Get Mystery Box with random crypto!

ዶ/ር አሕመዲን አህመድ የአማራ ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ ሁነው መሾማቸው ታውቋል። ዶ/ር አህመዲን | አቢሲኒያ - Times

ዶ/ር አሕመዲን አህመድ የአማራ ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ ሁነው መሾማቸው ታውቋል።

ዶ/ር አህመዲን ከዚህ ቀደም የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና በመከላከያ ሚነስቴር ተቋማት በሚኒስትር ዴኤታ መስራታቸው ይታወቃል። በዛሬው ዕለት የአማራ ክልል ብልጽግና ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው በፋሽስቱ ዐብይ አሕመድ መሾማቸው ተገልጿል።

ዶ/ር አሕመዲን አህመድ የአጣዬ እና አካባቢው ሕዝብ የሕዝብ ተወካይ (እንደራሴ) መሆናቸው ይታወቃል። ነገር ግን አጣዬ ለአሥራ ሶስተኛ "ኦነግ ሸኔ" በሚል ስም ጥቃት ሲደርስባት ማስቆም አልቻሉም፤ የደረሰውን ጥቃትም ሲያወግዙ አላስተዋልነም።

የወከሉትን የአጣዬ እና አካባቢውን ሕዝብ መከራ እና ስቃይ ያልተጋሩ ግለሰብ ለአማራ ሕዝብ ያስባሉ ማለት ዘበት ነው።

በነገራችን ላይ ዶ/ር አሕመዲን አህመድ ለፋሽስቱ መሪ ዐቢይ አህመድ ታማኝ አገልጋይ ከሚባሉት እና የክልሉ ፕሬዚዳንት ትሆናለህ በሚል በተስፋ ሲኖሩ ከነበሩ የአማራ ክልል ባለስልጣናት አንደኛው መሆናቸውን አውቃለሁ። ይሄን ስልጣን ሲሰጡም አንድም የሸዋ አማራን በአማራ ብልጽግና ለመወከል ሲሆን ሁለትም ጠቅላዩ (አያልቅበት) በእጅ አዙር ክልሉን እንደፈለጉ ለመምራት ያስቀመጧቸው አሽከር መሆናቸው መታወቅ አለበት።

በመጨረሻ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ብልጽግና መሩ የፋሽስት ቡድን በመላው ኢትዮጵያ የዘር ማጽዳት እና ጭፍጨፋ እየፈፀመበት መሆኑን ያውቃል፤ በግለሰብ መቀያየርም ሆነ መሄድ እና መምጣት መብቱን እንደማያስከብር ተረድቶ ለሚፈልገው ግብ መታገል አለበት፤ እየታገለም ይገኛል።

@abisiniya_times
@abisiniya_times