Get Mystery Box with random crypto!

ጥሩ ነው ስብሰባ! ኬክ እየገመጡ ሚሪንዳ እየጠጡ ማቅለጥ ነው ጭብጨባ ልዩነት እርሙ ነው ያ'ገሬ | አብሮነት/Abronet

ጥሩ ነው ስብሰባ!

ኬክ እየገመጡ
ሚሪንዳ እየጠጡ
ማቅለጥ ነው ጭብጨባ
ልዩነት እርሙ ነው ያ'ገሬ ስብሰባ



ቢሆንም ቢሆንም ጥሩ ነው መሰብሰብ
ሺ ሆኖ ተቀምጦ እንደ አንድ ሰው ማሰብ
ጠንቋይ ፊት እንዳለ ወይም ከቃልቻ
አንገት አቀርቅሮ "አሜን አሜን" ብቻ
ጥሩ ነው ስብሰባ!



ሰብሳቢው ሲናገር ጭብጨባ ይቀልጣል
ደግሞ ከተቀማጭ አንዱ እጁን ያወጣል
"ጊዜ ካገኘሁኝ አብራራለሁ ነጥብ
ጊዜ ከሰጣችሁኝ አብራራለሁ ነጥብ"
እያለ
ጊዜ ይለምናል ጊዜ አግኝቶ ሳለ
ጊዜ ለመለመን ጊዜ እየገደለ
ያልታደለ!!!



ቢሆንም ቢሆንም ጥሩ ነው መሰብሰብ
ሺ ሆኖ ተቀምጦ እንዳ'ንድ ሰው ማሰብ
አንዱ ያነሳውን - ቃል እየቀየሩ - በቋንቋ መራቀቅ
ሰብሳቢው እንዳያይ - በሰው ተከልሎ - እንቅልፍ መሰለቅ

አንዱ ባጋጣሚ ምርጥ ሃሳብ ካነሳ
ሰብሳቢው በንዴት እንዳ'ውሬ እያገሳ
"የለም የለም የለም እሱን ሃሳብ ተወው
ከነጥብ አትውጣ አጀንዳው ሌላ ነው"
ብሎ ሲያሸማቀው አሁንም ጭብጨባ
ቢሆንም ቢሆንም ጥሩ ነው ስብሰባ
ኬክ እየገመጡ
ሚሪንዳ እየጠጡ

(ሀገሬን ሰቀሏት)

___
ደሱ ፍቅርኤል
ተይው ፖለቲካውን ዝም ብለሽ ሳሚኝ