Get Mystery Box with random crypto!

የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ abuhyder — የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
የቴሌግራም ቻናል አርማ abuhyder — የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
የሰርጥ አድራሻ: @abuhyder
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.46K
የሰርጥ መግለጫ

ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-05-02 23:42:22 ሸዋልን አደራ!

በአቡ ሀይደር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት የአላህ ባሮች ይሁን፡፡

የሸዋል ወር በእስልምናው አቆጣጠር ከረመዷን ቀጥሎ የሚመጣ 10ኛ ወር ነው፡፡ ሸዋል የወሩ ስም እንጂ በወሩ ውስጥ የሚፆመውን 6ቀናት የሚመለከት ስም አይደለም፡፡ ይህ ወር እንደተቀሩት 11 ወራቶች እሱም 29/30 ቀናት አሉት፡፡ በዚህ ወር ውስጥ ደግሞ 6ቀናትን በማከታተልም ይሁን በማፈራረቅ መፆም እጅግ ተወዳጅ ነው፡፡ ዋጋውም (አጅሩም) በአሥር በመባዛት የስልሳ ቀን (ሁለት ወር) ፆምን አጅር ያስገኛል፡፡ ከረመዷን አንድ ወር ፆም (አሥር ወር አጅር) ጋርም በመደመር የአንድ ሙሉ ዓመት ፆም ምንዳ(ክፍያ) ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ አላህ ይቀበለን፡፡ ይህንን በተመለከተም አሽረፈል ኸልቅ (የፍጥረቱ ሁሉ የበላይ) የሆኑት ነቢዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ በማለት አስተምረዋል፡፡ ኡመታቸውንም አነሳስተዋል፡-
"የረመዷንን ወር ጹሞ ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ነው" (ሙስሊም 1164)፡፡

ስለዚህም የሸዋል ወር ፆም ረመዷንን የፆመ ሙስሊምን ሁሉ ይመለከታል ማለት ነው፡፡ የአዋቂዎችና የአባቶች ፆም ነው በማለት ሌላው አካል መዘናጋት የለበትም፡፡ ወይንም፡- ባልፆመው የማስጠይቀኝ፡ ግዴታ ያልሆነ ተግባር ነው ብለን አንሳነፍ፡፡ በመፆማችን ደግሞ የምናገኘውን አጅር እናስላ፡፡ አንድ ወር ሙሉ በተከታታይ በአላህ ተውፊቅና እገዛ መፆም ከቻልን ስድስት ቀናትን መፆም ደግሞ እንደምን ይጠናብናል?
አንዳንዱ ደግሞ ፆሙ ይከብዳል እንደ ረመዷን አይቀልም ይላል፡፡ እውነት ነው የሸዋል ወር ፆም ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም፡- አንድ፡ በረመዷን የታሰረው ቀንደኛው ጠላታችን ሸይጧን ከዒድ ሶላት መጠናቀቅ በኋላ ተፈትቷልና ወደ ስራው ይመለሳል፡፡ ደግሞም ይህንን የሸዋልን ፆም ልክ እንደ ረመዷኑ ቤተሰብ፣ ጓደኞችና የመስጂድ ጀመዓዎች ሁሉም ስለማይፆሙት በሚፆሙት ላይ (አላህ ያገራለት ሲቀር) ሊከብድ ይችላል፡፡ ቢሆንም አላህ ዘንድ የሚገኘውን ሽልማት ያሰበና ያመነ ባሪያ ሊከብደው አይገባም፡፡

እንዴት እንጹመው?

ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ሸዋል ሙሉ ወር በመሆኑ 29/30 ቀናት አሉት፡፡ የመጀመሪያው ቀን የዒዱ ቀን ነበር፡፡ ከዛ በኋላ የሚቀረው 28 ቀናት ይሆናል ማለት ነው (ወሩ 30 ለመሙላቱ እርግጠኛ መሆን ስለማንችል)፡፡ በነዚህ 28 ቀናት ውስጥ የሸዋልን ስድስት ቀናት በተከታታይ በማከታተልም ይሁን ቀናቱን ለያይቶ በማፈራረቅ መፆም ይቻላል፡፡ ከፈለገ ሰኞና ሀሙስ እደረገ፡ በአንድ ኒያ የሰኞና የሀሙስን እንዲሁም የሸዋልን ፆም በመነየት ሁለት አጅር መሰብሰብ ይቻላል፡፡

ቀዷ ያለበትስ?

የረመዷን ቀዷ (በህመም፣ በሐይድ እና በመሳሰሉት) ያለበት ሰው፡ ቀዷው እያለበት የሸዋልን ፆም በመፆም ከዛ ቀዷውን ወዲያው ወይም በሌላ ጊዜ ማስከተል ይችላል ወይስ ቅድሚያ ቀዷውን ከዛም የሸዋልን ፆም? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡
እዚህ ላይ ሁለት ነጥቦችን ማንሳት ይኖርብናል፡፡ እነሱም፡-
1. ከሑክም አንጻር
2. ከሚገኘው አጅር አንጻር

1ኛ. ከሑክም (ከሸሪዓዊ ፍርድ) አንጻር፡ ጉዳዩ በዑለማዎች (የኢስላም ሊቃውንት) መሐል ኺላፍ ቢኖርበትም፡ በላጩ ሐሳብ፡- ማንም ሙስሊም የረመዷን ቀዷ ቢኖርበት፡ ያንን ቀዷ ከመክፈሉ በፊት ሌሎች የሱንና ፆሞችን መጾም አይችልም የሚል መረጃ የለም የሚለው ነው፡፡ ይልቁኑ ቅዱስ ቁርኣን በግልጽ የሚናገረው፡ በበሽታም ይሁን በሙሳፊርነት እንዲሁም በሌላ ምክንያት የረመዷን ቀዷ ያለበት ሰው ‹በሌሎች ቀናት ቀዷውን ያውጣ› በማለት ተናገረው እንጂ፡ በሸዋል ወር ውስጥ ቀዷውን ይክፈል የሚል አይደለም፡፡ ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-
"...فَمَنْ كَانَ مِنْكُمْ مَرِيضًا أَوْ عَلَى سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِنْ أَيَّامٍ أُخَرَ... " سورة البقرة 184-185
"…ከእናንተም ውሰጥ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነ ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን መጾም አለበት…" (ሱረቱል በቀራህ 184-185)፡፡
ስለዚህም የረመዷንን ቀዷ የመክፈያ ጊዜው እስኪመጣ በዚያ መሐል የሸዋልን 6ቀናት፣ ሰኞና ሀሙስ፣ የዙል-ሒጅጃህ ቀናት (በተለይ የዐረፋ ቀን) እና መሰል ፆሞችን መጾም አይቻልም አይባልም፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡

2ኛ. ከሚገኘው ምንዳ አንጻር፡- ዋናው ቁልፉ ያለው እዚህ ጋር ነው፡፡ ሙሉ አመቱን እንደፆመ እንዲቆጠርለትና አጅሩም ተቀማጭ እንዲሆንለት የፈለገ ሰው ግን ግዴታ ቀዷውን ቀድሞ ማጠናቀቅ አለበት፡፡ ምክንያቱም ከላይ በሐዲሡ ላይ እንደተገለጸው የሸዋልን ወር ፆም ያስከተለ የተባለው ‹ረመዷንን ለፆመ› ሰው ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰው ረመዷንን ጹሟል የሚባለው ሙሉውን ሲያጠናቅቅ ነው፡፡ የተወሰነ ቀሪ ዕዳ ካለበት፡ ረመዷንን የፆመ የሚለው ሐዲሥ ውስጥ አይካተትም፡፡ ስለዚህም የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ቅድሚያ ቀዷችንን በማጠናቀቅ ከዚያም ወደ ሸዋሉ ፆም መግባት ይቻላል፡፡ ደግሞም ቅድሚያ ዕዳን ከፍሎ ማጠናቀቁ ተገቢ ተግባር ነውና፡፡ የተሟላውን የአመት አጅር ለማግኘት ከሸዋል ወር ስድስት ቀን ጾም በፊት ቅድሚያ የረመዷን ቀዷ መከፈሉ ግድ መሆኑን ከሚገልጹ የዑለማዎች ፈትዋ መሐከል፡-

1. ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ) ፡- ፈታዋ ኑሩን ዐለ-ደርብ ካሴት ቁ 918
2. ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) ፡- ፈታዋ አል-ሐረሙል መኪይ ካሴት ቁ 7

አቋራጭ መንገድ ካለ?

መቼም ይሄ (shortcut) አቋራጭ መንገድ የሚባለው ነገር ተላምዶናል፡፡ በሰላምታ ወቅት (as wr wb) በሰላዋት ጊዜ (s.a.w) በምስጋና ተግባር ላይ (jzk)… ታዲያ አሁንም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዲሉ፡ የረመዷንን ቀዷና የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆም በአንድ በመነየት አጣምሮ መፆም ይቻላል ወይ? የሚል ጥያቄ ተነሳ፡፡
ይህን ጥያቄ ፈዲለቱ-ሸይኽ ሙሐመድ ቢን-ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን እንዲህ ይመልሱታል፡- ‹‹የረመዷን ቀዷ እያለበት የዐረፋን ቀን ወይም የዐሹራእን (የሙሐረምን 10ኛ ቀን) የፆመ ሰው ፆሙ ትክክል ነው፡፡ ደግሞም እነዚህን ቀናት የረመዷንን ቀዷእ በመክፈል ኒያ በአንድ ላይ ቢፆማቸው ሁለት አጅርን ያገኛል፡፡ የዐረፋ ቀን ፆምና የዐሹራእ ፆምን አጅር ከረመዷን ቀዷእ አጅር ጋር ማለት ነው፡፡ እሱም እነዚህ የሱና ፆሞች ቀጥታ ከረመዷን ጋር ቀጥታ ግንኙነት የሌላቸው በመሆናቸው ነው፡፡ የሸዋል ወር ስድስት ቀናት ፆም ግን ከረመዷኑ ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ምክንያት በአንድ ኒያ ሰብስቦ መፆሙ አይሆንም፡፡ ቅድሚያ ቀዷውን ከፍሎ ከዛም የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆም ያስከትል›› (ፈታዋ-ሲያም 438)፡፡
ወላሁ አዕለም

Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
17.2K views20:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-02 00:33:39 እንኳን ለተከበረው 1,443ኛው የረመዷን ወር ፆም አላህ በሰላም አደረሳችሁ!

አላህ ወሩን የዒባዳ፣ የድል፣ የአንድነት ያድርግልን
16.7K views21:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 18:08:44 አዲስ ተከታታይ ደርስ
ፃምን የሚያፈርሱ ነገራቶች
ክፍል 7

አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Join ➤➤ t.me/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
18.5K viewsedited  15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 14:18:18

18.0K views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-16 19:42:19
16.7K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-15 22:27:20 አዲስ ተከታታይ ደርስ
በፃም ወቅት የተፈቀዱ ነገሮች
ክፍል 6

አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Join ➤➤ t.me/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
16.3K viewsedited  19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-13 17:19:45

16.5K views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 22:25:34
14.9K views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 21:40:20

14.4K views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 17:27:07

22.1K views14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ