Get Mystery Box with random crypto!

አገዛዙ የተሰፋው ከውሸት እና ክህደት ነው የምንለው በምክንያት ነው፤ #ኢንተርፖል ጋዜጠኛ ጎበዜን | አቢሲኒያ - Times

አገዛዙ የተሰፋው ከውሸት እና ክህደት ነው የምንለው በምክንያት ነው፤
#ኢንተርፖል ጋዜጠኛ ጎበዜን በተመለከተ የምናውቀው ነገር የለም የሚል መልስ ሰጥቷል።
-

አገዛዙ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን በInterpol ትብብር ነው የያዝኩት ብሎ መዋሸቱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ በርካታ ተቋማትና ግለሰቦች ለInterpol ፅፈዋል። ከእነዚህ መካከል የአማራ ማህበር በሰሜን አሜሪካ (AAA) ለፃፈው ድርጅቱ የአገዛዙን ቅጥፈት ያጋለጠ መልስ ሰጥቷል።

በነጠላ ' የድምጽ ቅጂ'* የሽብርተኝነት ክስ ፈጥሮ አማራን ፈርጆ ማሳደድ የጀመረው ፋሽስቱ አገዛዝ ድምጹ በAI የተፈበረከ መሆኑ በተረጋገጠ ማግስት፣ በዚህ ፖለቲካዊ የጥላቻ ክስ ሰለባ የሆነው ጋዜጠኛ ጎበዜን በተመለከተ የሰራው ዘገባም ኢንተርፖልን እንደማይመለከት ተረጋግጧል።

እነዚህ ገዢ ሀቆች ናቸው። እነዚህ ሀቆች አገዛዙ በማን አለብኝነት የሚፈጽመውን ጥቃት ወንጀልነቱን ሁሉም ባለአዕምሮ በግልጽ መረዳት የሚችለው ነው።
እናም ይህን ጥቃት በመቃወም፣ በደልን እና በዳይን የሚታገለው የአማራ ህዝብ አላማው እና የቆመበት መስመር ተገቢ እና ትክክለኛ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
ይህን ፍትሀዊ ተጋድሎ ለእኛ ግዴታችን ቢሆንም ፍትህ የሚያሳስበው ሁሉ የተጋድሎው አጋር እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን።

@abisiniya_times
@abisiniya_times