Get Mystery Box with random crypto!

ABRET PRO

የቴሌግራም ቻናል አርማ abretpro — ABRET PRO A
የቴሌግራም ቻናል አርማ abretpro — ABRET PRO
የሰርጥ አድራሻ: @abretpro
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.03K
የሰርጥ መግለጫ

የአብሬት እንዲሁም የቃዲሪይ ሲልሲላ መንዙማዎችን ፣ ከአካቢሮች የሰማናቸውን ቀሰሶች ፣ እንዲሁም ከመሻኢኾቻችን ኪታቦች አንዳንድ ጠቃሚ ነገሮችን የምንማማርበት አጠቃላይ የሀድራ ስራዎችን የምንዘክርበት ቻናል ነው
@Abretpro

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 23:21:18
ዒንደ መውሊዲሂ ቀድ ኸረቲል አስናም
ኸመደቲል ናሩ መዕቡዱ ዚል አثا
ወነበዐል በሕሩ ሊተውሒይደል ኪራም
ከአነሁል ሸምሱ ለም የብቃ ሚን ዞላም
ወኑሢኽተ ሚንሁ አሕካሙል አወሊ
ሓሚሉል ሊዋኢ ሸፊዑል አዘሊ

ወዐመል ፈረሑ በይነል ኸልቂ ጡራ
ነዘለ ጂብሪይሉ ቢልሐሪይሪል ሐድራ
ሐፈሁ ቢልኑሪ ኑረን ሙነወራ
ዘየነል ጂናኑ ከዛሊከል ሐድራ
ቀድ ዐሊመ ቢሂ ኩሉል ቀባኢሊ
ሓሚሉል ሊዋኢ ሸፊዑል አዘሊ

አሏሁመ ሰሊ ዓላ ሙሐመዲ
ሠሒቁል አንዋሪ ወልሚሥኪ ወልአንበር
ሓሚሉል ሊዋኢ ሸፊዑል አዘሊ
294 views20:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:01:09
ለይለተል ጁሙዓህ
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀

﴿ ﷽

﴾﴿ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ﴾

አሏህም መላኢካዎቹም ነብዩﷺ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ እናንተ ያመናቹ ሙእሚኖች ሆይ ሰላት እና ሠላም በነብዩﷺ ላይ አውርዱ

قال رسول الله ﷺ :

أَكثِروا الصَّلاةَ عليَّ يوم الجمعةِ
وليلةَ الجمعة فمن صلَّى عليَّ صلاةً صلَّى اللَّهُ عليْهِ عشرًا ."

ረሡልﷺ አሉ:- የውመል ጁሙአ እንዲሁም ለይለተል ጁሙአ እኔ ላይ ሰለዋት አብዙ... አንድ ሰለዋት እኔ ላይ ያወረደ አሏህ እሱ ላይ አስር ያወርድበታል.

‎اللهم صل على سيدنا محمد في الأولين وصل على سيدنا محمد في الأخرين وصل على سيدنا محمد في النبيين وصل على سيدنا محمد في المرسلين وصل على سيدنا محمد في الملأ الأعلى الى يوم الدين
414 viewsedited  17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 16:43:11
አለፍ አልፍ ተብሎ የተቀነጫጨቡ
ጥቂት ስንኞች ከሠይድ ባኡ ሳኒ መድህ
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀

አሏሁመ ሰሊ ዓላ ሙሐመዲ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ
~~~~~~~~~~~~~~~

አዩሃል ነብዩ አንተ ቁረይሹ
ዘይን ባጢነና ቢሢሪ ሢሪከከ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ

ሓያቱ ሩሒና ወሐያቱል ቁሉብ
ኡክቱብ ቢቀልቢና ኑረ ጀማሊከ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ

ዘለለሁል ገማም ወሚፍታሁል ዞላም
ኩሉ አንቢያኢ ተሕተ ሊዋኢከ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ

ተዐጀበል አምላክ ቢኑሪ ጀዲከ
ተሸፈዓ ቢከ ቢጃሂ ፈድሊከ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ

ኢፍተኸረል አርዱ ቢሐቢቢል ሰመድ
ዘየነሁል ጀሊል ኢንደ ዙሁሪከ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ

ተመናል ከሊሙ ኩንተ ኡመተሁ
ኩሉ አንቢያኢ ተወሠለ ቢከ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ

ኸሰሰል ኡመቱ ቢአፍደሊል ሙርሠል
የቁሉል ኡመሙ ኩንተ ኡመተከ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ

አስሉ ጀማሊና ቢማዕና አቢና
ኢቅተበሠል ኑሩ ሚን ኑሪ ወጅሂከ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ

ካነ ጁሉሱና ቢዘልመቲል አደም
ሰለሐቲል ዓለም ቢሢሪ ለደይከ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ

አልቢሥና ሠይዲ ታጀን ሚነል ሐሪር
አዚል ጊጣአና አውሱል ሐድረተከ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ

ፈቁልሊ ሠይዲ ኡሕዱር ሐድረተና
ቢዘንቢ ወዐይቢ የዙሉ ከርበከ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ

ውሊደል ሙስጠፋ ቢፈትረቲል ዘማን
አሽረቀቲል አርደ ዒንደ ውጁዲከ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ

ዋጂቡ ዓለይና አን ኑሒበሁ
ሡከሩ በዕደሁም ወቀተለ ዐንከ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ
606 views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:18:13 ሙሳ ዐሰ ተውራትን ሙሉ በሙሉ ካነበበ በኋላ አላህን እንዲህ ሲል ጠየቀው፡-‹‹ ያ አላህ በዚህ መጽሃፍ ውሰጥ ህዝቦች ይታዩኛል፤ በመጨረሻ የሚመጡ ሲሆኑ ግና ከሁሉም ህዝቦች ቀዳሚዎች ናቸው፡፡ እባክህ የኔ ህዝቦች አድርጋቸው፡፡››

አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ያ አላህ በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ህዝቦች ይታዩኛል፤ ህግጋቶቻቸውን በልቦቻቻው ሸምድደው ያነበንቡታል፡፡ እባክህ የኔ ህዝብ አድርጋቸው፡፡››

አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ ያ አላህ በዚህ መጽሀፍ ውሰጥ ህዝቦች ይታዩኛል ፤ ምርኮን ፈቅደህላቸዋል፡፡ እባክህ ህዝቦቼ አድርጋቸው፡፡››

አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ያ አላህ በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ህዝቦች ይታዩኛል፤ ምጽዋትን ይለጋገሳሉ በሱም ትመነዳቸዋለህ፡፡ እባክህ ህዝቦቼ አድረጋቸው፡፡››

አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ ያ አላህ በዚህ መጽሃፍ ውስጥ ህዝቦች ይታዩኛል፤ ጽድቅን ለመስራት አስበው ባይሳካለቸው አንድ ምንዳ ትመዘግብላቸዋለህ፡፡ ከተሳካላቸውም በ10 ታባዛላቸዋለህ፡፡ እባክህ ህዝቦቼ አድርጋቸው፡፡››

አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡- ‹‹ያ አላህ በዚህ መጽሃፍ ውስጥ ህዝቦች ይታዩኛል ፤ ለማመጽ ሲያስቡ ምንም አትመዘግብባቸውም፡፡ ግና ሲያምጹ አንዲትን ብቻ ትመዘግብባቸዋለህ፤ እባክህ የኔ ህዝብ አድርጋቸው፡፡››

አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም ጠየቀ፡-‹‹ ያ አላህ በዚህ መጽሃፍ ውሰጥ ህዝቦች ይታዩኛል ፤ የቀደምትን እና የመጺኣንን ትውልዶች ዕውቀት በሙሉ አሸክመኃቸዋል፤ መሲሁ ደጃልንም ይገድሉታል፡፡ እባክህ የኔ ህዝብ አድርጋቸው፡፡››

አላህም አለ፡-‹‹እነሱማ የአህመድ ኡመቶች ናቸው››

ሙሳም አለ፡-‹‹ በል እንግድያ እኔንም የሙሐመድ ህዝብ አድርገኛ፡፡››
ሙሳም ንግግሩን ቀጠለ፡-‹‹ ቆይ ግን ጌታዬ ከኔ ህዝብ እሚልቅ ህዝብ አለን››

አላህም አለ፡-‹‹ሙሳ ሆይ በሙሀመድ ህዝቦች እና በሌላው ህዝብ መካል ያለው ልዩነት በኔ እና በፍጥረቴ መከካል እንዳለው ልዩነት እንደሆነ አታውቅምን፡?>>

ሙሳም አለ፡-‹‹እንደው ይኸን የጉድ ህዝብ እንኳን አንዴ አሳየኝ››

አላህም አለ፡-‹‹ልታያቸው አይቻልህም፤ ግና ድምጻቸውን ላሰማህ፡፡››

ከፍጥረት አድማስ ወድያ ከሩሆች ስብስብ ከመናፍስት አለም ያሉ የሙሀመድ ህዝቦችን አላሀ ተጣራ፡፡

ህዝቦችም በአንድ ድምጽ፡-‹‹ለበይከላሁማ ለበይክ›› ይሉ ጀመር።

አላህም አለ፡-‹‹በረከቴ በእናንተ ላይ ይስፈን ፤ እዝነቴ እናንተ ላይ ቁጣዬን ቀደመ ፤ ማርታዬ ስለናንተ ቅጣቴን ቀደመው፡፡

እናንተ ሳትጠይቁኝ አኔ እሰጣችኋለሁ ፤ ከእናንተ ውስጥ የኔን ጌትነት አምኖ በሙሀመድ መለዕክተኝነትም ያመነ መላ ሀጽያቶቹን እሽርለታለሁ፡፡››

Sefwan sheik Ahmedin
----------------------------------------------------------
ነቢ ልቀው እኛን አላቁን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
----------------------------------------------------------

ምንጭ፦
المواهب اللدنية
حلية الأولياء
91 views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:29:59
ውሊደል ሙስጠፋ ቢፈትረቲል ዘማን
አሽረቀቲል አርደ ዒንደ ውጁዲከ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ

አሏሁመ ሰሊ ዓላ ሙሐመዲ
ሙባሪካ አሠላም ዓለይካ
446 views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:02:31
አሏህ ካፊና ወናዚሩና
ፈጁድ ቢሉጥፊ ፊእሕዋሊና
አንተ ሃዲና ወሙንዒሙና

ለየትኛውም የጠበቀ ሀጃ ነይተው አሏህን በዚህ ተወሱላት ከለመኑት ኢንሻአሏህ አሏህ ይቀበለዋል ብለዋል::

قال المؤلف سئلت الله تعلى ان يلهمن بالدعاء المستجاب الذى لايرد عنده بعد السؤال به فالهمن هذه القصيدة فاليقرء عند الحاجة والنازلة انشاء الله تعلى يكون مستجاب الحمدلله الذى وفقني على الصواب والصلاة والسلام على زين
الاحباب وباله وصحبه ذوى الايدى والالباب واتباعه صاحب الاعمال الصالحاتى وكثير الثوابتي

አብሬይ አልሳኒ አሉ... ነይተው ለቀሩት ሀጃ ሁሉ የሚሆን ለየትኛውም ሀጃ ተነይቶ በዛ ዱኣ ብትለመን የምትቅበለው የሆነ ተወሱላት(ዱኣ) ግለፅልኝ ብዬ አሏህን ጠየቅኩት አሏህም ይህንን ተወሱላት ገለፀልኝ አሉ አመደደሏሁ ቢመደዲሂም:: ለየትኛውም የጠበቀ ሀጃ ነይተው አሏህን በዚህ ተወሱላት ከለመኑት ኢንሻአሏህ አሏህ ይቀበለዋል ብለዋል አብሬትይ አምሳኒ በኪታባቸው::

‎الله كافينا وناظرنا
‎فجد بالطف فى احوالنا
‎أنت هادينا ومنعمنا


ለሐገራችን ሰላም ፣ ለዲናችን ሰላም ፣ ለሙእሚን ሙእሚናት ነይተን ብንቀራው በረካ ነው::
523 views13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:15:59
ይሄ ሀላባ ላይ የሚገኝ መስጊድና መድረሳ ነው ወንድማችን ሸይኽ ዐብዱል መሊክ ሸይኽ አህመዲን የመስጊዱ ኢማምና ኸጢብ ነው ።

ቪዲዮውን እዩት ። ከተጀመረ 3 አመት ሆኖታል ። በብር እጥረት ደሞ ከቆመ አንድ አመት ሆኖታል ። የመስጊዱ ጊቢ 5000 ካሬ ይሆናል ። መስጊዱ ያረፈበትና እስካሁን የተሰራውን ስራ ቪዲዮውን ከፍታቹ ማየት ትችላላቹ ። በሀላባ ውስጥ የሒፍዝና የዒልም ማዕከል የመጀመርያው ነው የሚሆነው ቢኢዝኒላህ ። ነገር ግን ስራው አላለቀም በጣም ብዙ ነገር ይቀረዋል ። ለአኼራችንና ለቀብራችን የምንሳሳ ከሆነ የሚያስጨንቀን ከሆነ ይሄን የመስለ ዘመን ተሻጋሪ የዒልም ማዕከልን እንደመስራት ሌላ ምርጥ ነገር ላናገኝ እንችላለን ። ወላሂ በጣም ነው ልቤን የነካኝ። የተቻላቸውን ያክል ለፍተውና ጥረው ይሄን ያክል አድርሰው ዞር ብሎ የሚያያቸው አጥተው አመት ሙሉ ምንም ሳይሰራ ቁጭ ብለዋል ። አቅሙ ያለን ወንድም እህቶች የተቻለንን ነይተን የበኩላችንን ለመሳተፍ እንሞክር ። ልብን ከፋቹ አላህ ነው ። አሏህ ላይ ነው ተስፋችን ።

https://t.me/mededulhabib

የምትችሉ በዚህ አካውንት የተቻላቹን ድጋፍ አድርጉ

ኡስታዝ አንዋር አሕመድ (1000338124841)
ስልክ ቁጥር : 0911449925

በአካል ለማየት ወይም ለማግኘት የምትፈልጉ በዚህ ስልክ ደውላቹ ኡስታዝ አንዋርን እዚው አዲስ አበባ ጦር ሀይሎች ሸኽ አደም በዳኔ መድረሳ ማግኘት ትችላላቹ ።
408 views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:52:22 መገርገበያ
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀

الشيخ محمد بن عبدالرحمن المالكي العلوي المغربي في بيت الشيخ سيد مقباس النور الڠا‎ڠوري الأبرتي الحبشي

የሞሮኮው ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዓብዱልራሕማን ሠይዲን በዘየሩበት ወቅት ከተቀሩ መንዙማዎች የተቀነጫጨበ

ሠይዱል ኢስጢፋ ሩሑ አሕሊ ሰፋ

اللهم صل على محمد(٢)
سيد الاصطفا روح أهل الصفا



483 views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:29:21 የሞሮኮው ታላቅ ሸይኽ ሸይኽ ሙሐመድ ቢን አብዱልራሕማን እሁድለት ሸይኽ ሠይድ ሚቅባሰል ኑርን በዘየሩ ግዜ ሠይዲን የመደሁበት ግጥም ከማንበባቸው በፊት እንደ መግቢያ እጅግ ውብ በሆነ አረብኛ አገላለፅ አጠር ያለ ንግግር አቀርቡ:-

ወልዮችን ታላላቅ መሻኢኾችን ዑለማዎችን መዘየር ትልቅ ኒዕማ መሆኑን ተናገሩ ፣ በዚያራውም እጅግ መደሰታቸውንና እኚህን ትልቅ የአሏህ ወልይ ፣ ዓሊም ፣ ሠይድ ፣ ሸሪፍ ፣ የረሱልﷺ ኸሊፋ ወራሽ ከሆኑ ትልቅ ሸይኽ አጠገብ በመቀመጤ ለአሏህ ትልቅ ምስጋና አቀርባለው ፣ ከእሳቸው ከንግግራቸው ፣ ከዒልማቸው ፣ ከፈሕማቸው የሚወጣው በረካ እኛንም ፣ የተቀማመጠውንም እንዲሁም ሁሉኑም የሚያካትት አሏህ ያድርገው ፣ እሳቸውን ዘይረን ያገኘነው በረካ እስከ ህይወታችን መጨረሻ ድረስ የሚቀጥል አሏህ ያድርገው ፣ ለእሳቸው ያለን ሙሓባም ዘውታሪ አሏህ ያድርገው ፣ ቀልባችንም ሁሌም ከእሳቸው ጋር ያድርግልን ብለው ለ ሠይዲም ለተቀማመጠው ሰውም ዱዓ አድርገው ይህንን ግጥም የገጠምኩት ዘራቸው የተከበረ ፣ ከተከበረ ዘር የተገኙ ለሆኑት ፣ በጥሩ ባህሪ በዘራቸውም የታወቁ ለሆኑት ፣ አልዓላማ ፣ አልፈኻማ ፣ ሠይድ ፣ ሸሪፍ ለሆኑት ትልቅ ዓሊም ነው በማለት ነበር ወደ ግጥማቸው የሄዱት:-

ስለ ግጥሙ ትርጉም ከአዋቂዎች የሰማሁት እንደሚከተለው ነው::

አባታቹህ የደገሙትን መካሪም(ምርጥ ምርጥ የተባለ ነገር ሁሉ) እናንተም ከአባታቹህ በሁዋላ ትደግሙታላቹ:: አባታቹ ግልፅ እንዳወጡ እናንተም ግልፅ ታወጡታላቹ:: አባታቹ ሰዎችን ወደ ቀጥተኛው መንገድ እንዳመላከቱት እናንተም ቀጥተኛውን መንገድ ታመላክታላቹ:: አባታቹ ለሰዎች እንደሰጡት እናንተም ትሰጣላቹ:: ቀናቶች የደበቁዋቸውን ሲር(ሚስጥር) ሁሉ በእርሶ ግልፅ ታወጣለች ፣ (ወሚቅባሰን) በጣም በሚጣፍጥ ሁኔታ ስጦታን እየሰጠች ትሄዳለች:: አባታቹ የገነቡት መሰረት ጠንካራ ሆኖ የቆየ ቢሆንም ጠንካራው ምሰሶ ላይ እናንተም እንደገና ጠንካራ የሆነ ምሰሶ ጨምራቹሁበታል:: የኔ ግጥም የኔ ልፋት እርሶ ካለዎት ፈድል ለእርሰዎ ከተሰጦት ስጦታ አንድ አስረኛውንም እንኳን አይሞላም:: ግን በእኔ ልክ ሳይሆን በእርሰዎ ቀድር ልክ ነው:: የእርሰዎ መካሪም ምርጥ ባህሪ የተባለን በሙሉ በጥሩ ሽታው አጥኖታል:: ሀገሩን አለሙን በሙሉ ሽታው ያዳረሰ ነው:: ይህ መሬት ይሄ ሀገር እርሰዎ በተገኙ ግዜ እርሰዎ በተወለዱ ግዜ ምነኛ ታደለች ፣ ለዚህች መሬት እናንተ ናቹ የደስታው ፣ የበረካው ፣ የሰዓዳው በሙሉ አውጪው። ይሄ ነው የኔ ሀሳብ ፣ ከእኔ በፊት የመጣውም ፣ ከኔ በሁዋላ የመሚመጡትም ይሄንን ነው የሚሉት ብለው ግጥማቸውን ጨረሱ::
611 viewsedited  14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:29:16
የሞሮኮው ታላቅ ሸይኽ ሸይኽ ሙሐመድ ቢን አብዱልራሕማን እሁድለት ሸይኽ ሠይድ ሚቅባሰል ኑርን በዘየሩ ግዜ ሠይዲን የመደሁበት ግጥም ከማንበባቸው በፊት እንደ መግቢያ እጅግ ውብ በሆነ አረብኛ አገላለፅ አጠር ያለ ንግግር አቀርቡ:-
557 views14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ