Get Mystery Box with random crypto!

ዓለም ጸንታ የቆመችው ለሌሎች በሚደረግ መልካም ነገር ነው። ገንዘባችንን፣ ዕውቀታችንንና ጉልበታች | Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

ዓለም ጸንታ የቆመችው ለሌሎች በሚደረግ መልካም ነገር ነው። ገንዘባችንን፣ ዕውቀታችንንና ጉልበታችንን እጅግ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከማዋል በላይ ሀገርን የመውደድ መገለጫ የለም።

ከለውጡ ወዲህ ከተከተልናቸው መርሖች አንዱ በማኅበራዊ ኃላፊነት ማኅበራዊ ችግሮችን መፍታት ነው። ማዕድ ማጋራት፣ የድኾችን ቤት መሥራት፣ ትምህርት ቤቶችንና የጤና ተቋማትን መገንባት፣ የችግረኛ ገበሬዎችን እርሻ ማረስ፣ አካባቢን አረንጓዴ ማድረግ፣ ባህል እንዲሆኑ ሠርተናል። ሚልዮኖችም የዚህ ተሳታፊ ሆነዋል። ከሕጻናት እስከ አረጋውያን ባህላቸው አድርገውታል።

በዚህ ዓመት በተደረጉት እነዚህ ማኅበራዊ አገልግሎቶች የተሳተፋችሁትን ሁሉ በራሴና በመንግሥት ስም አመሰግናችኋለሁ። አገልግሎቱን ያገኙት ወገኖች እንደሚመርቁንና እንደሚጸልዩለን አምናለሁ። ኢትዮጵያችን በእነዚህ ወገኖች ምርቃትና ጸሎት ፈተናዎቿን አሸንፋ እንደምትጓዝ ርግጠኛ ነኝ።