Get Mystery Box with random crypto!

መታወቂያ ለተዘጋጀላችሁ የፌደራል ጠበቆችና የህግ አማካሪዎች ************************ | abyssinialaw.com

መታወቂያ ለተዘጋጀላችሁ የፌደራል ጠበቆችና የህግ አማካሪዎች
****************************

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር አዲስ አበባን ጨምሮ በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የፌደራል ጠበቆችን ምዝገባና መረጃዎችን የማደራጀት ተግባራትን ለተከታታይ ወራት ሲያከናውን መቆየቱ የሚታወስ ነው::

የጠበቆች ማህበሩ ከዚሁ ጎን ለጎን ለፌደራል ጠበቆችና የህግ አማካሪዎች መታወቂያ ዲዛይን አጠናቅቆ በህትመት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ በታች ስማችሁ የተዘረዘረ ጠበቆች አዲሱ መታወቂያችሁ የተዘጋጀ በመሆኑ ከፒያሳ ከፍ ብሎ ባለው የፍትህ አካላት ህንፃ (አራዳ የፌ/ከ/ፍ/ቤት ያለበት) 9ኛ ፎቅ ባለው የማህበሩ መ/ቤት ከዛሬ ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት በአካል እየቀረባችሁ እንድትወስዱ እናሳውቃለን::

መረጃው ላልደረሳቸው እንዲደርስ የማህበሩን ኦፊሴል የፌስ ቡክ ገፅ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
መጋቢት 26 ቀን 2015
አዲስ አበባ