Get Mystery Box with random crypto!

ጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያም

የቴሌግራም ቻናል አርማ abunehabtemariyamtsdik — ጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያም
የቴሌግራም ቻናል አርማ abunehabtemariyamtsdik — ጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያም
የሰርጥ አድራሻ: @abunehabtemariyamtsdik
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.13K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ #ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ #ሀብተ ማርያም ታሪክ ፣ ገድል ፣ ተአምራት እና መልክዕ እንዲያገኙ ይቀላቀሉ።
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን የጻድቁ ቤተሰብ ይሁኑ
👇👇👇👇👇👇👇
@AbuneHabtemariyamtsdik
@AbuneHabtemariyamtsdik
👆👆👆👆👆👆👆
Contact @yordanos_26

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 05:50:54 #አቡነ_ሀብተማርያም

ታላቁ ጻድቅ አባታችን አቡነ ሀብተማርያም የተወለዱት በመንዝ አውራጃ ልዩ ስሙ የራዊ በተባለ ቦታ ሲሆን የአባታቸው ስም ፍሬ ብሩክ የእናታቸው ስም ዮስቴና ይባላል፡፡ ሁለቱም በሕግ ጋብቻ ጸንተው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው ምግባር ቱሩፋት ሰርተው በንጽህና በቅድስና ይኖሩ ነበር፡፡ ሆኖም ልጅ አለነበራቸውም፡፡ በዚህ ሁኔታ ያዘኑ ቅድስት ዮስቴና ማለት እናታቸው መንነው በአከባቢያቸው ከሚገኝ ጫካ ውስጥ ዋሻ ፈልገው ገብተው ዘጉ፡፡ በዚያም አንድ መናኝ መነኩሴ አግኝተዋቸው እግዚአብሔር በቅድስቲቱ ያለው ድብቅ ነገር ስለገለጠላቸው አንቺ ለምንኩስና የተፈቀደልሽ አይደለሽም ወደ ቤትሽ ግቢ ጸሎቱ ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ሰው ሁሉ የሚማጸነው ስሙ፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የሚነገርለት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ አሏቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ድንቅ ተዓምር የሰሙ ቅድስት ዮስቴናም እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቤቸው ተመለሱ፡፡

የተናገረውን የማያስቀር አምላክ በቸርነቱ ጎበኛቸውና ነሐሴ 26 ቀን ጸነሱ፡፡ ግንቦት 26 ቀንም ደም ግባታቸው እንደ ንጋት ኮከብ ያማሩ ሀብተማርያም ተወለዱ፡፡ እግዚአብሔር ለቅድስና ሥራ ስለመረጣቸው በእናተቸው ጀርባ ታዝለው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው በሕጻን አንደበታቸው ከቀዳሹ ካህን ጋር “እግዚኦ ማሐረነ ክርስቶስ” በማለት ይጸልዩ ነበር፡፡ ባደጉም ጊዜ ይህን ጸሎት ደጋግመው ይጸልዩ ነበር፡፡ ላባቸውም እስኪንጠባጠብ ድረስ በመስገድ ይጋደሉ ነበር፡፡ አንድ ቀንም ከአባታቸው ጎን እንደ ተኙ በድንገት እግዚአብሔር በድምጽ “ሀብተማርያም ሆይ! አንተን የተመረጠ ዕቃ አድርጌሃለሁና ቃሌን ለተመረጡ ሰዎች ተናገር” አላቸው፡፡ ይህን ግን የተበሰረላቸው የቤተሰቦቻቸውን ከብቶች በሚጠብቁበት ጊዜ ነበር፡፡ እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ አባታቸው ትምህርት ቤት አስገቡአቸው፡፡ ለአቅመ አዳም በደረሱ ጊዜ ሚስት አጩላቸው፤ እርሳቸው ግን የድንግልናን ህይወት በመምረጥ ከወላጃቸው ቤት ኮብልለው ገዳም ገቡ፡፡

“ልጄ ሆይ እራስህን ለእግዚአብሔር ታስገዛ ዘንድ ወደ ገዳም ብትሄድ ሰውነትህ ለመከራ አዘጋጅ፡፡”
መጽሐፈ ሲራክ 2፡1.

በዚያን አባ ሳሙኤል ለሚባሉ በረዳትነት ሲያገለግሉብዙ ገቢረ ተዓምራት ተደርጎላቸዋል፡፡ ዛሬ ይሰበይ ገዳም ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ለሦስት ወራት ጽሙድ እንደበሬ ትጉህ እንደ ገበሬ እንዲሉ በጾም በጸሎት ተጠምደው ሳለ መታሰቢያህን በዚህ ዋሻ አደርግልሃለሁ በማለት እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ጊዜ እረፍታቸው በደረሰ ጊዜ ጌታ ተገልጦላቸው ስለ ተጋድሎአቸውና ስለንጽህናቸው ሳባት አክሊል እንደሚቀበሉ ነግሯቸዋል፡፡
በ490 ዓ.ም ህዳር 26 ቀን ዐርፈው በደብረሊባኖስ ገዳም መካነ ቅዱሳን ቀበሯቸው፡፡
የአባታችን የጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም ረድኤት፣ በረከት፣ ምልጃና ቃል ኪዳናቸው አይለየን፡፡


#አቡነ #ተክለሃይማኖት አና #አቡነ #ሀብተማርያም
ያን ጊዜ ክቡር የሆነ #አቡነ_ተክለሃይማኖት ጠርቶኝ ልጄ ሀብተማርያም ሆይ ፈጣሪየ እግዚአብሔር ስለ ወደደህ ብዙ ምህርኮ እንደአገኝህ በአንተ ፈጽሞ ደስ ይለኛል አለኝ ፤ ነገር ግን የሞለምንክ አንድ ነገር አለና እሽ በለኝ ቢለኝ አቤቱ ጌታዩ ምንድን ነው ነገሩ አልሁት ፣ ክቡር አባታችን አባ ተክለሃይማኖትም ከተቀበርኩበት ቦታ እንድትቀብር ቃል ኪዳን ግባልኝ አለኝ፤ይንን አደርግ ዘንድ ስለምን ትለምነኛለህ ብየ ብመልስለት፣ እነሆ በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስ መቅሰፍቶች አሉና ስለዚህ ነው ፤ እሊሁም አንዱ መብረቅ ነው ፣ ሁለተኛው ቸነፈር ነው ፤ ሦስተኛው የረኃብ ጦር ነው ፣ አራተኛ ወረርሽኝ ነው ፡፡ አምስተኛ የእሳት ቃጠሎ ነው ፤ የአንተ አጽም በውስጡ የተቀበረ እንደ ሆነ አጥንቴ የተቀበረባት ሀገር ከእንዚህ መቅስፍታት ትድናለች፣

ልጄ ሀብተማርያም ሆይ አንተ የማታውቀው ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሄር የተሰጠህ እኔ የማውቀው ክብር አለህና ስለዚህ ነው አለኝ ፣ ይልቁንስ እንዳልኩክ በተቀበርኩበት ቦታ እንተቀበርልኝ ቃል ኪዳን ግባልኝ ብሎ መላልሶ ማለደኝ. ✞ #ከገድላቸው

#አቡነ_ሀብተ_ማርያም በቃል ኪዳናቸው ሀገራችንን ከአምስቱ መቅሰፍታት ይጠብቁልን አሜን !

በአ.አ በዓሉ በድምቀት ከሚከበርባቸው አድባራት አንዱ በቃሌ ተራራ ደብር መድኃኒት አቡነ ሃብተማርያም ገዳም አንዱ ነው ::
አቅጣጫ አስኮ አካባቢ

#ፅንሰታቸው ነሐሴ 26
#ልደታቸው ግንቦት 26
#ዕረፍታቸው ህዳር 26

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
120 views02:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 05:50:48
#ነሐሴ26 ፅንሰቱ ለ አቡነ ሀብተማርያም ጻድቅ

ጽሩይ እምወርቅ

ጽሩይ እምወርቅ ወእምብሩር ንጡፍ ወኅሩይ እምአእላፍ ፣ ሀብተ ማርያም መልአክ ዘውገ ኪሩብ ቀሊለ ክንፍ
አማን ስሙዐ ዜና እስከ አጽናፍ፡፡

✞ እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደሰችሁ

† "ሰላም ለፅንሰትከ እማህፀነ ቅድስት #ዮስቴና
በብሥራተ ጻድቅ ባሕታዊ ሠናየ ዜና
ሀብተ ማርያም ጴጥሮስ ሐዋርያ ወልደ ዮና
መሐረኒ ምግባረ ጽድቅ ወጸግወኒ ልቦና
አፍቅሮ ቢጽ እኃሥሥ ዘምስለ ፍጽምት ትሕትና::"
(መልክአ አቡነ ሀብተ ማርያም)
116 views02:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 08:29:22
እንኳን ለጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያም በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ አሜን:፡

መዝ.96፡10
“እግዚአብሔር የቅዱሳንን ነፍስ ይጠብቃል ከሃጢአት እጅም ያድናቸዋል::”

† የጻድቁ አባታችን የሀብተማርያም ልጆች ሆይ በማስተዋል እና በማገናዘብ በዓላቶቹን አክብሩ በጠዋት እና በማታም ያለመታከት ምስጋናን አቅርቡ የእግዚአብሔር ክብር ሁሌ በሱ ላይ ይገለጻል እና ቃል ኪዳኑም ለዘለዓለም ተስፍ ይሁነን ::

† በአለም የተበተኑ በጏች የተባሉ ልጆችህ የሚጠበቅበት የእምነት ዘንግን ለጨበጠ መሐል እጅህ ሰላምታ ይገባል::ጻድቁ አባቴ ሀብተማርያም ሆይ የዚች አለም ጸጥታዋና ሰላሟ አንተ ነህ እኮ እኔን ለመውደቅ የተፍገመገምኩትን እንደብረት ዘንግ የሆነ ጸሎትህ ከወደቅኩበት መሬት ያንሳኝ ይደግፈኝ ሁለተኛም የጏሰቆለች ነፍሴን ቃልኪዳንህ አይለያት::

† ሰላም ለልብከ ለቃለ መጻህፍት ምዕራፍ ::ዘበውስቴታ ይትረከብ መራኁተ ጽድቅ ዘእደ ኬፋ::ሀብተ ማርያም መልአክ ዓቃቤ ትእዛዙ ለአልፋ ይሡቀኒ እምትንታኔ አልብየ ተስፋ::ጸውዖ ስምከ ዘአልቦ ዘለፋ::

† ኦ አምላከ አቡነ ሀብተ ማርያም ዕቀቦ ወአድኅኖ ወባልሆ እመከራ ሥጋ ወነፍስ ወእምኩሉ ተቃራኒ ወእምኩልነ ክቡር ሀብተ ማርያም ለዓለም ዓለም አሜን ለይኩን ለይኩን::

(መልክአ አቡነ ሀብተ ማርያም)
863 views05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 07:25:25 ጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያም pinned «#ግንቦት_26 ልደቱ ለ አቡነ ሀብተማርያም ጻድቅ † እንኳን ለአባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የልደት መታሰቢያ በዓል አደረሰን አደሰችሁ :: ሰላም ለጽንሰትከ እማኅፀነ ቅድስት ዮስቴና፤ በብሥራተ ጻድቅ ባሕታዊ ሠናየ ዜና፡፡ ሀብተማርያም ጴጥሮስ ሐዋርያ ወልደ ዮና፤ መሐረኒ ምግባረ ጽድቅ ወጸግወኒ ልቡና፤ አፍቅሮ ቢጽ እኅሥሥ ዘምስለ ፍጽመት ትሕትና፡፡…»
04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 07:25:16 #ግንቦት_26 ልደቱ ለ አቡነ ሀብተማርያም ጻድቅ

† እንኳን ለአባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የልደት መታሰቢያ በዓል አደረሰን አደሰችሁ ::

ሰላም ለጽንሰትከ እማኅፀነ ቅድስት ዮስቴና፤
በብሥራተ ጻድቅ ባሕታዊ ሠናየ ዜና፡፡
ሀብተማርያም ጴጥሮስ ሐዋርያ ወልደ ዮና፤
መሐረኒ ምግባረ ጽድቅ ወጸግወኒ ልቡና፤
አፍቅሮ ቢጽ እኅሥሥ ዘምስለ ፍጽመት ትሕትና፡፡

#አቡነ_ሀብተማርያም

በመራ ውዕይ (ሸዋ ፥ ቡልጋ) ከአባታቸው ፍሬ ቡሩክና ከእናታቸው ቅድስት ዮስቴና ነው የተወለዱት፡፡ ወላጆቹ በተለይም እናቱ ከማግባቷ በፊት መንና ነበር፡፡ ጻድቁን እንደምትወልድ በበቃ ባሕታዊ ተነግሯት ጻድቁን ወልዳ በጽድቅ ኑሮ ኑራ አክሊላትን ተቀብላ በክብር አርፋለች፡፡

አቡነ ሀብተማርያም በሕፃንነታቸው ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ›› ሲባል ይሰማሉ፤ በሕፃን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ ‹‹ማረን እባክህን›› እያሉ ይሰግዱ ነበር፡፡ ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ፡፡ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል፤ ጓደኞቻቸው የሌላ ሰው እሸት እየነቀሉ ሲበሉ እርሳቸው ግን አይበሉም ነበር፡፡ የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በአየር ላይ ሰቅለው አውለውታል፡፡

ወደ ት/ቤት ገብተው ትምህርትን ከቀሰሙ በኋላ ለአካለ መጠን ሲደርሱ ቤተ ሰቦቻቸው ሚስት አጩለት፤ እርሱ ግን ወደ አፋር ከአባ ሳሙኤል ዘንድ ሂዶ ለ12 ዓመታት ረድዕ ሆኖ ተቀመጠ፡፡ ከአፋርም ወደ ምኔት ወደሚባል ቦታ መጥቶ በታላቁ አባት በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሰ፤ ከአፋር ወደ ይነውፋ፥ ከይነውፋ ወደ ጉሐርብ ወደሚባል ሃገር ሂዶ ምናኔን፣ ትሩፋትንና ተጋድሎን ሠራ፡፡

ለአብነትም፤

† ባሕር ውስጥ ሰጥሞ 500 ጊዜ ይሰግዳል፤
† በየቀኑ 4ቱን ወንጌልንና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያል፤
† በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባል፤
† ምግቡ ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው፤
† በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋል፤
† ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላል፥ ክቡር ደሙን ይጠጣል፤
† በልቡ ውስጥ በፍጹም ቂምን፣ መከፋትን አያሳድርም፡፡
† የብረት ሰንሰለት በወገቡ ታጥቆ ይሰግዳል ይጸልያልም፡፡
"ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሀብተ ማርያም" የተባለላቸው ታላቅ አባታችን ናቸው ፡፡

ዲቁናን ከጳጳሱ አቡነ ይስሐቅ ዘንድ ተቀበሎ ወደ በዓቱ ተመለሰ፡፡

ኋላ ቆይቶም እንደገና ከአቡነ ይስሐቅ ዘንድ ቅስናን ተቀበለ፡፡ ወደ ጓና ወደ ምትባል ሀገርም ሂዶ ተቀመጠ፡፡ ቀጥሎም ጐላጐት ወደ ምትባል አገር ሂዶ ተቀመጠ፡፡ የአፄ ናዖድ የንስሐ አባት ነበረና ንጉሡን ያስተምረውና ይገስጸውም ነበር፡፡

ጌታችንም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቶት በዚያ እየበረረ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ተለያዩ ቦታዎች ይሔድ ነበር፡፡ ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በኋላም የክብር ባለቤት መድኀኒታችን ክርስቶስ አእላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ እንዲህ አላቸው::

"*ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: *ስለ ምናኔሕ: *ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: *ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: *ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: *ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: *ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"

"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን: 500 የዕንቊ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ: በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ በርእስየ' ብዬሃለሁ" አላቸው::

+ቅዱሳን መላእክትም "ሀብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: መላእክትም ዝማሬም ወሰዷት::

ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ሥልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነርሱም፤
፩ኛ. #መብረቅ፣
፪ኛ. #ቸነፈር፣
፫ኛ. #ረሃብ፣
፬ኛ. #ወረርሽኝ፣
፭ኛ. #የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡

በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ቦታውን ሲባርክ ሦስት አጋንንት በጸሎቱ ሥልጣን የታሠሩለት ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡

በግንቦት 26 ተወልዶ፤ በ1490 ዓ.ም. በወርኀ ኅዳር 26 ባረፈ ጊዜም፤ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማኅሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በደብረ ሊባኖስ ቀበሩት፡፡
(ከወርቅ ንፁህ ከብርም የጠራ ከሁሉ የሚበልጥ የተመረጠ ሃብተማርያም መልአክ ዘበምድር ነው መልካሙ ዜናው እስከ አጽናፍ ተሰማ፡፡)

ክብርት በሆነችው ጸሎቱና ምልጃው ይማርን ይጠብቀን፡፡
1.4K views04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 14:52:40 ክርስቶስ ተንስአ እሙታን -> በዐቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን -> አግአዞ ለአዳም
ሰላም -> እምይእዜስ
ኮነ -> ፍሰሀ ወሰላም ::

† እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደሰችሁ†
ማቴ 10:40-42
“እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።"

† † † በስመ እግዚአብሔር አብ እም ቅድመ ዓለም ዘሀሎ
ወበ ስመ እግዚአብሔር ወልድ ለስጋ ማርያም እንተ አልአሎ
ወበ ስመ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እምኔሆሙ በኢሰስሎ
ኢየኃስድ ሰሌላዳ ስሙ ከመ እጽሐፍ ፊደሎ
ለዘ እም ኃበ አልቦ እሎንተ ዘአምጽአ ኩሎ::

†ሰላም ለጽንሰትከ እማህፀነ ቅድስት ዮስቴና
በብሥራተ ጻድቅ ባሕታዊ ሠናየ ዜና
ሐብተ ማርያም ጴጥሮስ ሐዋርያ ወልደ ዮና
መሐረኒ ምግባረ ጽድቅ ወጸግወኒ ልቦና
አፍቅሮ ቢጽ እኃሥሥ ዘምስለ ፍጽምት ትሕትና::

(መልክአ አቡነ ሀብተ ማርያም)

ረድኤት በረከቱ አይለየን ::

@AbuneHabtemariyamtsdik
1.2K views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 17:07:13
† እግዚአብሔር የቅዱሳንን ነፍስ ይጠብቃል ከሃጢአት እጅም ያድናቸዋል::†
መዝ.96፡10

እንኳን ለታላቁ ጸድቅ ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም በዓል እና ለዓብይ ጾም በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ::

ጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም በፈሪሃ እግዚአብሔር በትምህርት አደገ፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን ካህናቱ በቤተክርስቲያን ምህላ ሲያደርሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" እያሉ ሲፀልዩ ሰምቶ በልቡናው ይህች ፀሎት በጣም ጥሩና መልካም ፀሎት ናት አለ በዚህ ፀሎት ከዓለም አሳችነት ከገሃነም እሳት እንድንባት ዘንድ አውቃለሁ የንስሐ መንገድ ናት ብሎ ተናገረ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አባታችን አቡነ ሀብተማርያም በዚህች ፀሎት ተጠምዶ በጾምና በፀሎት በስደት የሚኖር ሆነ::
(ገድለ አቡነ ሀብተ ማርያም)
1.5K views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-03 13:27:10
† እግዚአብሔር የቅዱሳንን ነፍስ ይጠብቃል ከሃጢአት እጅም ያድናቸዋ፡ † መዝ.96፡10

#እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ አሜን፡፡

የጻድቁ አባታችን የሀብተማርያም ልጆች ሆይ በማስተዋል እና በማገናዘብ በዓላቶቹን አክብሩ በጠዋት እና በማታም ያለመታከት ምስጋናን አቅርቡ የእግዚአብሔር ክብር ሁሌ በሱ ላይ ይገለጻል እና ቃል ኪዳኑም ለዘለዓለም ተስፍ ይሁነን ::

“ምግባሩ የተወደደ የሆነ የጸድቅ ባህታዊ ብስራት የተጸነስክበት የእናትህ የዮስቴና ማህጸን በእውነት ሰላምታ ይገባል፡፡ጻድቁ አባቴ ሀብተማርያም ሆይ እንደዮና ልጅ እንደ ጴጥሮስ የእውነት ሥራን አስተምረኝ አይነ ልቦናዬንም አብራልኝ ፍጽምት ከሆነች ትህትና ጋር ባልንጀራኤን እንደራሴ እወድ ዘንድ፡፡”


ኦ አምላከ አቡነ ሀብተ ማርያም ዕቀቦ ወአድኅኖ ወባልሆ እመከራ ሥጋ ወነፍስ ወእምኩሉ ተቃራኒ ወእምኩልነ ክቡር ሀብተ ማርያም ለዓለም ዓለም አሜን ለይኩን ለይኩን::
1.4K views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-04 08:16:00 “ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ፡፡"
መዝ 111/112፡6

እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ አሜን፡፡

ሰላም ለዝክረ ስምክ

በዃለኛው ዘመን የዚህን ዓለም ረሃብና ጥም የሚያስረሳና ከወይን ዘለላ ይልቅ ለሚወደድ ስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ህጻን የሆነ የማርያም ልጅ ወዳጅ ጻድቁ አባቴ አቡነ ሀብተ ማርያም ሆይ በቦታው ታርፍለት ዘንድ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጥብቆ እንደ ለመነ እኔም አገልጋይ ከሀዘን ሁሉ ታድነኝና በቤቴም ታርፍ ዘንድ እለምነሃለሁ፡፡

#ለሀገሪትነ ሰላማ ኪያከ ተሀቅብ /፪/
አባ ኦ አባ /፪/ አቡነ ሀብተማርያም /፪/ አባ
1.5K views05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-05 13:40:06 ጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያም pinned «#ኅዳር_26 ዕረፍቲሁ ለ አባ ሀብተ ማርያም ጻድቅ “ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ፡፡” መዝ 111/112፡6 ✞ እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ አሜን፡፡ ✞ ሰላም ለመቃብሪከ ከፀሎትና ከገል ብዛት የተነሳ እግሩ የተሰበረ የአባታችን የተክለ ሃይማኖት ገዳም በሆኑት ደብረ ሊባኖስ ውስጥ ለሆነች መቃብርህ ሰላምታ ይገባል:: ጻድቁ…»
10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ