ሸይሁል ቃጥባሬ (አቡል ጀበል) አንድ ሊስትሮ ስለ ቸርነታቸው ሲገልፅ እንዲህ ብሎ ነበር፤ ከአንድ | ABRET PRO

Picture 1 from ABRET PRO 2026-01-23 12:21:31
ሸይሁል ቃጥባሬ (አቡል ጀበል) አንድ ሊስትሮ ስለ ቸርነታቸው ሲገልፅ እንዲህ ብሎ ነበር፤ ከአንድ ከወቅቱ ባለስልጣን ጋር ቆመው ሁለቱም ጫማዎቻቸውን አስጠርገው ሲከፍሉ ባለስልጣኑ ለጠረገላቸው ልጅ የተወሰነ ሳንቲም ይሰጡታል፤ አባባ ግን ወደ ኪሳቸው ገብተው ሳያዩም እጃቸው የቻለውን ያህል አውጥተው ያክሉለታል፤ ታዲያ የሆነ ቀን በዚያ ሲያልፉ አያቸውና ወይኔ ያ ሳያዩ/ሳይቆጥሩ የሚሰጡት ሰውዬ መጡ አለ ይባላል።

ሠይዲም (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ከአንሷር የሆኑ ሰዎች ወደ እርሳቸው መጥተው ስጦታ ጠየቁ ሰጧቸው። በድጋሚ ጠየቁ ሰጧቸው፤ በጃቸውን ያለው ሰጥተው ከጨረሱ በኃላ እንዲህ አሏቸው፦
ABRET PRO

ABRET PRO

@abretpro
4.55K ተመዝጋቢዎች
ሃይማኖት ምድብ
የአብሬት እንዲሁም የቃዲሪይ ሲልሲላ መንዙማዎችን ፣ ከአካቢሮች የሰማናቸውን ቀሰሶች ፣ እንዲሁም ከመሻኢኾቻችን ኪታቦች ...