኋላ የምሰራት" አለው። ሀኪምም "ኧረ አንተ ታምረኛ ነህ" ........ "እንዴት ፀጉር መስራት ደሞ እንዴህ ያስብላል አንዴ ሙኔ አንኪ በእዚህኛው እጅሽ ይህንን ያዚ " አለ። ለሙና ከፍሎ የተረፈውን ፁጉር እየሰጣት። ሀኪምም "እንዴ በጣም ነው የሚያስገረመው" አለውና ዕዝራ የሙናን ፀጉር ሰረቶ እስኪጨረስ ምስጥ ብሎ እያየው ዕዝራ ጨረሰና "እ እንዴት አየከው?" አለው። የሙናን ጭንቅላት ወደ ሀኪሚም ዞር አረጎ "በጣም ያምራል ማመን ሁሉ አልችልም በጣም የተለየክ ሰው ነህ ቀን በቀን እንዳስገረምከኝ ነው" ሲለው። ሙናም በጣቶቾ ፀጉሯን እየደባበሰች እውነትም በጣም ነው የሚያስገረመው አይ አንተማ ተነቦ የማያልቅ መፅሀፍ ነህ ከእዚህ በኋላም ብዙ አስደናቂ ነገሮችን ካንተ እንጠብቃለን አደል ሀኪም" ስትል ሀሚም "በትክክል ምን ጥያቄ አለው" አለ። ዕዝራ "ኦ በጣም አካበዳቹ" አላቸው። የሙናን ተዳፍት (ቤቢ
113 viewsɖąཞƙŋıɧą, 14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 22:52:28 ፨ ዕዝራ ወደ ሙና መግባት በጣም ፈረቷል እስካሁን አልገባም ሊገባ ይልና ይመለሳል። በሩ ዳር እና ዳር ላይ የቆሙት ጠባቂዎች ምንም አላሉትም ዝም ብለው ብቻ የዕዝራን ሁኔታ መከታተል ተያይዘውታል። ሀኪም ወደ ዕዝራ ጠጋ ብሎ "ዕዝራ ምን እያረክ ነው ሙናን አዋራሀት እንዴ?"..... "ሙኔን ገብቶ ማዋራት በጣም ከበደኝ" አለ ዕዝራ ትክዝ ብሎ። ሀኪምም " ደፈር በልና ገበሰተህ አዋራት" ብሎ አደፋፈረው።

፨ ዕዝራ እሺ ብሎ ሊገባ ሲል የሀኪም ስልክ ጠራ። "ማነው?" አለ ዕዝራ ሀኪምም "እስቲ ቆይ ልየው" ብሎ ከጃኬቱ ስልኩን አውጥቶ አየውና ከቤት ነው የሚደውሉት አባትህ ናቸው" ብሎ ስልኩን አነሳው። "ሄሎ"......."ሄሎ ሀኪም ልጄ እንዴት ነህ"...... "እንዴ የዕዝራ እናት እረሶ ኖት እንዴ አልሀምዲላ"....... "ልጄስ እንዴት ነው መቼም በጣም አዝኗል አደል ሙናስ እንዴት ናት አሁን" ........... " እሷም እሱም ደና ናቸው ዕዝራ አጠገቤ ነው ያዋሩት" ብሎ ለዕዝራ ስልኩን ሰጠው። ዕዝራ "ሄሎ እማማ" አለ ለሰስ ባለ ድምፅ እናቱ "ምነው ልጄ ድምፅህ ሙና ደና ከሆነች ለምን" ብለው ወሬያቸውን ሳይጨረሱ "እማማ ሙኔን እኮ አስከፋዋት" አለ። እናቱም "ሁሉን ነገር አስሚ ለእኔ እና ለአባትህ ነግራናለች ልጄ አይዞህ ይቅርታ ጠይቃት እንደውም ከጠየካት በኋላ ደውልልኝ እና ምን እንደተፈጠረ ንገረኝ በል አሁኑኑ ስልኩን ዘግተህ ሂድ!" ዕዝራ "እሺ እማማ" ብሎ ስልኩን ዘጋው።
፨ ዕዝራ በቀስታ ወደ በሩ ተጠጋና ሀኪምን እያየው የበሩን እጀታ ያዘው ሀኪምም እንዲገባ ምልክት ሰጠው። ዕዝራ በቀስታ የበሩን እጀታ አዞሮ ከፍቶ ገባ። ሙና ወደ ላይ እያየች ነው። ጠጋ ብሎ አያት ፍጥጥ ብላ ታስፈራለች አይኑ ዋን አየው አይረገበገብም። "ሙኔ?" አላት ዝም አለች። የሲማይ አይን ትዝ አለው። የሞተች እለት የፈጠጠው ዕዝራ ደነገጠ። በድጋሜ "ሙኔ!" አላት አራቅ ብሎ መልስ የለም እየሸሻት "ሙኔ እባክሽን ተይ እንዲህ አታረጊኝ" ብሎ እራሱን ይዞ "ፈጣሪዬ በህልምህ ነው በለኝ።" አለ። በአንዴ ፊቱ እና አይኑ ቲማቲም መሰለ። መጫህ ሁሉ አቃተው ጩሆ ሰው መጣራት አቃተው እጁም እግሩም አፉም ተሳሰረ።





ክፍል 37 (ሰላሳ ሰባት)ይቀጥላል
#share
@achacher
149 viewsɖąཞƙŋıɧą, 19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ