Get Mystery Box with random crypto!

ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ ስለታሪኩ ብርሃኑ (ባባ)... 'እስከ መች ኢንተርቪው እንቢ ትላለህ ? አንተ | ዳሰሳ አዲስ-Access Addis

ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ ስለታሪኩ ብርሃኑ (ባባ)...

"እስከ መች ኢንተርቪው እንቢ ትላለህ ? አንተ እኮ በዚህኛው ዘመን ላለው የሀገራችን ፊልም ቀለም ከሆኑ ወጣት አርቲስቶች አንዱ ነህ ፡ በጣም ብዙ አድናቂዎችህ ፡ ያንተን ፈለግ መከተል የሚፈልጉ ወጣቶች ስላንተ ማወቅ መስማት ይፈልጋሉ

አዱ ግድ የለህም ይለፈኝ በዚህ ጉዳይ ከሰይፉም ጋር ተጨቃጭቀናል እኔ ሚዲያ ላይ መቅረብ ብዙም አልወድም ፡ ፊቴ መቀያየሩን ሲያይ አዱ ተክልዬን ከደበረ ኢንተርቪውን ዝም በለን እንስራው እና አንድ ቀን ደስ ካለኝ አሁን አስተላልፈው እልሃለው

ለኔ ስትል ከሆነ አሁን ይቅርና ደስ ያለ ቀን ኢንተርቪው ትሰጠኛለህ አልኩት

እንቢ ሲለኝ ደብሮኝ ነበር ቀርፀን እናስቀምጠው ያለኝን እሺ ባለማለቴ ደግሞ የበለጠ እንድከፋ አድርጎኛል