Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ለህክምና ወደ ውጭ እንዲሄዱ በፍርድ ቤት ተፈቅዷል | አቢሲኒያ - Times

ሰበር ዜና

ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ለህክምና ወደ ውጭ እንዲሄዱ በፍርድ ቤት ተፈቅዷል!

ከወራት በፊት ለህክምና ወደ እስራኤል ሃገር ለመሄድ ወደ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያቀኑት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ከሃገር እንዳይወጡ መከልከላቸው ይታወቃል።
ይህንንም ተከትሎ ጀነራል ተፈራ ማሞ ክስ መስርተዋል።
ፍርድ ቤቱም በጀነራል ተፈራ ማሞ ላይ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በህገወጥ መልክ ክልከላ ፈፅመዋል ብሏል።
በዚህም ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ከሃገር የመውጣት በህግ የተሰጣቸውን መብት የገደበ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ከአገር ወጥተው እንዲታከሙ ወስኗል ሲሉ ጠበቃቸው ለሮሃ ቲቪ ተናግረዋል።

ምንጭ ፦ ሮሀ ሚዲያ
#Share
@abisiniya_times