Get Mystery Box with random crypto!

ከንቲባ አዳነች አቤቤና ካቢኔያቸው ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝተዋል። ከንቲባዋና ካቢኔያቸው ዛ | አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)

ከንቲባ አዳነች አቤቤና ካቢኔያቸው ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝተዋል።

ከንቲባዋና ካቢኔያቸው ዛሬ የካቲት ፰ ቀን ፳፻ ወ፲፬ ዓ.ም በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ የተገኙት ቋሚ ሲኖዶሰሰ የካቲት ፬ ቀን ፳፻ ወ ፲፬ ዓ.ም በመስቀል አደባባይ፣ በወይብላ ማርያም ጉዳይ፣ በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀትና በሌሎች የቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች ዙሪያ ተወያይቶ አሉ የሚባሉ ችግሮችን በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ለመፍታት ይዞት የነበረው ቀጠሮ በወቅቱ የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ስብሰባ ስለነበረውና ከንቲባዋም በዚያ መገኘታቸው የግድ ስለሆነ ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር የነበረው ቀጠሮ ለዛሬ እንዲተላለፍ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና ከአስተዳደሩ የተወከሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአካል ተገኝተው ለቋሚ ሲኖዶስ በገለጹት መሰረት የውይይቱ ጊዜ ለዛሬ እንዲተላለፍ መደረጉ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ከንቲባዋና የካቢኔ አባላቶቻቸው ዛሬ የካቲት ፰ ቀን ፳፻ ወ፲፬ ዓ.ም በሰዓቱ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ሲሆን ከቋሚ ሲኖዶስ አባላት በተጨማሪ ሌሎች ብፁአን ከባቶች፣የሕግ ባለሙያዎች፣ከመምሪያ ኃላፊዎች ጋር በሚያደርጉት ውይይትም አሉ የሚባሉና ቤተክርስቲያን የምታቀርባቸው ጥያቄዎች ሁሉ ፍጹም ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ መፍትሔ የሚያገኝበትን ሁኔታ ይፈጥራሉ ተብሎ ይገመታል።

ከዚህ ቀደም በቋሚ ሲኖዶስ አባላትና በከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ መካከል ሊደረግ የታሰበው ውይይት በተለያዩ ምክንያቶች እንቅፋት እየገጠመው መቆየቱ ይታወሳል።
ምንጭ፡-የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation,EOTC