Get Mystery Box with random crypto!

ከ2013 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለ12ኛ ጊዜ ባካሄድኩት የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግምገማ በለ | Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

ከ2013 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለ12ኛ ጊዜ ባካሄድኩት የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግምገማ በለወጥነው የፕሮጀክት አስተዳደር እና ክትትል ስርዓት የተነሳ የአጠቃላይ ግንባታው ሂደት 62% ላይ መድረሱን በመመልከቴ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ በአፍሪካ ደረጃ በግዙፍነታቸው አንደኛ እና ሶስተኛ የሆኑትን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ እና የኮይሻ ግድቦች ባለቤት በመሆናችን የንፁህ የኃይል ማመንጨት ስራችንን እና ጥረታችንን አቻ የሌለው ያደርገዋል፡፡ በቅርብ ርቀት በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኘውን የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅን በምንመርቅበት በአሁኑ ወቅት የኮይሻ ግድብ ለአካባቢው የቱሪዝም ዕድል ተጨማሪ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

On my 12th review of the Koysha hydroelectric power project since 2020, I’m pleased to witness the stage of construction has reached 62% through our reformed project management and follow up processes. Our national clean energy endeavor is unparalleled as we possess the first and third largest hydroelectric dams in Africa, the GERD and Koysha respectively. As we inaugurate the nearby Chebera Elephant Paw Lodge within the Chebera Churchura National Park, the Koysha Dam and its vicinity will also contribute to the tourism potential of the area.