Get Mystery Box with random crypto!

EGC SCHOLARSHIP NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ academic_learn — EGC SCHOLARSHIP NEWS E
የቴሌግራም ቻናል አርማ academic_learn — EGC SCHOLARSHIP NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @academic_learn
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.99K
የሰርጥ መግለጫ

Purposes of the Channel
👉 Relevant Scholarships News 🥳
👉 Scholarships Related Tips 😃
👉 Blogs and Videos 😊
👉 Various Opportunities 🤩
For Any Scholarship Related Support Visit Our Website
: Www.Ethio-Genuine-Consultancy.com

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 09:04:56
Woldia University

በጦርነቱ ምክንያት የወልዲያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ መሆኑን ከቤተቦቻችን የደረሰን መረጃ ያሳያል ።

"የወልደያ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ውጡ ተብለው ግቢውን ለቀው በእግራቸው እየሄዱ ነው።
ሮቢት እና ገንደመዩ ላይ ውጊያው እንደቀጠለ ነው።"

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

https://t.me/Academic_learn
375 views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:34:05 የ 12ኛ ክፍል ፈተና በ 2ት ዙር ይሰጣል።

1ኛ ዙር---Social Science ከ መስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3

2ኛ ዙር ---Natural Science ከ ጥቅምት 8 እስከ 11

በዚህ አመት 984,000 በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፈል ፈተናን ይወስዳሉ።

Social Science .......622,739 ናቸው።

Natural Science.....361,279 ናቸው።

Share
@Academic_learn
804 views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:02:57 #Update

የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ለዚህም ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ #ለኦቢኤን በሰጡት ቃል ፤ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ያላቸው በመሆኑ በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 /2015 አስቀድሞ ፈተናው እንደሚሰጣቸው አቶ ረዲ ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ደግሞ 361,279 ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩ የፈተና ችግሮችን ለመፍታት ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ፤ ፈታኞቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም ፤ ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ማለቱን ገልፀዋል።

ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

@Academic_learn
685 views17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 20:52:46 የ 2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በ 2'ት ዙር ይሰጣል።

ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች እስከ መስከረም 28 ድረስ መደበኛ እና የክረምት ተማሪዎችን ወደ ቤት ይሸኛሉ።

ከ መስከረም 30 እስከ ጥቅምት 17 ባሉት ቀናት ሁለቱም ዙር ፈተና ይሰጣል። ለምሳሌ:- አንደኛ ዙር ፈተና ከ ጥቅምት 4--7 ብሰጥ ከዛ እነዚህ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ይወጣሉ። ከዛ ጥቅምት 9 እና 10 የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርስቲው ይገባሉ። ከዛ ከ ጥቅምት 11--14 ሁለተኛ ዙር ፈተና ይሰጣል ማለት ነው።

ይህ የሆነበት ሁኔታ የተፈታኞች ቁጥር ብዙ ስለሆነ ዩኒቨርስቲዎች በአንድ ጊዜ ማስተናገድ ስለማይችሉ ነው።

ስለዚህ ፈተናው ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ዩኒቨርስቲ ብቻ ስለሚሄድ እንዳይሰረቅ እና ውዝግብ እንዳይፈጥር ጥብቅ ቁጥጥር ይኖራል።

@Academic_learn
1.3K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 12:47:23 #MoE

" የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 /2015 ዓ/ም ጀምሮ በ2 ዙር እንዲሰጥ ታቅዷል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ2ዐ14 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ #በሁለት_ዙር እንዲሰጥ መታቀዱን በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተፈርሞ ለ42 ዩኒቨርሲቲዎች በተላከውን እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትክክለኛነቱን ባረጋገጠው ደብዳቤ መመልከት ችለናል።

በዚሁ መሠረት ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ዩኒቨርስቲዎች ፦

1. ምንም አይነት የመደበኛ ተማሪ በግቢ እንዳይኖር እንዲያደርጉ፤

2. በቀጣይ በሚገለጸው ተማሪ ቁጥር ልክ ምግብ እንዲቀርብ ዝግጅት እንዲያደርጉ፤

3. ለፈተናዎች ማቆያ ቦታ እንዲዘጋጅ እና

4. የፈተናውን አሰጣጥና ደህንነት የሚቆጣጠር በፕሬዚዳንት የሚመራ ዋና ግብረ-ኃይልና በየካምፓሶቹ በዲን /ካምፓስ ኃላፊ የሚመራ ንዑስ ግብረ-ኃይል እንዲያደራጁ መልዕክት ተላልፎላቸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የ2ዐ15 የአካዳሚክ ካላንደር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወቅት (ከመስከረም 28 - ጥቅምት 17) ታሳቢ በማድረግ እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አሳስበዋል።

@Academic_learn
942 views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 00:27:48 ማሳሰቢያ

ለሁሉም የትምህርት ተቋማት
አዲሱ ስርዓተ ትምህርት አተገባበር በተመለከተ አጭር ማብራሪያ


አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ2015 ዓ.ም ጀምሮ ከ1ኛ_8ኛ ክፍል ተግባራዊ ይደረጋል።

አዲሱ የመፀሀፍት ህትመት እንዳለቀ ለትምህርት ቤቶች ይሠራጫል

በሳምንት የሚሠጠዉ የክ/ግዜ ብዛት 35 ነዉ።

የክፍለ ግዜ ስርጭት በቅርቡ ይላካል

7ኛ እና 8ኛ ክፍል ICT ትምህርት ስለሚሰጥ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይገባል።

ቅድመ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ይካሄዳል።

ነባሩን ስረዓተ ትምህርት መፀሀፍት በ2015 ዓ.ም ማስወገድ አይቻልም ።አወጋገዱን በተመለከተ ትምህርት ቢሮ አቅጣጫ ያስቀምጣል።

አዲሱ የስረዓተ ትምህርት መፀሀፍ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ለመምህራን የማስተዋወቅ ስራ ይሠራል።ቀኑ ወደፊት ይገለጻል።
የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከነሀሴ 3 ጀምሮ ከአዲስ አበባ ትምሀርት ቢሮ መፀሀፍ መግዛት ይችላሉ።

Via የካ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት
@Academic_learn
775 views21:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 14:02:57 ማንኛውም የግል ትምህርት ቤት መፅሃፍም ሆነ ደብተር መሸጥ እንደማይችል ማሳሰቢያ ተሰጠ

አንድ የትምህርት ተቋም ፍቃድ የተሰጠው ለማስተማር እንጂ፤ መጽሐፍም ሆነ ደብተር ለመሸጥ አይደለም ሲል የ #አዲስአበባ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ማንኛውም የግል ትምህርት ቤቶች ከመመሪያ ውጪ ያልተገባ ክፍያ አስከፍለው በተገኙ ተቋማት ላይ ርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።።

በመመሪያ አተገባበሩ ላይ የተለያዩ ጥቆማዎች እየደረሱ እንደሚገኝም ኃላፊዋ አክለዋል። በመመሪያ አተገባበሩ ላይ ከመጡት ጥቆማዎች ውስጥ አንዳንድ ተቋማት የምዝገባ ክፍያ መጨመር፣ በዓይነት መቀበል ለአብነት እሽግ ወረቀት እና የመፀዳጃ ቤት የንፅህና እቃዎችን የሚጠይቁ እንዳሉበት ገልፀዋል።

በተጨማሪም ባልተፈቀደ ክፍያ ጭማሪ እያደረጉ ያሉ የትምህር ተቋማት እንደሚገኙ ጥቆማ ደርሶናል ወርደን እናስተካከልን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ማንኛውም የግል ትምህርት ቤቶች ከመደበኛ ክፍያ ውጪ በየትኛውም መልኩ ክፍያ ማስከፈል አይቻሉም፤ አንድ የትምህርት ተቋም ፍቃድ የተሰጠው ለማስተማር እንጂ መጽሐፍም ሆነ ደብተር ለመሸጥ አይደለም ብለዋል።ከተሰጠው ፍቃድ ውጪ ሲንቀሳቀስ በሚገኝ ተቋም ላይ ርምጃ ይወሰድበታል፤ የሰበሰበውን ገንዘብም ሆነ ማንኛውንም አይነት ቁሳቁስ እንዲመልስ ይደረጋል ሲሉ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

#share_please
Invite your friends
@Academic_learn
657 views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 14:02:57 Advanced Synonyms

Very calm ― Screen
Very ugly ― Hideous
Very small ― Petty
Very funny ― Hilarious
Very quiet ― Hushed
Very rich ― Wealthy
Very expensive ― Costly
Very dirty ― Filthy
Very tall ― Towering
Very easy ― Effortless
Very wet ― Soaked
Very slow ― Sluggish
Very good ― Excellent
Very stupid ― Idiotic
Very happy ― Ecstatic
Very exciting ― Exhilarating
Very warm ― Hot
Very weak ― Frail
Very little ― Tiny
Very bright ― Luminous
Very busy ― Swamped
Very careful ― Cautious
Very clear ― Obvious


SHARE SHARE
╔════════════
JOIN: @Academic_learn
JOIN: @Academic_learn
610 views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 18:28:06
"የሚገነቡት ትምህርት ቤቶች ዘመናዊና የወደፊቷን ኢትዮጵያ የሚመስሉ ናቸው" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፤ የትምህርት ሚኒስትር

...................................................................................

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጦርነቱ ከወደሙ ትምህርት ቤቶች መካከል በሰሜን ወሎ ዞን በሐብሩ ወረዳ በመርሳ ከተማ መልካ ጨፌ ትምህርት ቤት ግንባታ መሠረት ድንጋይ ተቀመጧል፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በአማራ እና አፋር ክልል ሙሉ በሙሉ የወደሙ 1ሺሕ 300 ትምህርት ቤቶችን በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ ለመገንባት መታቀዱን አንስተዋል።

የሚገነቡት ትምህርት ቤቶችም ዘመናዊና የወደፊቷን ኢትዮጵያ የሚመስሉ ናቸው ብለዋል።

የትምህርት ጥራትን ለማሻሻልና የተቋማቱን ደረጃ የማሳደግ ሥራ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በትኩረት እየሠራ መሆኑንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአማራ ክልል 8 ትምህርት ቤቶችን በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚገነባውን ሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅትም አመስግነዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪ ጋሻው አስማሜ በበኩላቸው አሸባሪው ሕወሓት የሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ 777 ትምህርት ቤቶች ላይ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ውድመት ማድረሱን ገልጸዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ፣ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የኢትዮጵያ አገር አቀፍ ተጠሪ አቶ ይልማ ታዬን ጨምሮ የሀብሩ ወረዳ እና የመርሳ ከተማ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም መምህራን እና ተማሪዎች ተገኝተዋል።
584 views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 09:25:25
ነፃ የትምህርት ዕድል !

የሳንድፎርድ ኢንተርናሽናል ት/ቤት በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር በሚገኙ የመንግሥት ት/ቤቶች በመማር ላይ ከሚገኙ #በትምህርታቸውና #በፀባያቸው የተመሰከረላቸውን ተማሪዎች አወዳድሮ የነፃ ትምህርት ዕድል ለመሥጠት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አሳውቆናል።

ተወዳዳሪ ተማሪዎች ለነፃ ትምህርቱ ውድድር ለመመዝገብ ሲመጡ የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልተው የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት መግለጫ ኮፒ ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል።

1. በአ/አ ከሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተማሪ መሆን

2. ተማሪው የተወለደው እ.ኤ.አ ነሐሴ 31/2008 ድረስ 14 ዓመት የሚሞላዉ ነገር ግን 15 ዓመት በታች የሆነ ይህንንም የሚያረጋግጥ የልደት የምሥክር ወረቀት ይዘው መቅረብ የሚችሉ

3. በ2014 የትምህርት ዘመን መጨረሻ የ8 ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አማካይ ወጤት ከ95% በላይ የሆነ

4. የ7ና 8 የክፍል ትምህት ለየብቻው አማካይ ውጤቱ ከ90% በላይ የሆነ

5. ስለመልካም ሥነምግባሩ ወይም ፀባዩ ከሚማርበት ት/ቤት የጽሁፍ ማስረጃ በሳንድፎርድ ተቀባይነት ሲያገኝ ማምጣት የሚችል

6. ት/ቤቱ የሚሰጠውን የመግቢያና ቃለመጠይቅ ፈተናዎችን የተሻለ ዉጤት ማስመዝገብ

7. የወላጅ/የአሳዳጊ ሙሉ ፈቃድ ያገኘ

8. አሸናፊ የሚሆነው ተማሪ በአሥረኛ (10) ክፍል በት/ቤቱ ተመዝግቦ ለመማር ፈቃደኛ የሆነ ናቸዉ።

9. የምዝገባ ሰዓት ጠዋት 2፡30 - 6:00 ከሰዓት ከ7:30 - 9:30

መስፈርቱን ያሟሉ ተማሪዎች ነሐሴ 19/2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ለፅሁፍ ፈተና ይቀርባሉ።

ቦታ፦ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል አካባቢ በሳንድፎርድ ት/ቤት እስከ ነሐሴ 18 ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይቻላል።
536 views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ