Get Mystery Box with random crypto!

#NEAEA ' ... አሁን የመቁረጫ ነጥቡ ( የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ) ይለያል አይለይም | የእውቀት ማህደር ®

#NEAEA

" ... አሁን የመቁረጫ ነጥቡ ( የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ) ይለያል አይለይም የሚለውን ኤጀንሲው ሊወስን አይችልም፤ የኤጀንሲውም ስልጣን አይደለም " - አቶ ተፈራ ፈይሳ

በሁለተኛው ዙር የሀገር አቀፍ ፈተና በፀጥታ ችግር ምክንያት ፈተና ላይ መቀመጥ ያልቻሉ ተማሪዎች ከጥቂት ቀናት በፊት ፈተናቸውን ወስደዋል።

በአጠቃላይ በአማራ፣ አፋር፣ኦሮሙያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከ60 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተና ወስደዋል።

ፈተናውም የወሰዱ ተማሪዎች እና የትምህርት ባለሙያዎች " ተፈታኞች ያሳለፉትን የስነልቦ ጫና እና አስቸጋሪ ሁኔታ ከግምት ያስገባ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ሊኖር " ይገባል እያሉ ይገኛሉ።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክታ ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል ይህንን የመወሰን ስልጣን የኤጀንሲው እንዳልሆነ ገልፀዋል።

አቶ ተፈራ ፈይሳ ፥ " ... ያሉ ጥያቄዎች አሉ፤ ይሄን ኤጀንሲው አሁን ላይ የሚለውም ምንም ነገር የለም። በዚህ ደረጃ ኤጀንሲው አይወስንም ፤ ይህ ትልቅ ጉዳይ ስለሆነ። ዞሮ ዞሮ ችግሩ እንዳለ እንረዳለን። ችግሩን ለመፍታት እኛ የተወሰነ ጊዜ ከመስጠት ባሻገር አሁን የመቁረጫ ነጥቡ ይለያል አይለይም የሚለውን ኤጀንሲው ሊወስን አይችልም የኤጀንሲውም ስልጣን አይደለም። ...ይሄን የሚወስነው መንግስት ነው "

በሌላ በኩል ፤ ኤጀንሲው በትግራይ ክልል ካሉ ተማሪዎች ጋር በተያያዘ የታሰበ ነገር ያለ እንደሆነ ከሬድዮ ጣቢያው የተጠየቁት አቶ ተፈራ ፥ " በእኛ በኩል የሚፈታ አይደለም። ከአጠቃላይ ከሀገራዊ ፀጥታ ጋር የሚታይ ስለሆነ ሀገራዊ ፀጥታው ሲረጋገጥ ፣ ትግራይም እንደማንኛውም ክልል ሰላም ሲሆን ፈተና የምንፈትነው " ሲሉ መልሰዋል።

#MesfinArageVOA