Get Mystery Box with random crypto!

قناة أبي حنيفة عبد الكريم لنشر التوحيد والسنة.✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ abuhanifa_2 — قناة أبي حنيفة عبد الكريم لنشر التوحيد والسنة.✍ ق
የቴሌግራም ቻናል አርማ abuhanifa_2 — قناة أبي حنيفة عبد الكريم لنشر التوحيد والسنة.✍
የሰርጥ አድራሻ: @abuhanifa_2
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 665
የሰርጥ መግለጫ

وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالأِنْسَ إِلاَّ لِيَعْبُدُونِ 
*ሱራህ 51, አያህ 56*
ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡
================================

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-03 15:31:10 አኺራችንን እናስቀድም
~
* ልጅ ሆይ! ስለ ወላጅ ሐቅ ክብደት ሲነገር አይክበድህ። የወላጅን ሐቅ በመጠበቅ ከወላጅ በላይ የሚጠቀመው ልጅ ነው።
* ሚስት ሆይ! ስለ ባል ሐቅ በተደጋጋሚ ሲነገር አይደብርሽ። የባልን ሐቅ በመጠበቅ ከባል በላይ የምትጠቀመው ሚስት ናት።
* ባል ሆይ! ስለ ሚስት ሐቅና ኃላፊነትህን ስለ መወጣትህ ሲነገር አትሰላች። የሚስትን ሐቅ በመጠበቅ ከሚስት በላይ የሚጠቀመው ባል ነው።

~ ማንም ቢሆን በፈጣሪው የተጣለበትን ሐቅ ቢወጣ ከሚያከብረውና ከሚንከባከበው አካል በላይ የሚጠቀመው እራሱ ነው። ደግሞም በፈጣሪ የተጣለብንን አደራ ለመወጣት ሲያደርጉ እናደርጋለን፣ ሲተው እንተዋለን ዓይነት የ 'ሰጥቶ መቀበል' ሂሳብ ውስጥ መግባት የለብንም። አባትህ ቢበድልህ የበደል ሂሳብ ውስጥ አትግባ። በወንጀል እስካላዘዘህ ድረስ በምትችለው ከጎኑ ሁን። ከሌሎችም አንፃር እንዲሁ። አላህ ነፍስያችንን ረግጠን ለትእዛዙ የምናድር ያድርገን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
89 views12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 12:06:15 بسم الله. الحمد لله. والصلاة والسلام على رسول الله وعلى أله ومن والاه. أما بعد:-

ሚስጥረ ሁለቱ

በሁለቱም አለም ስኬትን ማግኛ
ፍጡር ከፈጣሪው ፍፁም መገናኛ
ሲያመልክም ሲከተል ሲሆን ነው ሐቀኛ
አሏህ የመከረው ብሎ ከእውነተኛ
ሁኑ አደራችሁን እንቅልፍም አልተኛ
እንግልጃም አትይዘኝ ሌት ከቀን ዘበኛ
የሐቋ ጠባቂ እኔው ያለም ዳኛ
ፈራጅ በሁሉም ላይ ቅንጣት አትቀረኛ
አብሽሩ ሲል አሏህ እንሁን ደስተኛ።
በዱኒያ ስራ ነው ክፍያው የአኼራ
ታዳ እንዴት ይረሳል የኋላው ምርመራ
ተጠንቀቅ ወንድሜ እህቴም አደራ
ሩቅ አይምሰለን ነገ የኛ ተራ
ሲባል አናርቀው አሁን ነው ጠንካራ
ትጉ መሆን ለአሏህ በአሏህ ስም እንስራ
ወደ አንድነት በሐቅ በትጋት እንጥራ
ምነው ጠወለገ የአንድነት አዝመራ
ተንከባካቢ አጣ ነው ወይስ ተዘራ
ፀረ-አንድነት አረም የሰው ክፉ ስራ
ለምነው ችላ ያልን ከሶሓቦች ተራ
ከነዚያ ባለርስት የእስላም አባወራ
ከፍ አርገው ከያዙት የተውሒድ ባንድራ
ሴት ወንድ አጠቃላይ በነሱ ቢመራ
መች ይጎዳን ነበር ይህ ሁሉ መከራ፤
የልዩነት ገፈት የጀህል ተራራ
አይገፋ በጀህል በከንቱ ፉከራ
ያላአቅም በመጮህ ማንም ቢንጠራራ
አይከለክለንም ከደጋጎች ስራ
ሚስጥረ ሁለቱ በደንብ ይብራራ።
በየአካባቢያችን የሶሐቦች ፋና
ጠንክረን ከሰራን እንድሆን ገናና
ሞራል ካልወረደ ወኔያችን ከጠና
ቅስም ሳይሰበር ያ ስነልቦና
በእስላም መገለጫ የማያፍር ጀግና
ካፈራን ተተኪ ንቁ ተሳታፊ ለተውሒድ ለሱና
ተቆርቋሪ ወጣት ፈሕሙ የተቃና
በሰለፎች መንሐጅ ታጋይ ባለዝና
ወሬ ቀነስ አርጎ በተግባር ነውና
ሚስጥረ ሁለቱ ለገባው ናሙና
አለለት ምሳሌ ሳይተክዝ ይፅናና
ይልቅ ደስ ይበለው አንገት ይበል ቀና
በሶሓቦች መሪ በአበልቃሲም ሱና
ረሱሉሏሂ ወዐብዱሁ ፀና
ከዚህ የበለጠ መሞገሻ ዝና
ለሙሐመድ ክብር ሌላስ ምን አለና?
ሶለሏህ ዓለይሂ ወሰለም ሳትሉ
ስማቸው ተነስቶ ማለፍ ተከልከሉ
በአሽረፈልኸልቁ ላይ ድጋሜ ሶሉ
ሚስጥረ ሁለቱ አንዱ ይህ ነው በሉ
አሽሃዱ አነሁ ዐብዱን ወርረሱሉ
ሱናን ብቻ ያዙ ቢድዓን ንቀሉ
ከስሯ እንድትደርቅ የግፍ ሳር ቅጠሉ
ይቃጠል በይፋ ሙብተዲዕ አካሉ
ከሱና ኑር ነጥፈው ጠውልገው የዋሉ፤
ዋናው ቁም ነገሩ ለሰው ለጅን ሁሉ
በቀውል ሆነ ተግባር እሱን መከተሉ
ብቸኛ መንገድ ነው ለስኬት አባሉ
በዱኒያም ባኼራም እንዳው በጥቅሉ
ሐቅን መቃረብ ነው መራቅ ከባጢሉ።
በአምልኮም ልከተል ረሱል በቂዬ
የስኬቴ ሚስጥር በዱኒያ አኼራዬ
ሁለተኛው ሚስጥር ይህ ነው የጌታዬ
ተመላኪ በሐቅ ብቸኛ አለኝታዬ
አምሳያ የሌለው ታማኝ ጠባቂዬ
ረዳቴ ፍፁም ተንከባካቢዬ
በሐቅ የሚመለክ ባለውለታዬ
ላኢላሃ ኢለሏህ ናት ሁለመናዬ።
ሽርክንና ኩፍርን ኒፋቅን ባይነቱ
ፍፁም ያወገዘች ሚስጥረ ሁለቱ
የጀነቷ ሰበብ መግቢያ ከድሎቱ
ያፀደቀች ሐቁን አምልኮን ባይነቱ
ለአሏህ ለብቻው ተመላኪነቱ
በልቅናው እሱው በብቸኝነቱ
አንድም የማይመስለው በሲፈት በዛቱ
በሁሉም ሙሉ ነው የሌለው ጉድለቱ
በሱው ላይ አማረ አሲማእ ወስሲፈቱ
ከዐርሹ በላይ ነው ከፍ ያለው በዛቱ
በሰባት ቦታ ቁርአን መቅራቱ
على العرش إستوى الرحمان
ማለቱ
ለምን ይመስልሃል ጠይቅ ከአዛውንቱ
ከእስልምና አበዎች ሚስጥሩን ከፈቱ
ከነዚያ ቀደምቶች ሰለፎች ከጥንቱ
ያበጥሩልሃል ገብቷቸዋል ስልቱ
ዓረብኛ ቋንቋው ሸሪዓው ባይነቱ፤
ደግሞም ከባሪያው ጋር ፀድቋል አብሮነቱ
በጥበቃ በእውቀት በእርዳታና እዝነቱ
ነውና አደራ ይቅር ማዛባቱ
ተሕሪፍ ተዕጢል ተክይፍ በተምሢል መቅራቱ
የአይሁድ ተንኮል ነው እስላም የማጥፋቱ
የጧት ተሞክሮ እንጅማ በእውነቱ
ይህን ያላመነ ከሰረ በከንቱ
ፍፁም አላማረም የአኼራ ቤቱ
ሞትን የፈራበት ዱኒያ መቆየቱ
ፍፁም ረዝሞበት ያ ከንቱ ምኞቱ
መምሸቱን የረሳ ሲነሳ ከጧቱ
ሳይገባው ቀርቶ ነው የዋለለው ስንቱ
ከዚህ አይነት በላእ ባሪያውን ማፅዳቱ
አልሐምዱሊላሂ በቀን በምሽቱ
እባካችሁ ይግባን ሚስጥረ ሁለቱ።

ተፃፈ
በአቡ ሐኒፋ ዐብዱልከሪም (ከገጠር)
ረቡዕ፣ ሙሐረም 5፣ 1444 ሂጅሪያ
ሐምሌ 27፣ 2014 ዓ.ል.
Wednesday, August 3, 2022 G.C.
81 views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 12:06:15
70 views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 16:45:16 ሰላትን ለመገላገል ብለን መስገድ ይብቃ !

https://t.me/Muhammedsirage
104 views13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 15:38:21
106 views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 22:19:35 የሙሐረም ወር ቱሩፋት

ከአቡ ሁረይራ (ረዲዬሏሁ ዐንሁ) ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንድህ ማለታቸው ተላልፏል:-
«ከረመዳን በመቀጠል በላጭ የሆነው ፆም የአላህ ወር የሆነው የሙሐረም (ወር ፆም) ነው።
ከግደታ ሶላት በመቀጠል በላጭ የሆነው ሶላት የለይል ሶላት ነው።» [ሙስሊም]

➼ ይህ ሐዲሥ ከረመዳን ፆም በመቀጠል የሙሐረም ወር ፆም በላጭ እንደሆነ ግልፅ የሆነ መረጃ ነው።

➼ እንድሆም የሐዲሡ ግልፅ መልእክት የሙሐረምን ወር ሙሉ መፆምን ያመላክታል ነገር ግን ከፊል ዑለሞች ሁሉንም መፆም ሳይሆን ከሙሐረም ወር ብዙ ቀናቶችን በመፆም ማነሳሳት ነው በሐዲሡ የተፈለገው ብለዋል።
ኢብኑል ጀውዚይ (ረሒመሁሏህ) ለጧኢፉል መዐሪፍ ገጽ 39 ላይ የሚከተለውን አስፍረዋል:-
«ከሙሐረም ወር በማከታተል ከፆሙት መካከል ዑመር፣አቡ ጦልሐ፣ዓኢሻ እና ሌሎችም ይገኙበታል ኢብኑ ዑመር፣ሐሰኑል በስሪና ሌሎች ደግሞ የሙሐረም ወርን ሙሉውን ይፁሞ ነበር»

ማሳሰቢያ:- በዚህ ሐዲሥ የተፈለገው ከሙሐረም አስረኛውን (የዐሹራን) ቀን መፆም ሳይሆን ከሙሐረም ወር ሁሉንም ወይንም አብዘሀኛውን ቀነሰቶች መፆም ነው። ስለዐሹራ ፆም ሌላ እራሱን የቻለ ሐዲሥ አለ የአላህ ፍቃድ ከሆነ በሌላ ፅሑፍ እመለስበታለሁ።

➼ የሙሐረም ወር የሂጅራ አቆጣጠር የሚጀምርበት የአመቱ መጀመሪያ ወር ነው።

➼ የሙሐረም ወር አሏህ በቁርኣን ውስጥ ከጠቀሳቸው አራት የተከበሩ ወራቶች መካከል አንዱ ነው።

{ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ ۚ فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ ۚ }

«የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡» [ተውባ (36)]

እነዚህን የተከበሩ አራት ወራቶች ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሚከተለው ሐዲሥ ጠቅሰዋቸዋል «… አመት አስራ ሁለት ወር ነው። ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው:- ሶስቱ የተከታተሉ ናቸው ዙል ቂዕዳ፣ዙል ሒጃና ሙሐረም እና ረጀብ የሙደሮች ወር ያ በጁማዳ እና በሸዕባን መካከል ያለው…» [ቡኻሪና ሙስሊም]

➼ ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከላይ ባሳለፍ ነው ሐዲሥ የሙሐረምን ወር ወደ አላህ በማስጠጋት የአላህ ወር ብለው ጠርተውታል ይህ የዚህን ወር ደረጃ ትልቅነት የሚያሳይ ነው ምክኒያቱም ከፍጥረቶቹ ወደአላህ በመጠጋት የሚጠሩት ነገሮች ከፍጥረቶቹ ውስጥ ለየት ያለ ደረጃ ያላቸው ፍጥረቶች ናቸው። ለምሳሌ ከዕባን بيت الله የሷሊሕን ግመል ناقة الله በማለት በክብር ወደ እሱ እንዳስጠጋቸው እሄም ወር ከሌሎቹ ወር በመለየት ወደአላህ በማስጠጋት ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጠርተውታል።

➼ ከላይ በሳለፍነው የቁርአን አንቀፅ ውስጥ አሏህ «በእነርሱ(በእነዚህ በተከበሩ አራት ወራቶች) ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡» ይለናል :- ይህ ማለት
በእነዚህ በአራት ወራቶች ውስጥ ወንጀልን አትፈፅሙ ወንጀል በየትኛውም ወራት ሐራም ቢሆንም ግን በእነዚህ የተከበሩወራቶች የሚፈፀም ወንጀል ቅጣቶ በሌሎቹ ወራቶች ከሚፈፀሙ ወንጀሎች ከበድ ያለነው።
ታላቁ ሙፈሲር ኢማም ኢብኑ ከሢር እንድህይላሉ:-
« በማንኛውም ወራቶች በደልን መፈፀም ወንጀል ቢሆንም በሌሎች ወራቶች ከሚፈፀም በደል በበለጠ በተከበሩት ወራቶች የሚፈፀም በደል ሀጢአቱና ወንጅሎ የከበደ ነው።…» [ተፍሲር ኢብኑ ከሢር (4/89)]

➼ በዚህ በተከበረ ወር እራሳችንን ከሀራም አርቀን በቻልነው መልካም ስራ ለመስራት ቆርጠን እንነሳ በተለይ ከላይ ባሳለፍነው ሐዲሥ እንዳየነው በዚህ ወር ፆም ወደአላህ እጅግ የተወደደ መልካም ስራ ስለሆነ በቻልነው ያክል ለመፆም እንሞክር በጥቅሉ ነገ ሞት መጥቶ በእኛና በመልካም ስራ መካከል ሳይጋርደን በስተፊት ዛሬ በዱኒያ ላይ የተሰጠንን እድል መልካም ስራ በመስራት ሳያልፍ እንጠቀምበት

አላህ ሆይ የመልካም ስራ በሮችን ክፈትልን ወዳንተ የሚያቀርበንን መልካም ስራ በፈፀም ላይ አበርታን

ወንድማችሁ ኢብኑ ሙሐመድ ዘይን (ሙሐረም 01/1444)
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/IbnuMuhammedzeyn
131 views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 08:12:41 አቡ ሐኒፋ ዐብዱልከሪም (ከገጠር)
ቅዳሜ፣ ሙሐረም 1፣ 1444 ሂጅሪያ
ሐምሌ 23፣ 2014 ዓ.ል.
Saturday, July 30, 2022 G.C.
በኢሕሳን መስጅድና እስላማዊ ትም/ቤት ለአጠቃላይ ተማሪዎች የተደረገ የዳዕዋ ፕሮግራም
156 views05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 09:55:11
Photo from عبد الكريم
214 views06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 09:51:48 ሐቅና ውለታ
بسم الله
ብዬ ልጀምር በወጉ
ሐቅ ላይም ያፅናን እስከ አኼራ ጥጉ
ባጢል ተወጋጅ ነው ፍፁም እንዳትሰጉ
ባይሆን ኢኽላስ ይኑር ኢቲባዕን ዘርጉ
ሶብርና የቂን እንዳትዘነጉ
እንዳይወድቅ አጋዥ የቀኝ እጅ ዘንጉ
አደራ ብያለሁ ይህ ነውና ደጉ
ወደ አሏህ ላሰበ ወግና ማረጉ።
ብዙ ተወያይተው ውሸት ከተወራ
ስንት ተመካክረው ልክ እንዳልተሰራ
የተስማሙበትን ክደው በየተራ
እንቢ ከተባለ አሏህ ካልተፈራ
ተው ይፈርጁን እኛም ስራ እንስራ
ኋላ እንቀርባለን እዛው ለምርመራ
ግን አልተመኜሁም ማንም ላይ ኪሳራ
ከሰፊዋ ጀነት ከዛች ፅዱ ስፍራ
ስልጣኑ የሱ ነው ብዙም ባናወራ
ወሕሽይን ሲያስገባ ሲስቅ ማንን ፈራ
እጅግ አይድነቅህ በከንቱም ቢወራ
እሳት ጀነት በአሏህ እንጅ በፉከራ
አይደል በቀረርቶ በከንቱ ለጠራ፤
አልሐምዱሊላህ አወለን ወአኼራ
ሐምዛም ከአሏህ ወዷል በቁርአን ሲወራ
ከፊሉን በተውበት በመልካምም ስራ
ያስገባውን አሏህ አስብ ለሱው ስራ
የሌለውን "ተምዪዕ" ለጥፈህ ስትኮራ
ራስህ እንዳትቀልጥ አቅልጠህ በጉራ፤
ግን ጥሩ አጋጣሚ ለራስ ለምርመራ
እንጠቀምበት ፊትናውን ለስራ
እኛ ሰበብ ሳንሆን ለፊትናው ሳንሰራ
ስሜት አስወግደህ ለአሏህ ስትል ዝራ
ኋላ ምታጭደውን ነገ በአኼራ
ምርጥ ዘር እያለ የሌለው መከራ
እንክርዳድ አታድርግ አራሙቻ ውራ።
ውለታና ሐቁ አብረው ካልተጓዙ
ውለታ ከብዷችሁ ሐቅን አትበርዙ
ይልቅ ለውለታ "ሙካፈአ"ን አብዙ
ውለታ ከብዷቸው ሐቅ ያደበዘዙ
ባጭር ተለያዩ ሩቅ ሳይጓዙ
ይህ የአሏህ ሱና ነው ስሞታም አታብዙ
ቅድሚያ ለሐቅ በል ፍፁም ሳይተክዙ፤
በከንቱ መደገፍ በጭፍን መጓዙ
ከግልፅ ስህተት ጋር ዱኒያ ላይ ቢበዙ
ብቸኝነት አለ ከቀብር ሲጓዙ
አጫዋች እንድሆን ሐቅን በጥብቅ ያዙ
ዋልህ ዋልሽ ኋላ ከባድ ነው መዘዙ።
አሏህ ፊት ነው እንጅ ቂያማ ለምርመራ
አንገናኘውም ከእንግድህ ተጠራ
በተውበት እንዝጋው ያለቀውን ሒጅራ
አስራ አራት አርባ ሶስት ሄደ ቀይ አበራ።
ፋይሉን ጠቀለለ በጁሙዓ ዘጋ
ወደ መሃሪያችን አሏህ እጅ እንዘርጋ
በጠራችው ተውበት ከደጁ እንጠጋ
ባጢል ቢኮፈስም ሐቅ አለች ጠራርጋ
ታስወግደዋለች ፍፁም እንዳትሰጋ
ግን ፈተና አይቀርም አይሆን አልጋ ባልጋ
ሐቅን ለመፈለግ በሐቅ ላይ ትጋ
ስንቶች በባጢል ላይ ሐቂቱን ፍለጋ
ተንጠላጥለው ቀሩ ተውፊቁ ሲዘጋ።
ስለዚህ እህቴ አንተም ቅን ወንድሜ
አይጠቅምህም እንጅ ቢቀዳልህ ደሜ
አልሰስትም ላንተ ሐቅን አስቀድሜ
እባክህ አደራ ስልሽ ደጋግሜ
ለሁላችን እንጅ ራስ አስቀድሜ
በተቅዋ አደራ ስል የዘላለም ሕልሜ
ይህ ነው መጨረሻ መልእክቱ የግጥሜ።
አብረው ካልተጓዙ ሐቅና ውለታ
አሏህ ይበቃሃል በፍጡራን ቦታ
ሐቅን አጥብቀህ ያዝ ፍፁም አታመንታ።

አቡ ሐኒፋ ዐብዱልከሪም (ከገጠር)
ጁሙዓ፣ ዙልሒጃ 30፣ 1443 ሂጅሪያ
ሐምሌ 22፣ 2014 ዓ.ል.
Friday, July 29, 2022 G.C.
166 views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ