Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅርን በትዳር ውስጥ: #እጠብቅሻለሁ ምንም ነገር ብሆን ፈተና ቢበዛ፣ አላህ የፈቀደው እለት እ | ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ

ፍቅርን በትዳር ውስጥ:
#እጠብቅሻለሁ

ምንም ነገር ብሆን ፈተና ቢበዛ፣
አላህ የፈቀደው እለት እስኪመጣ፣
እጠብቅሻለሁ ጣጣም አላባዛ፣



#ከተራራው_ማዶ

ከዚያ ከወዳኛው ከተራራ ማዶ፣
ከአድማሱ ሰፈር የሩቅ ሰውን ወዶ፣
ትዳር ሲመሰረት በፍቅራት ደምቆ፣
ይኖራል ያቤቱ ከጨለማ ወጥቶ።



ቆይ ቆይ ቆይ
#ሚስት በሏን ማወደስ የለባ ትም ያለው ማነው


የህይወት አካሌ
የግማሿ ግማሽ የሲሶዋ ሲሶ፣
የህይወት አካሌ ዋልታና ምሰሶ፣
ከሀራም ያ"ራከኝ የትዳር ቀን ደርሶ፣
ሁሌ እወድሀለሁ ልቤ ፍቅር ይዞ።

ፍቅርህ የኔ ፍቅር ሁለቱም አብቦ፣
በአይኔ ባየሁት አበባው አፍርቶ።


#ትዳር_እንድህ
እንደቀልድ


" አንዳንድ ወንዶች ትዳር እንደ ግሩፕ መስሏቸው ጆይን (join) ብለው ይገቡና ከወራቶች በኋላ ሊፍት ብለው ይወጣሉ።" ይላል

ያነበብኩት ፖስተር።

ትዳር እንድህ እንደ ቀልድ ከተያዘማ፣
አወ ሁሉም ቀሪ ነው ሳይ ወጣ ማማ።


#ግን_ትዳር
የነብያት ሱና
የአላህ ገፀበረከት
የፍቅር ዋልታ ማገር፣
የኢማን ማሟያ መስመር፣
የልጆች ማፍሪያ ሰፈር፣
የህይወት መምሪያ ቀመር፣

መሆኑን ለተረዳ የትዳር ጣእም ለናፈቀው፣
ከላይ ያለው አበባል ለሱ ምንም አይገልፀው።



#አረንጓዴ_አሻራ


"ለባሏ አረንጓዴ አሻራ ያስቀመጠች ማለት ጥብቅ ሆና የተገኘች እንስት ናት።"

#ከአንዲት_ሰለፍይ_እንስት_ያገኘሁት ፁሁፍ #አላህ_ይጠብቃት

እርግጥም እውነት አለች
ነፍሷን ለአላህ የገበረች፣
ከሰይጣን ጉትጎታ የራቀች፣
ከስሜት አሉቧልታ የተጥራራች፣
ጥብቅ ሆና በጥብቅነት የኖረች፣
የማይናወጥ ክብር ከባሏ ልብ የፃፈች፣
ከአላህ ዘንድ ተወዳጂ ሆና ከሰው ዘንድ የተወደደች፣
እሷናት የእውነትም አረንጓዴ አሻራ ያስቀመጠች።



#በሳር_ቤት_ጎጆዬ



እንደዘመነኛው ቪላቤት ባይኖረኝ፣
ኮከብ የሚመስለው መብራት ባይገባልኝ፣
ሳሎን አልጋቤቱ የሸዋር ባይኖረኝ፣
እቃቤቱ ሳይኖር ክፍሌ እንኳ ብጠበኝ፣

ከተወሂድ ከሱና ከዲን ጋር የኖረች፣
የአይን ማረፊያ እንቁ ሚስት ካለች
የሳር ቤት ጎጆዬ ምንም አትበድለኝ።

ያ የአላህ ባሪያ እንቁው አሽረፈል ሀልቅ፣
(ሱለሏሁ አለይሂ ወሰለም)
ሲኖሩ እንዴት ነበር ትዳራቸው ሲደምቅ

ህይወታቸው ሁሉ በመብቃቃት ሲዘልቅ፣
እስቲ ዘወር ብሎ ይሻላል መጠየቅ፣
እነዚያ ሶሀቦች የኖሩትን ህይወት፣


ሰለፍይ እኮነኝ ብለን ለምናስብ ፣
የእውነት እንሁን እንተግብረው ከልብ፣
ነጃ እንወጣለን በጋብቻ ሰበብ።

=========================

አቡ ተቅይ ቃዒድ
========================
ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል
https://t.me/AbuTeqiyPomeChannel

ግሩፕ
https://t.me/PomeChannelGroup

ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ፔጅ - Home
https://m.facebook.com/KunSelefiyeAllMineOfIniformation/?ref=bookmarks

የፌስቡክ ግሩፕ
https://facebook.com/groups/717908414984387/