Get Mystery Box with random crypto!

የዋስትና መብት መከበር ላይ በፖሊስ የሚቀርብ የይግባኝ ጥያቄ ህጋዊ አንድምታው ሲገመገም በ፡ ንጉሴ | abyssinialaw.com

የዋስትና መብት መከበር ላይ በፖሊስ የሚቀርብ የይግባኝ ጥያቄ ህጋዊ አንድምታው ሲገመገም
በ፡ ንጉሴ ረዳይ

ፖሊስ ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቅ የወሰነለትን ሰው አለቅም ለማለት የህግ መሰረት አለው ወይ? በዋስትና ጉዳይ ላይ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ ፖሊስ ለበላይ ፍርድ ቤቶች ይግባኝ እንዲያቀርብ የሥነ-ስርዓት ህጉ ይፈቅዳል ወይስ አይፈቅድም? እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት፤ የወንጀለኛ መቅጫ የሥነ-ስርዓት ህግ እና ሌሎች ህጎችን ለማየት ተሞክሯል። በመጨረሻም ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በጎላ መልኩ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እየታየ የሚገኘው የፖሊስ አሰራር የተያዙ ሰዎችን ህገ-መንግስታዊ መብት የሚጥስ እና በቂ የህግ መሰረት እንደሌለው ክርክር ቀርቧል።

የዚህ አጭር የፁሁፍ ምልከታም ይህንን ህገ-መንግስታዊ መብት የሆነውን የዋስትና መብት አፈፃፀምን በተመለከተ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይም በፖሊስ በኩል ፍርድ ቤቶች የዋስትና መብት ላይ የሚያሳለፏቸው ብይኖች ላይ፤ ብይኑን አላስፈፅምም ይግባኝ እላለሁ በሚል በሚቀርቡ የይግባኝ አቤቱታዎችን ለመገምገም ያለመ ሲሆን የእነዚህ ይግባኞችን የህግ መሰረትም ይፈትሻል።

https://www.abyssinialaw.com/blog/the-legal-implications-of-an-appeal-submitted-by-the-police-on-the-enforcement-of-the-right-to-bail